Hiber Radio: የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) በመተማ ከተማ ጥቃት መሰንዘሩን አስታወቀ | አዲስ ዘመን ሆቴል ላይ የቦምብ ጥቃት አድርሻለሁ ብሏል

በሰሜን ጎንደር የወያኔ ደህንነቶች መከማቻ ሆና በምትገኘው በመተማ ከተማ አዲስ ዘመን ሆቴል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ(አዴኃን) ትላንትና ማለትም ጥር 15÷2010 ዓ.ም ከምሽት 2:30 ላይ የህወሃት ወያኔ ቀኝ እጅና የሆቴሉ ባለቤት በሆነው ሀዲሽ በላዕይ እና አብረሁት የሚሰሩ ሰላዮች ስብስብ ላይ በእጅ ቦንብ ጥቃት ፈፅሟል፡፡ በተደረገውም ጥቃት ይህ መረጃ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ 3 በአደገኛ ጉዳት ላይ ሆስፒታል የሚገኙትን ጨምሮ 8ቱ ላይ ጥቃት ደርሶባቸዋል ሲል ሀላፊነቱን ወስዶ  ከአዴኃን ሕዝብ ግንኙነት የደረሰን የዜና መግለጫ ይፋ አድርጓል።

በግንባሩ መግለጫ መሰረት ግዳጁን የፈፀሙት የአዴኃን መቺ ታጋዮች በሚፈለገው ቦታ በሰላም እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ፡፡አዴኃን አማራ ህዝብን ሲያፍኑ፣ሲያስገድሉ እና ሲያሳድዱ የቆዩ የህወሃት ሰላዮች ላይ በየትኛው ቦታ እና ጊዜ እርምጃውን እንደሚቀጥል ይገልፃል ብሏል።

አዴአን በዚህ መግለጫ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጸው ትግላችን የአማራ ህዝብ እየደረሰበት ካለው ልዩ የሆነ የፖለቲካ፤የኢኮኖሚ፤የማህበራዊ፤የስነ-ልቦናና የዘር ጥቃት ነፃ ወጦ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተከበሩባትና ለዚህም የሚቆሙ ነፃና ገለልተኛ የዴሞክራሲ ተቋማት ዕውን የሚሆኑባት፤የኢትዮጵያ ህዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነት የተረጋገጠባት፤የህዝብ አንድነት፤ፍቅርና እኩልነት የጠነከረባት፤ጠንካራና ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ዕውን ሆና ማየት።ለዚህም የማንከፍለው መስዋዕትነት አይኖርም፡፡ ሲል የሚታገልለትን ዓላማ ጭምር በአጽንዎት አስታውሷል።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *