በአዲስ አበባ ሕዝቡ በአይ.ሲ.ስ የተወሰደውን እርምጃ በመቃወም በተለያዩ አቅጣጫዎች አደባባይ ወጣ ፣<<መንግስት የሌለው ኢትዮጵያ ብቻ ነው!>> << ወያኔ እኛን ከምትደበድብ አይ.ሲ.ስን ደብድብ>> << ይሌያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ!>> ሰልፈኛው፣ ተደብድበው የታሰሩ አሉ

cherkos-addis-ababa_001ዛሬ በአዲስ አበባ ሕዝቡ ያለማንም ቀስቃሽ አደባባይ ወጥቶ በሊቢያ በአሸባሪው አይ.ሲ.ስ የግፍ ግድያ ለተፈጸመባቸው ወገኖቹ ሐዘኑን በለቅሶ፣በመፈክር ገለጸ። ሰልፈኛው ከጨርቆስ ተነስቶ በየመንገዱ ያለው ሕዝብ እየተቀላቀለው በከፍተኛ ወኔ ቁጭቱን የገለጸ ሲሆን ቁጥሩ በርካታ የሆነውን ሕዝብ ለማስፈራራት በርከት ያሉ የፌዴራል ፖሊሶች ሰልፈኛውን የከበቡ ሲሆን << መንግስት የሌለን እኛ ብቻ ነን>> የሚሉና ሌሎች ቁጭቶቹን ሕዝቡ በማንሳቱ የተደበደቡና የታሰሩ ወጣቶች መኖራቸውን በሰልፉ ላይ የተሳተፉ በማህበራዊ ሚዲያው ያወጡት መረጃ ይገልጻል።

በስልጣን ላይ ያለው መንግስት በሊቢያ የሞቱትን ተከትሎ ያሳየው ኢትዮጵአዊ መሆናቸውን አላረጋገጥኩም የሚል ግዴለሽነት ለዛሬው ቁጣ የተቀላቀለበት ያለ ዝግጅት በተደረገ ሕዝባዊ ሰልፍ ላይ ተንጸባርቋል። << መንግስት የሌላት ኢትዮጵያ ናት>> <<ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ>> <<ሉዓላዊነት ለሕዝብ መቆም ነው!>> <<ያስደፈረን ወያኔ ነው>> <<ዌአኔ የመንደር ጀግና>> << ወያኔ እኛን ከምትደበድብ አይ.ሲ.ስን ደብድብ>> << ይሌያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ!>>

የሚሉ መፈክሮች ይጠቀሳሉ።

በዋናነት ያነሱ ሲሆን ለቅሶ ጩኸት እና ቁጭት የተቀላቀለበት ዝማሬ የነበረ ሲሆን አሽከርካሪዎች ለሰልፉ ድጋፍ ለመስጠት ጡሩንባ ሲያሰሙ በፖሊሶች መዋከብ ደርሶባቸዋል። ወጣቶች በቆመጥ እየተደበደቡ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ተይዘው መታሰራቸው ታውቋል።

ከከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ሲያመራ ከነበረው ሰልፈኛ መካከል በተለይ ከጨርቆስ እና ከቡልጋሪያ ማዞሪያ የተነሳው የሚጠቀስ ሲሆን የጨርቆሱ ቀድሞ በመነሳቱና በርካታ ሕዝብ በየመንገዱ የተቀላቀለው ሲሆን ከቡልጋሪያ ማዞሪያ የተነሳው በርካታ ሕዝብ ፈጥኖ ቢቀላቀለውም በፌዴራል ፖሊሶች በሀይል ተበትኗል።

ቁጥሩ በአስር ሺዎች ይቆጠራል የተባለው ሰልፈኛ በቁጭት መውጣት የስርኣቱን ሰዎች ያስደነገጠ መሆኑን ከስፍራው የወጣው መረጃ ያሳያል። የስርኣቱ ካድሬዎች << ለሐሙሱ ሰልፍ ሰው ሲወጣ ረብሻ ካለ መንግስት እርምጃ ይወስዳል!>> እያሉ በየመንደሩ ማስፈራራት የያዙ ሲሆን ለጊዜው የስርኣቱ ሰዎች ራሳቸው በአስተባባሪነት የጠሩት ሌላ ሰልፍ በነገው እለት ይደረጋል የሚል ጥሪ እየተላለፈ ይገኛል።

የሐሙሱ ሰልፍ አገር ቤት ባለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ ጽ/ቤት የተጠራ ሲሆን ብጹዕ አቡነ ማትያስ አስቀድመው በሰጡት መግለቻ የአሸባሪዎቹ ጥቃት የማንንም ሀይማኖት የማይወክል ነው ብለዋል። ሀሙስ በመስቀል አደባባይ ሕዝቡ ወጥቶ ሐዘኑን ይገልጻል ተብሎ ይጠበቃል። በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ረብሳ ይነሳል ሚል ስጋት ላይ ወድቋል።

በአዲስ አበባ ዛሬ የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ የሚያሳይ ፎቶ( ዘ_ሐበሻ)
በአዲስ አበባ ዛሬ የተደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ የሚያሳይ ፎቶ( ዘ_ሐበሻ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *