Hiber Radio: ወቅታዊ ዜና- በአማራ ስም የተደራጁ የተለያዩ ተቃዋሚ ድርጅቶች የጋራ አንድ ግንባር መመሰርታቸውን ገለጹ

 

የአማራ ሕዝብ ለረጅም በማንነቱ ሳቢያ የተከፈተበትን ጥቃት እያየ ሳይደራጅ መቆየቱ ያስቆቻቸውና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተደራጁና የአማራና የሌላውንም ኢትዮጵአዊ ጥቅም ለማስከበር በጋራ ለማስከበር የወሰኑና በኢትዮጵያ ህልውና ላይ የማይደራደሩ ተበታተኑ በአማራ ስም ተቋቋሙ ድርጅቶች ላለፉኢ አስራ አንድ ወራት ሲአደርጉት የነበረውን የውስጥ ውይይት አጠናቀው አንድ አማራ የፖለቲካ ሀይል ሆነው መውጣታቸውን ለህብር/ዘሐበሳ በላኩት መግለጫ ገለጹ።

የአንድ አማራ የፖለቲካ ሀይሎች መግለጫ የሚከተለው ሲሆን መግለጫውን ተከትሎ ወደፊት ተጨማሪ መረጃ ይዘን ለመምታት እንሞክራለን። ሙሉ መግለጫው እነሆ፦

አንድ አማራ የፖለቲካ ሃይሎች ግንባር የምስረታ መግለጫ

በትግራይ ነጻ አውጪ የወያኔዎች ቡድን ቅጥ ያጣ ዘረኝነት ኢትዮጵያ በታሪኳ አይታ ወደማታውቀው የትርምስና የጭለማ ዘመን ላይ ደርሳለች። ሕዝባዊ ትግሉም ተፋፍሞ አፋጣኝ መፍትሄ የሚፈልግ የፓለቲካ አጣብቂኝና መስቀለኛ መንገድ ላይ አድርሷታል:: በተለይ ላለፉት አራት አስዕርተ አመታት ጥላቻን ባነገቡ የትግራይ ወያኔዎችና ግብረአበሮቹ በቅንጅትና በቅንብር የአማራውን ነገድ በሁለንተናዊ መልኩ አዳክሞ ማንነቱን ለማጥፋት ይህ ቀረሽ የማይባል ዘመቻ ሲያካሂዱበት ቆይተዋል።

አማራው ለእናት ሃገሩ ካለው ቀናዒነት በዘር ተደራጅተው ኢላማ ሲያደርጉት ሃገሩንና አብሮነቱን አስጠብቆ ለማስቀጠል ሲል በታላቅ ትግዕስት መሪር መስዋዕትነትን እየከፈለ ቆይቷል:: የአማራው ነገድ ምንም ማንነቱን ለማጥፋት በትግራይ ወያኔዎች ቢዘመትበትም ለረጅም ግዜ ከብሄር አሰላለፍ ይልቅ የህብረብሄራዊ የትግል አቅጣጫን ይዞ ለነፃነት፣ ለዲሞክራሲና ለፍትህ የሚያደርገውን ትግል በስፋት ይዞ ቆይቷል። ሃገራዊ መግባባት በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ሃገራዊ አንድነትን ከመገንባት ይልቅ ፤ የአንድ አናሳ የትግራይ ገዢ ቡድን የበላይነት ከግዜ ወደ ግዜ የሚፈጽመውን ግፍ አጠናክሮ በመግፋቱ በሃገራዊ አመለካከት ጸንቶ የቆየውን የአማራውን ነገድ ራሱን ለመከላከልና ሕልውናውንም ለማቆየት በብሄር ማንነቱ ዙሪያ ተሰልፎ የሚያካሂደውን ትግል እጅግ ወሳኝ ወደሆነ ደረጃ እንዲያሸጋገረው አስገድዶታል። ይህን በአማራው ላይ የተከፈተውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማስቆምና ሕዝባችንን የመብቱ ባለቤት ለማደረግ በሃገር ወዳዶች አቀራራቢነት በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ያሉትን የአማራ ድርጅቶች በአንድ ግንባር አሰባስቦ የተጠናከረ ትግል ለማድረግ የሚያስችል ሃይል ለመፍጠር ላለፉት አስራአንድ ወራት እጅግ አድካሚና እልህ አስጨራሽ እንቅስቃሴ ሲደረግ ቆይቷል ።

በዚህ የረጅም ወራት እንቅስቃሴ በአማራ ስም የተደራጁና በኢትዮጵያ የግዛት አንድነት የሚያምኑትን የፖልቲካና የሲቪክ ተቋማት በመለስተኛ ፕሮግራም አሰልፎ የጋራ ግንባር ለመፍጠር ያደረግነው ሙከራ ምንም እንደታሰበው ሁሉንም ሃይሎች ባያካትትም የጋራ ትግሉን አስፈላጊንት በተረዱ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጋራ ጥረት አንድ አማራ የፖለቲካ ሃይሎች ግንባር መስርተናል። የአንድ አማራ ራዕይ የአማራው ሕዝብ የተቃጣበትን ሕልውናውን የማጥፋት ዘመቻ ለመመከት ሁለንተናዊ መብትና ጥቅሞቹን ለማስከበር ከአማራው ሌላ ማንም ሊኖር ስለማይችል የተበታተነውን የማህበረሰባችንን የትግል እንቅስቃሴ በተቀናጀ ሁኔታ ለማጠናከርና በሰለጠነ የትግል አቅጣጫ ለማስተባበር ነው። office@oneamhara.org 01/22/2018 Am/pr/No.001 እኛ የአንድ አማራ የፖለቲካ ሃይሎች ግንባር መስራቾች ወደዚህ ታላቅ ውሳኔ ላይ የደረስነው በሃገር ውስጥ በሕዝባችን ላይ የተከፈተው የጥፋት ዘመቻ ተባብሶ በቀጠለበት በዚህ ወቅት ምንም የአማራው ጉዳይ ጉዳያቸው አድርገው አቅማቸው የፈቀደውን ድጋፍ እያደረጉ ያሉ በአማራ ስም የተቋቋሙ ድርጅቶች ተሳትፎ በበጎ ሁኔታ የሚታይ ቢሆንም ከችግሩ ስፋትና ጥልቀት አንጻር በሚፈለገው ደረጃ ባለመሆኑ ይህንን ክፍተት በመሙላትና ያለትሄደባቸውን አማራጭ የትግል አቅጣጫዎችን ለማበርከት በሚቻለውና በማንኛውም መንገድ ትግሉን የማስተባበር ሃላፊነት ለመወጣት ነው።

ስለ ድርጅታችን ሆነ ስለቆምንለት አላማ ወደፊት በዝርዝር የምንገልጽ እና በቅርቡም በምናካሂደው ድርጅታዊ ጉባዔ የምናሳውቅ መሆኑን ለወገኖቻችን ማሳወቅ እንፈልጋለል። በዚህም አጋጣሚ በአማራው ላይ የተቃጣውን አደጋ ለመከላከል በቡድንም ሆነ በግል የሚንቀሳቀሱ ወገኖች መጥተው ለመቀላቀል በራችን ክፍት በመሆኑ ከሁሉም ታጋዮች ጋር የተባበረ እንቅስቃሴን ለመፍጠርና በየትኛውም የሃሳብ ነጥብ ላይ ለመነጋገር ዝግጁ መሆናችንን ስንገልጽ የተነሳንለትን አላማ ትክክለኛነት በመረዳት ከጎናችን እንደምትቆሙ በመተማመን ነው። በመጨረሻም የአማራ ወገናቸው ጉዳይ አሳስቧቸው መራራውን ትግል ተጋፍጠው በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገር በአማራነት ለቆሙት ሁሉም ወገኖች ያለንን ታላቅ አክብሮት እንገልጻለን። ትግሉን የማይጠቅም ፥ የሕዝባችንን መከራ ሊያረዝም ከሚችል ፤ የእርስበእርስ ሽኩቻ በመራቅ ሕልውናው አደጋ ላይ የወደቀውን ሕዝባችንን ለመታደግ አባቶቻችን ባስቀመጡልን የጨዋነትና የመከባበር ባህል ላይ ተመስርተን በመከባበርና በመደጋገፍ በጋራ ቆመን የህልውና ጠላታችንን እንድንታገል ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ድል ለሕዝባችን ! እውነተኛ አማራ እንኳን ተነጋግር ተያይቶ ይግባባል !!

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *