Hiber Radio: የደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮኮቦች ህብረት በወልዲያና በሌሎችም ቦታዎች በንጹሃን ላይ የሚደረገውን ጭፍጨፋ አውግዞ መግለጫ አወጣ

የሀገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ከደቡብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ኮኮቦች ህብረት የተሰጠ ድርጅታዊ የትግል አጋርነት መግለጫ፤

በመላው ኢትዮጵያ የተቀጣጠለውን የህዝቦች መሰረታዊ የፍትህ፣ የእኩልነት፣ የዲሞክራሲና የነፃነት ጥያቄዎች በሀይል ለመጨፍለቅ አምባገነኑ

የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ የሚያካደው ግድያና ጭፍጨፋ በከፋ ሁኔታ መቀጠሉ ታሪክ ይቅር የማይለው አሳፋሪና አሳዛኝ ክስተት ብቻ ሳይሆን ጊዜው

ሲደርስ በሕግ የሚያስጠይቅ፤ በሕዝብና በሀገር ላይ የተፈፀመ ከባድ ወንጀል ነው። ይህ የህወሓት/ኢህአዴግ ገዥ ቡድን የአገዛዝ ዘመኑን ለማራዘም ሆን

ብሎና አቅዶ በሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ የሚያካሂደው ጅምላ ግድያ፣ እስራት፣ ስቃይና መከራ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋና እየባሰ መጥቶ ሀገራችንን ወደ

ማትወጣበት አደገኛ ሁከት፤ ትርምስና ብጥብጥ እንድትገባ እያደረጋት ይገኛል። በተጨማሪም ክቡር የሆነው የወገኖቻችን ደም በየዕለቱ መፍሰሱና ግድያዉ

ያንገሸገሸው ወገናችን፤ እስከ አፍንጫው ከታጠቀዉ የአጋዚ ጦር ጋራ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት በጥንካሬ፣ በቆራጥነትና በጀግንነት እየተፋለመ ይገኛል።

በተለይም ከሰሞኑ በወሎ ወልዲያ የጥምቀት በዓሉን ሊያከብር የወጣዉን ህዝብ በዘመናዊ የጦር መሳሪያ ጭምር በታጠቁት አጋዚ ወታደሮች፤ ሌሎች የጦር

ሀይሉ እና ደህንነት አካላት መፈጸሙን ተከትሎ በቆቦ፤ መርሳ፤ ስሪንቃ እና በሌሎች የአከባቢ ከተሞች ህዝቦች መሰረታዊ ደሞክራሲያዊ መብቶቻቸዉን

ተጠቅመዉ አጋርነት በማሳየት ድምጻቸውን ለማሰማት በወጡ ሰላማዊ ህዝቦች ላይ ባካሄደው እና እየፈጸመ ባለው የጅምላ ፍጅት ሕፃናትን ጨምሮ ንፁሀን

ዜጎች የጭፍጨፋው ሰለባ ሁነዋል። በመሆኑም ይህንን አሰቃቂ ዕልቂት በጥብቅ ለማዉገዝ እና በደቡብ ህዝቦችና በመላዉ ሀገሪቱ ዕየተደረገ ያለዉን የነጻነት

ትግል አጋርነት ለመግለፅ የደቡብ ኢትዮጵያ አረንጋዴ ኮከቦች ሕብረት የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አዉጥቷል።

  1. የጦር ሠራዊቱና የአጋዚ ሀይል በአስቸካይ ከሕዝብ መሀል አንዲወጡና በሀገር አቀፍ ደረጃ የጦር ሀይሉ በሕዝብ ላይ እንዲዘምት የሠጡትን ትዕዛ

አንስተው ጠ/ሚንስትር ሀ/ማርያም ደሳለኝ በአስቸካይ ከሥልጣን እንዲወርዱ እያሳሰብን እዉነተኛ ዴሞክራሳዊ መንግስትና ስርዓት እንዲቋቋም

እንጠይቃለን።

  1. ፍጅቱን ያስፈፀሙ የህወሓት/ኢህአዴግ ጦር አበጋዞች፣ በድርጊቱ የተሳተፉ ፖሊሶችና ታጣቂዎች እንድሁም ሲቪል ባለስልጣናት በሰላማዊዉና የፍቅር

ህዝብ በሆነዉ የወሎ ወገኖቻችን ላይ ሆን ተብሎ የተፈጸመዉን ጅምላ ግድያ፣ እስራት፣ ስቃይና መከራ በገለልተኛ አካል በአስቸኳይ ተጣርቶ ለፍርድ

እንዲቀርቡ እና በሕዝብ ላይ በታወጀው ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ተገቢ ካሳ እንድያገኙ እየጠየቅን በወሎ ወልዲያ፣ በቆቦ፤ መርሳ፤ ስሪንቃ

እና ሌሎችም የአከባቢዉ ከተሞች በግፍ ታፍነው የተወሰዱና የታሰሩ ሁሉም ዜጎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ ከዕስር እንድፈቱ

እናሳሰባለን።

  1. የወሎ ወልዲያ፣ ቆቦ፤ መርሳ፤ ስሪንቃ እና የሌሎችም የአከባቢዉ ከተሞች ህዝብ ሆይ፤ የደቡብ አከባቢ ህዝብ በዝህ አስቸጋሪ ወቅት በሞታችሁና

በሃዝናችሁ ከጎናችሁ በመቆም የችግሮችን ሁሉ ምንጭ ለማድረቅ የሚታደርጉትን የነጻነትና የፊትህ ፀረ-ወያኔ ትግል አስፈላጊዉን ድጋፍ እና ትብብር

ያደርጋል።

  1. የደቡብ አከባቢ ወጣት ልጆች ሆይ በኦሮሞ፤ በአማራና በለሎችም አከባቢዎች የሚፈሰዉ ደም የገዛ ደማችን ስለሆነ የዚህን የትግል አጋርነት

ለመግለጽና ለማረጋገጥ በሲዳማ፤ በኮንሶ፤ በጉራጌ-ወልቂጤ፤ በሀዲያ፤ በጋሞ ጎፋ-አርባምንጭና ቁጫ፤ በቴፒ፤ በከፋ፤ በገዲኦ-ዲላ፤ በደቡብ ኦሞ፤

በስልጤ እና ለሎችም የደቡብ አከባቢዎች በመደረግ ላይ ያለዉን ፀረ-ወያኔ ትግል በተጠናከረ፤ በተጠና እና በተባበረ መልኩ እየተካሄደ በመሆኑ

ዛሬዉኑ ትግሉን እንድትቀላቀሉ ጥሪ እናቀርባለን::

  1. የህወሓት/ኢህአዴግ ገዥ ቡድን “የፖለቲካና የህሊና እሥረኞችን እፈታለሁ“ በማለት በሀገራችን ህዝቦች ልጆች ላይ ማላገጡን ትቶ በፖለቲካ

የአመለካከት ልዩነት ምክንያት የታሰሩትን የሲዳማ፤ የኮንሶ፤ የጉራጌ-ወልቂጤ፤ የሀዲያ፤ የጋሞ ጎፋ-አርባምንጭና ቁጫ፤ የቴፒ፤ የከፋ፤ የገዲኦ-ዲላ፤

የደቡብ ኦሞ፤ የስልጤ እና ለሎችም የፖለቲካና የህሊና እሥረኞችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ የመፍታት ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንድያደርግ

እናሳሰባለን።

  1. በሀገር ውስጥና ዉጭ ያላችሁ ተቃወሚ ኀይሎች በአስቸኳይ ሁሉንም ድርጅቶች የተሳተፉበት አንድ ጠንካራ የተቃወሚዎች ተቋም በማቋቋም

ትግሉን ወደ ከፍተኛና ህዝብን በምመጥን ደረጃ በማሸጋገር መምራት የወቅቱ አንገብጋቢ ምላሽ መሆኑን በመገንዘብ የሀገራችን ህዝቦች እያካሄዱ

የሉትን እልህ አስጨራሽና በድል ዋዜማ ላይ ያለዉን የፀረ-ወያኔ ትግል በተጠና እና በትኩረት መስራት ይጠበቅብናል። በዚህ መሰረት የአረንጓዴ

ኮኮቦች ህብረት ከሌሎች ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋራ የጀመረዉን እንቅስቃሴ ከምን ጊዜዉም በበለጠ አጠናክሮ ይቀጥል ።

በአጠቃላይ ለተጎዱ ወገኖቻችን ቤተሰቦች መፅናናትን እየተመኘን በትግሉ የተሠውና የተጎዱ ዜጎች የዲሞክራሲ ስማዕታት በመሆናቸው በሀገራችን ታሪክ

ዉስጥ ሁሌም ስታወሱና ሲዘከሩ ይኖራሉ:: በመጨረሻም የሕዝብ ትግል በማንኛውም የሀይል ርምጃ መጨፍለቅና መደምሰስ ስለማይቻል መላው የኢትዮጵያ

ሕዝብ እጅ ለእጅ ተያይዞ ይህንን የግፍ አገዛዝ ለመስወገድ ትግሉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ድርጅታችን ከሕዝቡ ጎን በፅናት መቆሙን እናረጋግጣለን ።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *