የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ዛሬ በቬጋስ ከሕዝቡ ጋር ይወያያሉ፣በአዲስ አበባ የአይ.ሲ.ስን ጥቃትን ለመቃወም የወጣው ሕዝብ በአገዛዙ ፖሊሶች ተደበደበ ፣የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታስረዋል ፣ የሻማ ማብራት ስነ ስርዓት ይደረጋል

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

police_beaten_isis_protester002police_addis_003 የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ዛሬ ማምሻውን በቬጋስ ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚወያዩበት የፓርያቸውን ወቅታዊ የትግል እንቅስቃሴና የአገር ቤቱን ተጨባጭ ሁኔታ በአካል ተገኝተው ለማስረዳት ትላንት ማምሻውን ቬጋስ ገብተዋል። ዛሬ ከቀኑ ማምሳውን በከተማው 5150 ስፕሪንግ ማውንቴን ጎዳና በካዚኖ ላውንጅ ስብሰባው ይደረጋል። ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ባለፈው ቅዳሜና እሁድ በሚኒሶታና በቺካጎ ካሉ ኢትዮጵአውያን ጋር ተገናኝተው የተወያዩ ሲሆን ከተሳታፊዎች የቀረቡ ጥያቄዎችንን መልሰው የተሳካ ውይይት ማድረጋቸውን ከስብሰባው አዘጋጆች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በሰሜን አሜሪካ በተሌኤዩ ከተሞች ለተጠራው የፓርቲው ስብሰባ ሊወጡ ሲሉ አስቀድሞ ከአገር ቤት እንዳይወጡ ታግደው የነበሩት የሰማያዊ ፓሪቲ ሊቀመንበር ከቀናት በሁዋላ የታገዱበት ምክንያት ሳይገለጽላቸው ፓስፖርታቸው ተመልሶላቸው ወጥተዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ በሊቢያ በአ.ይ.ሲ.ስ አሸባሪዎች ጥቃት በተፈጸመባቸው ኢትዮጵያውያን ያዘነው ሕዝብ አደባባይ መውጣቱን ተከትሎ ለጥቃቱ በአገዛዙ በኩል ለሟቾቹ ተገቢውን ክብርና ለጥቃቱም ተገቢው ምላሽ ባለመሰጠቱ ሕዝቡ ቁጭቱን ተቃውሞውን በማሰማት <<ይሌአል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ!>>፣ <<ያስደፈረን ዌአኔ ነው>> ፣ <<እኛን ከምትመቱ አይ.ሲ.ሲን ምቱ>> << ውርደት በቃን>> የሚሉ መፈክሮች መዝሙሮች ተስተጋብተዋል። በርካታ ሕዝብ በመስቀል አደባባይና በየአካባቢ ሰልፉና ተቃውሞውን ለማፈን ከተሰማሩትና የሀይል ትንኮሳ ባደረጉት ፖሊሶች ላይ ተቃውሞውን አሰምቷል። ባለስልጣናቱ በአደባባዩ ለተሰበሰበው ሕዝብ ንግግር ለማድረግ ሲሞክሩ ሕዝቡ<<ሌባ ሌባ >> በሚል በተቃውሞ እንዲያቋርጡ አስገድዷቸዋል። የፖሊስ ሀይል ያገኘውን ሁሉ መደብደቡን ህጻናትና አዛውንቶች ሳይቀር ለሐዘን ወጥተው መደብደባቸው ብዙዎችን አስገርሟል።

የዛሬውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ኢትዮጵያው በህወሃት የሚመራው አገዛዝ ቁጥራቸው አስር የሚደርሱ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ሆን ብሎ ለሰልፉ ሲንቀሳቀሱ የያዘ ሲሆን ማምሳውን ባወጣው መግለቻ ለዛሬው ተቃውሞ ሰማአዊ ፓርቲን ተጠያቂ አድርጎ ወንጅላል። ሰማያዊ ፓርቲ << መንግስታዊ ሽብር የህዝብን ቁጣ ያባብሳል እንጂ መፍትሔ አይሆንም!>> በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ የፓርው አባላት እንደማንም ዜጋ የተወካዮች ም/ቤት በጠራው ሰልፍ ላይ ለመገኘት ሲሄዱ አደባባይ ከመድረሳቸው በፊት እየታደኑ መታሰራቸውን ገልጿል። በዚህም ዛሬ ከታሰሩት መካከል 1- ወይንሸት ሞላ – የድርጅት ጉዳይ አባል (ወደ ሰልፉ በመሄድ ላይ ሳለች ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስጢፋኖስ አካባቢ ተይዛ ታስራለች) 2- ጠና ይታየው – የ2007 ሀገራዊ ምርጫ የተ/ም/ቤት ተወዳዳሪ (በሀይል እርምጃው ወቅት ተደብድቦ የታሰረ) 3- ኤርምያስ ስዩም – የፓርቲው አባል (በሀይል እርምጃው ወቅት ተደብድቦ የታሰረ) 4- ማስተዋል ፈቃዱ – የፓርቲው የቂርቆስ ክ/ከተማ አስተባባሪ (በሀይል እርምጃው ወቅት ተደብድቦ የታሰረ) 5- ዳንኤል ተስፋዬ – የፓርቲው የጉለሌ ክ/ከተማ አስተባባሪ (በሀይል እርምጃው ወቅት ተደብድቦ የታሰረ) 6- ቴዎድሮስ አስፋው – የአዲስ አበባ ምርጫ ጉዳይ ኮሚቴ ህ/ግንኙነት (በሀይል እርምጃው ወቅት ተደብድቦ የታሰረ) 7- እስክንድር ጥላሁን – የ2007 ሀገራዊ ምርጫ የተ/ም/ቤት ተወዳዳሪ (የታሰሩትን ለመጠየቅ ምግብ ይዞ በሄደበት የታሰረ) 8- ይድነቃቸው አዲስ – የ2007 ሀገራዊ ምርጫ የተ/ም/ቤት እጩ ተወዳዳሪ (የታሰሩትን ለመጠየቅ ምግብ ይዞ በሄደበት የታሰረ)   በየሚገኙ ሲሆን ከዛሬው የአደባባይ የፌዴራል ፖሊሶች ድብደባ ከተጎዱት በተጨማሪ በተለያዩ ጣቢያዎች በርካታ ወጣቶች መታሰራቸውን ነገረ ኢትዮጵያ የፓርቲው ልሳን ገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳላ በቬጋስ ዛሬ ከቀኑ 5 ፒ.ኤም ላይ 5150 ስፕሪንግ ማውንቴን ጎዳና ላይ በሚገኘው ካዚኖ ላውንጅ ፊት ለፊት በሊቢያ የአ.ሲ.ስ የጥቃት ሰለባ ለሆኑ ወገኖች የሻማ ማብራት ስነ ስርኣት ሚደረግ ሲሆን በርካታ ኢትዮጵአውአን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።የሻማ ማብራት ስነስርዓቱን የቬጋስ የኢትዮጵአ ኮሚኒቲና የኢትዮጵአ ራዕይ ማህበር በጋራ መጥራታቸውን አስታውቀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *