Hiber Radio: የቬጋሱን የዕሁዱን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ኤፍ ቢ አይ ጥሪ አቀረበ ፣ፖሊስ ያልተጣራ ወሬ ለምርመራው ጠቃሚ አለመሆኑን ገለጸ

(ህብር ሬዲዮ ላስ ቬጋስ) የዕሁዱን የኦክቶበር 1/2017 አሰቃቂ ጭፍጨፋን አስመልክቶ ምርመራው መቀጠሉንና አሉባልታ፣አልተጣራ ወሬና ይሆናል ሳይሆን እውነተኛ ለምርመራ ሂደቱ የሚረዳ መረጃ ወይም ጥቆማ ሕዝቡ እንዲሰጥ አዲስ ዘመቻ መጀመሩን ይፋ አደረገ። የላስ ቬጋስ ፖሊስ በበኩሉ እውነተኛ አልሆኑ ጥቆማዎች ለምርመራ ሂደቱ አጋዥ ባይሆኑም በማህበራዊ ሚዲያ ጨምሮ የደረሰውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ የሚወጡትን  በሙሉ መከታተሉን ገልጾ ተቃሚ እና እውነተና መረጃ ብቻ ምርመራውን ያግዛል ብሏል።

የአሜሪካ ፌደራል የምርመራ ቢሮ(ኤፍ.ቢ.አይ) የቬጋስ ሀላፊ ራውንሰን ዛሬ በሜትሮ ፖሊስ በሰጡት መግለጫ ስለ ጥቃት አድራሹ እውነተና መረጃ ያለው ማንም ሰው ያየውን እንዲናገር ጥሪ አድርገዋል። ለመራጃ መስቻ የኤፍ.ቢ.አይን ተዘጋጀ ቁጥር ይፋ አድርገዋል በዚህም መሰረት ማንኛውም ታማኝ መረጃ ያለው  በሚከተለው ስልክ ቁጥር call 1-800-CALL-FBI with credible tips (not rumor or theories) on the shooter or his activities. በማለት ገልጸዋል።

የላስ ቬጋስ ሜትሮ ፖሊስ በዋና አዛዡ ሰሪፍ ስር መግለቻውን የሰጡት ኬቨን ማክማሂል አማካኝነት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ብዙ ጊዜ የቬጋሱን መሰል የጅምላ ግድያ አድራጊዎች ዓላማቸው አስቀድሞ ወይ በማህበራዊ ሚዲያ፣በስልክ ልውውጥ ወይ በኮምፒዩተር ግንኙነት ላይ በሚደረግ ምርመራ ጥቃቱ ከደረሰም በሁዋላ ዓላማቸው እንደሚታወቅ ጠቁመው ዛሬም ፖሊስ የቬጋሱን ጥቃት አድራሽ ዓላማ ምም እንደሆነ አለማወቁንና ምርመራው ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተዋል።

የዕሁዱን ጭፍጨፋ የፈጸመው ስቲቨንፓዶክ አርፎበት የነበረው የማንዳላቤ ሆቴል የጥበቃ ሰራተና በአደጋው ወቅት ከዲስፓች በደረሰው ትዕዛዝ ወደ 32ተና ፎቅ ክፍት ወደሆነና አላርም ወደጮኸበት ክፍል ሄዶ ምርመራ ማካሄዱን ፣የተኩስ እሩምታ የከፈተው ሩም አጠገብ ከዕሁዱ ጥቃት አድራሽ በተከፈተበት ተኩስ እግሩ ላይ ተመቶ መቁሰሉን ፣ለፖሊስ ወሳን የነበረውን መረጃ ተኩሱ የተከፈተበትን 32ተኛ ፎቅና ስለሁኔታው መግለጹን በመጥቀስ በወቅቱ ስራውን ፖሊስ በተገቢው መንገድ ይፋ ባለማድረጉ ይቅርታ ጠይቀው እውነተና ጀግና መሆኑን በመግለጽ ስሙም በመገናኛ ብዙሃን አስቀድሞ እንደተገለጸው የሱስ ካምፖስ መባሉን አመልከተዋል።

ፖሊስ ከዕሁዱ ጥቃት አድራሽ መኪና ያገኘውን ተቀጣጣይ ንጥር ምንነት በስም የገለጸ ሲሆን ፍንዳታ የሚያደርሰው ታነራይድና አሚኒየም ናይትሬት መገኘቱን አመልክቶ እውነተና መረጃ ስለ ጥቃት አድራሹ እንቅስቃሴ ፣ማህበራዊ ግንኙነት፣የፋይናንስ ሁኔታና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ምርመራው እንደሚቀጥል አመልክተዋል። አይሲስ በተደጋጋሚ ትቃቱንና ትቃት አድራሹን አስመልክቶ የሚያወታውን መረጃ ማየቱን ገለጸው ፖሊስ ያ እውነት አለመሆኑንና የሀይማኖትም ሆነ የፖለቲካ ፍላጎት እንዳለው የሚአሳይ መረጃ አለመገኘቱን አሳውቋል። ያልተጨበጡ መረጃዎችና ወሬዎች የምርመራ ሂደቱን እንደማያግዙም አመልክቶ ከአንድ በላይ ጥቃት አድራሽ እንዳለ ተደርጎ ተወራውም ሀሰት መሆኑን በአጽንዎት ገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዕሁዱ ጥቃት ከተገደሉት 58 ንጹሃን አንዱ የሆነውና ለመዝናናት በሙዚቃ ኮንሰርቱ ላይ ከባለቤቱ ጋር ተገኝቶ ሕይወት ለማዳን ሲል የተገደለው የፖሊስ ባልደረባ የሆነውን ቻርልስተን ሀርትፊልድ  መታሰቢያ ስነ ስርኣት አስቀድሞ በወጣው መረጃ መሰረት ትላንት ማምሻውን፣ የከተማዋ ባለስልጣናት፣የፖሊስ ሀላፊዎችና በርካታ ፖሊሶች  በሺህ የሚቆጠሩ የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በፖሊስ መታሰቢያ ፓርክ በታላቅ ስነ ስርዓት ተካሂዷል።

በቬጋስ የዕሁዱን ጥቃት ተከትሎ በአንዳንድ ሆቴሎች ከዚህ ቀደም ባልነበረ ሁኔታ ወደ ሆቴል የሚገቡና የሚወጡ ላይ ለደህነት ሲባል ፍተሳ እተካሄደ ሲሆን ጥቃቱ ከሆቴል ሩሙ የተሰነዘረበት ማንዳላቤ ሆቴልና ሌሎች የኤም.ጂ.ኤም ኩባኔአ ንብረት የሆኑ ሄቴሎች በተመሳሳይ ፍተሳ ይቀጥላሉ አይቀጥሉም የታወቀ የለም።

ፖሊስ በምርመራው ሂደት የጥቃት አድራሹ ዋና ኣላማ ይታወቃል ብሎ ተስፋ እንደሚያደርግ በዛሬም መግለቻ ጠቅሶ ይህንኑ ወደፊት እንደሚአሳውቅ አመልክቷል።

የኔቫዳ መስኪት ነዋሪ ሆነው 64 ኣመቱ ስቲቭ ፓዶክ ፖለቲካም ሆነ የሀይማኖት ኣላማ  የሌለው በኑሮው የተደላደለ በአብዛናው ቁማር መጫወት የሚወድ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ከሆቴል ክፍሉ የተገኙትን 23 ጠመንጃዎች ጨምሮ በአጠቃላይ 47 ጠመንጃ የተገኘበት ሲሆን 33ቱን ባለፈው አንድ ዓመት መግዛቱን የወጡ መረጃዎችን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

የዛሬውን የፖሊስ መግለጫ እነሆ፦

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *