Hiber Radio: በቆቦ የትግራይ ወታደሮች በአማራ ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ እያካሄዱ ነው

ከአቻምየለህ ታምሩ

ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የቆቦ የአማራ ተጋድሎ የፋሽስት ወያኔ መዋቅር ወድሞ ሕዝቡ ራሱን እያስተዳደረ ቢሆንም በሄሊኮፍተር በታገዘው ጭፍጨፋ ግን ብዙ ሰው እስካሁንም ድረስ እንደቅጠል እየረገፈ ይገኛል። ቆቦ ከተማ ከኗሪው ቁጥር በሚበልጡ የትግራይ ወታደሮች ከበባ ውስጥ ናት። የሕዝባዊ ተጋድሎው መንስኤ ላለፉት ሀያ ስድስት የፋሽስት ወያኔ የአገዛዝ አመታት በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና ሰቆቃ ሲሆን መነሻው ግን በወልድያ ከተማ የትግራይ ወታደሮች ያካሄዱት ጭፍጨፋና የወልቃይት፣ የጠለምትና የሁመራ መሬት በትግራይ በግፍ መወረሩንና ባለመሬቶቹ ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ወድቀው የጅብ መጣላቸውን በመቃወም ነው።

የቆቦውን የአማራ ተጋድሎ ተከትሎ በቆቦ የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረ እንደሆነ የአገዛዙ ወናፎች በተለመደ ፈጠራቸው ላይ ተመስርተው የሀሰት ወሬ እያስተጋቡ ይገኛሉ። ገራሚው ነገር እነዚህ በቆቦ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት እንደተሰነዘረ የሚነግሩን የአገዛዙ ልሳኖች ትናንትና ቆቦ የትግራይ ነው ሲሉን የነበሩ ናቸው። ቆቦ የትግራይ ከሆነ እንዴት በትግራይ ምድር በትግራይ ተወላጆች ላይ ጥቃት ተሰነዘረ ትላላችሁ ብሎ የሚጠይቅ ቢኖር መልሳቸው ምን ይሆን? ቆቦስ የትግራይ ከሆነ ጥቃት ደረሰባቸው የሚባሉት «የትግራይ ተወላጆች» ለምን ወደ መቀሌ ይሄዳሉ?

ከባድ መስዕዋትነት በተከፈለበት በዚህ የቆቦ ሕዝባዊ ተጋድሎ አገዛዙ ለግፍ ተግባሩ የሚጠቀምባቸው ጸረ ሕዝብ ተቋማቱ በሙሉ ወድመዋል። አማራውን ባለርስትና ገበሬ ያለካሳ እያፈናቀለ ሜዳ ላይ በመጣል ከአሽንጌ ማዶ ለመጡ የወያኔ ሰዎች መሬት ያድል የነበረው የቆቦ መዘጋጃ ቤት መዘጋጃ ቤቱ ባፈናቀላቸውና ግፍ በፈጸመባቸው ግፉዓን ተቃጥሎ ሙሉ በሙሉ ወድሟል። ግፉዓኑ ሕዝብ ከሁሉ በፊት ተጋድሎውን የጀመረው የአገዛዙ ቀኝ እጅ የሆነው ኡስማን የሚባለውን የቆቦ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ኃላፊና ንጉሥ ዝናቡ የሚባለውን ከንቲባ መኖሪያ ቤት በማጋየት ነበር።

ኗሪው እየተፈናቀለ መዘጋጃ ቤት በሚሰጣቸው መሬት ላይ ህንጻ እንዲገነቡ ከአሸንጌ ማዶ ለመጡ የወያኔ ሰዎች ብቻ ገንዘብ የሚሰጠው ልማት ባንክም ግፍ ባንገሸገሽው ሕዝብ ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

ፋሽስት ወያኔ በትዕዛዝ ፍርድ የሚያሰጥበት የራያ ቆቦ ወረዳ ፍርድ ቤትም እንዲሁ በእሳት ዶግ አመድ ሆኗል። ማዘጋጃ ቤቱ ድሆችን ከመሬታቸው በማፈናቀል ከአሸንጌ ማዶ የመጣው የአገዛዙ እንደራሴ የገነባውና ብርሃኔ ኬንያ ሕንጻ የሚባለው የፋሽስት ወያኔ ሰላዮች መነሃሪያ የሆነው ብዙ የአገዛዙ የግፍ ቢሮዎችን የያዘው ህንጻም ጋይቷል።

ከቆቦ በስተ ሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ የአማራ ገበሬዎችን ከመሬታቸው በማፈናቀል ከአሽንጌ ማዶ የመጡ የወያኔ ሰዎች በተሰጠው መሬት ላይ ይካሄድ የነበረው ጎለሽ የአትክልትና ፍራፍሬ እርሻም በተፈናቀሉ ገበሬዎች ወድሟል።

ሁለተኛ ቀኑን በያዘው ሕዝባዊ ተጋድሎው የቆቦን ከተማ እስካሁን በወረሯት የትግራይ ወታደሮች እንደተከበበች ናች። ቆቦ ኢትዮጵያ ምድር ነው። በከተማው የሰፈረውን ድንበር ብቻ መጠበቅ የሚገባውን የትግራይ ወታደሮች ወረራ ላስተዋለ ግን ቆቦ በጠላት ጦር የተወረረች ያህል ይሰማዋል።

እስካሁን ባገኘሁት የተጣራ መረጃ መሰረት የአስር አመት ሕጻን ልጅን ጨምሮ ዘጠኝ ሴቶችና ሕጻናት ከብአዴን ጽህፈት ቤት በተተኮሰ የትግራይ ወታደሮች ጥይት ተጨፍጭፈዋል። ሕዝቡ ባካሄደው ራስ የመከላከል እርምጃም አንድ የትግራይ ወታደር የተጎዳ ሲሆን በፋሽስቶት ጥይት የሚወድቀው ሰላማዊ ሕዝብ ህክምና እንዳያገኝ ታግዶ ባለ ጊዜው የትግራይ ወታደር ግን የካቶሊክ ሚሺን ቆቦ ውስጥ ባቋቋመው ሆስፒታል ሲረዳ ቆይቶ ለተጨማሪ ሕክምና ወደ መቀሌ ሆስፒታል ተልኳል።

 

ሌላው አስገራሚ ነገር ባህር ዳር የተካሄደው አይነት ጭፍጨፋ ቆቦ መደገቡ ነው። የባህር ዳሩ ጭፍጨፋ ባብዛኛው የተካሄደው ነውረኛው ብአዴን ጽህፈት ቤት ጣሪያ ላይ ስናይፐር በጠመዱ የትግራይ ወታደሮች ነው። ቆቦም የሆነው ይህ ነው።

ልብ በሉ! ይህንን ሁሉ ንጹህ አማራ የጨፈጨፉት የትግራይ ወታደሮች የመሸጉትና የታጠቁት ካርታ እንዲያልቅ የተኮሱት ቆቦ ከተማ ከሚገኘው ከነውረኛው ብአዴን ጽህፈት ቤት ቅጥር ግቢ ነው። ዛሬ ቀን ላይ ቆቦን ይዞሮ የነበሩ ሁለት ቦንብ ጣይ ሄሊኮፍተሮች ለጨፍጫፊ የትግራይ ወታደሮች ተጨማሪ የጦር ትጥቅና ስንቅ አራግፈው የሄዱትም እዚሁ ቆቦ ከተማ በሚገኘው የብአዴን ጽህፈት ቤት ውስጥ ነው።

ብአዴን ለአማራ ሕዝብ መጥፊያነት የታለመለትን አላማ በትክክል እየሰራ ይገኛል። በየ አካባቢው የሚገኙ የብአዴን ቢኖዎች በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ስናይፐር የሚተኩሱ የትግራይ ወታደሮች መትረየስና ታንክ የሚጠምዱባቸው ምሽጎች ሆነዋል። ብአዴን የተቋቋመው ለአማራ እንደሚሰራ ሁሉ በአማራ ስም ነበር። ሆኖም ግን በየ አካባቢው ያሉ ቢሮዎቹ አማራን ለማጥቃት የሰለጠኑ የትግራይ ወታደሮች ታንክና መትረየው የሚጠምዱባቸው ምሽጎች ሆነዋል። ለዚህም ነው ብአዴን የፋሽስት ወያኔ ነውረኛ ድርጅት እንጂ የአማራ ሕዝብ አካል አይደለም የምንለ። የባህር ዳርሩ የብአዴን ጽህፈት ቤት የትግራይ ወታደሮች በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ስናይፐር ለመተኮስ እንደመሸጉበት ሁሉ የቆቦውም የብአዴን ጽህፈት ቤት ትናንትና ዛሬ የቆቦን ሕዝብ ለመጨፍጨፍ ስናይፐር የታጠቁ የትግራይ ወታደሮች መሽገውበት ውለው አድረዋል።

ከቆቦ ወደ ትግራይ የሚወስደው መንገድ በመዘጋቱ ነፍሰ በላ የትግራይ ወታደሮች እምቦቀቅላ የአማራ ህጻናትን ለመጨፍጨፍ የሰሜን እዝ ተጨማሪ የትግራይ ወታደሮች ከትግራይ ወደ ቆቦ በሄሊኮፍተር ተጉዘው ለግዳጅ ወደ ብአዴን ጽሁፈት ቤት ተሰማርተዋል። አማራን ለማጥቃት የሰለጠኑት የትግራይ ወታደሮች ለዘመቻ ሲሰማሩ «ግዳጅ ወጥተዋል» እንደሚባል መቼም ሁሉም ሰው የሚያውቀው እውነት ነው።

የወሎ መስመር በህዝባዊ ተቋውሞ መዘጋቱን ስርዓቱ አምኗል፡፡ ወደ ትግራይ የሚገቡ ነገሮች በሙሉ ተቋርጧል ሰላም ባስ ጨምሮ ማንኛውም የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ብሶት በወለደው ወጣት ተስተጓጉሏል የወያኔ ሠራዊት በወልዲያ ነዋሪ ላይ የተፈፀመው የንፁሓን ህዝብ ግድያና አሳዛኝ ደም መፍሰስ በህወሓት አባሎች ዘንድ ፍርሃት ፈጥሯል ህዝቡ የበቀል እርምጃ ይፈፅማል በማለት በስጋት ተጨንቀዋል፡፡ አብዛኛው የጨለማው አገዛዝ የጥቅም ተካፍይ ማህበርተኛ ድምፅ አጥፍተው ከወሎ ዙሪያና አካባቢ በፍጥነት እየለቀቁ መሆኑ ከነዋሪው ተሰምቷል፡፡

ህዝብ ያሸንፋል!”

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *