Hiber Radio: በኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ላይ የግድያ ሙከራ መደረጉ፣ጎሳ ተኮሩ ፌደራሊዝም ታላቅ ፈተና እና እየፈረሰ ያለው ኢህአዴግ፣የቬጋሱ ጥቃት አድራሽ የጻፈው ማስታወሻ ይፋ መሆን፣ተጨማሪ ወታደር ወደ ጎንደር፣የጥሩነሽ ዲባባ የማራቶን ድል መቀዳጀት ፣የአባዱላ ጉዳይ ሌሎችም ዜናዎች አሉን

የህብር ሬዲዮ  መስከረም 28 ቀን 2010  ፕሮግራም

<…በሱማሌ ልዩ ሐይል በኦሮሚያ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማዳከምና ሕዝቡ በጊዜያዊ ችግር ተይዞ ዋናውን ጥያቄ ይረሳል ብለው በንጹሃን ላይ የወሰዱት ጭፍጨፋ አገሪቱን ጭምር ወደ አደገኛ ሁኔታ እያመራና በውስጥም …> ጦማሪና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ስዩም ተሾመ ስለ አገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ከሰጠን ሰፋ ያለ  ቃለ ምልልስ( ያድምጡት)

<..በቬጋስ አደጋው ሲደርስ የሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ ስራ ላይ ነበርኩ ።ሙዚቃው ነበር፣ የሆነ ነገር ርችት ሚመስል ነገር ይሰማል ማናችንም የጥይት ተኩስ ይሆናል ብለን አልገመትንም…> ወጣት ሜሮን ታደሰ በቬጋስ አንድ ግለሰብ ተኩስ በከፈተበትና ለ58 ንጹሃን ሞትና ከአምስት መቶ በላይ ከቆሰሉበት አደጋ እንዴት እንደተረፈች ከሰጠችን ቃለ ምልልስ(ቀሪውን ያድምጡት)

<…የደረሰው አደጋ አሳዛኝ ነው ነገር ግን ቬጋስ ባይሆን ኖሮ ከዚህም የከፋ ሊሆን ይችል ነበር እአንዳንዱ ሆቴል ጠንካራ ሴኩሪቲ መኖሩ ፖሊስ ፈጥኖ እርምጃ ባይወስድ ኖሮ እንደ ሰውዬው ዝግጅትና በክፍሉ እንደተገኘው መሳሪያ ብዛት ከዚህም የከፋ ይሆን ነበር…>  ዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን በቬጋስ ከደረሰው የዕሁዱ ችፍጨፋ በሁዋላ ስላለው ሁኔታ ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ቀሪውን አዳምጡት)

አሜሪካ በታሪኳ ያስተናገደችው ዘግናኙ የላስ ቬጋስ እልቂት ከአለም አካባቢ ያገኘው አስተያየት(ልዩ ጥንቅር)

 ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ላይ የግድያ ሙከራ መደረጉ

ጎሳ ተኮሩ የኢህአዴግ ፊደራሊዝም ታላቅ ፈተና ላይ መሆኑ ተገለጸ

እየፈረሰ ያለው ኢህአዴግ

የቬጋሱ ጥቃት አድራሽ የጻፈው ማስታወሻ ይፋ መሆን

ተጨማሪ ወታደር ወደ ጎንደር

የአህያ ቄራ ተጨማሪ ተቃውሞ

የጥሩነሽ ዲባባ የማራቶን ድል መቀዳጀት

የአባዱላ መልቀቂያና አንድምታውና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *