Hiber Radio: ወሬ ሲነግሩህ ሃሳብ ጨምርበት በአቻምየለህ ታምሩ

በአቻምየለህ ታምሩ

ኢትዮጵያ ውስጥ ካልተማረው ማይምነት የተማረም ማይምነት ይበዛል። ዶክተርና ፕሮፌሰር እየተባለ እነ ተስፋዬ ገብረዓብ ያሰራጩትን ፈጠራ በስፋት ያስተጋባል። ተስፋዬ ፈልስሞ እንካችሁ የሚለው ሸቀጥ «ምንጭህ ከምን?» ብሎ የሚጠይቅ ስለሌለ ሁሉም እንዳወረደው እየተቀበለ የተስፋዬን ፈጠራ እውቀት እያደረገው ይገኛል። ተስፋዬ የወያኔ ፕሮጀክቶች የሆኑትን «የቡርቃ ዝምታን» እና «ተራሮችን ያንቀጠቀጠ ትውልድን» የጻፈው በዚህ መልክ በበሬ ወለደ ነበር። ለነገሩ ሳይመረምር የሚያስተጋባ ካድሬ የሆነ ዶክተርና ፕሮፌሰር ተቀባይ ስላለው ለምን ይጨነቃል።

ዛሬ ጧት አንዳንድ ወሬ ደጋሚዎች አብይ አህመድ የኦህዴድ ሊቀመንበር መሆኑን ተከትሎ ግዑዙ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ተገፍቶ በለቀቀው ወንበር ላይ ሊቀመጥ ይችላል በሚል ስሌት ከመሬት ተነስተው «ኢትዮጵያ የኦሮሞ ጠቅላይ ሚንስትር ኖሯት አያውቅም» በማለት አብይ አህመድን የመጀመሪያው ኦሮሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር [ከሾሙት ማለቴ ነው] አድርገው ያወራሉ። ይገርማል! መቼም እንድ ድንቁርና እንደልብ የሚያናግርና ድፍረት የሚሰጥ የእውቀት ጾመኝነት የለም።

ኢትዮጵያ ከልጅ እያሱ ዘመን ጀምሮ እስከ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ድረስ፤ አልፎም በዘመነ ደርግ የአገዛዝ አመታት ሁሉ የኦሮሞ ተወላጆች የሆኑ ጠቅላይ ሚንስትሮች ነበሯት።

የመጀመሪያው የኦሮሞ ተወላጅ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ልጅ እያሱ እህታቸውን [ ስኂን ሚካኤል] አጋብተው ጠቅላይ ሚንስትር አድርገው የሾሟቸው ቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ሚካኤል ናቸው።

ሁለተኛው የኦሮሞ ተወላጅ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር የታላቁ ጀግና የራስ ጎበና ዳጨ የልጅ ልጅ ራስ አበባ አረጋይ ሲሆኑ ራስ አበበ አረጋይ ጠቅላይ ሚንስትር ቢትወደድ መኮነን እንዳልካቸው በ1947 ዓ. ም. ከሞቱ በኋላ ከ1947 እስከ 1953 ዓ.ም. ድረስ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል። በ1953 ዓ.ም. መንግሥቱ ንዋይ ስለገደላቸው የጀግናው አርበኛ ራስ አበባ አረጋይ የጠቅላይ ሚንስትርነት ቦታ በጊዜያዊነት በራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴ ተይዞ ቆይቶ በኋላ ላይ በጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተ ወልድ ተተክተዋል። የትኛውም አውሮፓዊ ትምህርት ቤት ያልሄዱት ራስ አበበ አረጋይ ጠቅላይ ሚንስትር በነበሩበት ወቅት ስላሳዩት የተለየ የአመራር ብቃት የራስ አበበ ካቢኔ ሚንስትር የነበሩ ብዙ አጋሮቻቸው መስክረውላቸዋል።

ኢትዮጵያ በደርግ ዘመን መጨረሻ የነበሯት ሌላኛው የኦሮሞ ተወላጅ ጠቅላይ ሚንስትር የአምቦ ልጅው ተስፋዬ ዲንቃ ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትር ተስፋዬ ዲንቃ ባለፈው አመት ከዚህ አለም በሞተ የተለዩ ሲሆን የሕይወት ዘመን ትውስታቸውን «Ethiopia During The Derg Years» በሚል በጻፉት ዳጎስ ያለ መጽሐፍ አስፍረዋል።

ደጋሚዎቹና የውሸቱ ፈጣሪዎቹ ሌት ተቀን የሚፈለፍሉት «የዘር ችግር» በዚያ ዘመን እዚህ ግባ የሚባል ችግር እንዳልነበረ ስለቢትወደድ ኃይለ ጊዮርጊስ ወልደ ሚካኤል ታሪክ የሚከተለውን ተጨማሪ ሕዳግ ላክል።

ነጋድራስ ኃይለ ጊዬርጊስን የአፄ ምኒሊክ የመጀመሪያዎቹን ሚንስትሮች ሲያቋቁሙ የንግድ እና ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አድርገዋቸው ነበር። ኋላ ግን አፄ ምኒልክ ታመው አልጋ ላይ በዋሉ ጊዜ እቴጌ ጣይቱ በቤተ መንግሥቱ ማዘዝ ሲጀምሩ አልተስማሙምና ሊያነሷቸው ሲቃረቡ እሳቸው ግን አራዳ ናቸውና ቶሎ ብለው የእቴጌ ጣይቱን የወንድም ልጅ ወ/ሮ የተመኙ አሉላን አግብተው ከውድቀት ተረፉ። ቀጥሎም እቴጌይቱ ከስልጣን ተነስተው ራስ ተሰማ የልጅ እያሱ ሞግዚት ሆነው አገር ሲያስተዳድሩ ምቀኛ ተነሳባቸው እና ከስልጣን ተሻሩ። ሆኖም ግን አሁንም ቢትወደድ አክሮባት ሰርተው ወ/ሮ የተመኙን ፈተው የራስ ቢትወደድ ተሰማን ልጅ ወ/ሮ ላቀችን አግብተው ጠላቶቻቸውን ኩም አደረጓቸው። ከራስ ተሰማ ሞት በኋላ ልጅ እያሱ ብቻቸውን አገር ማስተዳደር ሲጀምሩና የልጅ እያሱ አስተዳደር ጡንቻው ሲያፈረጥም አሁንም በድጋሜ ምቀኛ ቢነሳባቸው በደንምብ የተካኑበትን ስልት በመጠቀም ወ/ሮ ላቀችን በመፍታት የልጅ እያሱን ታላቅ እህት ወ/ሮ ስኂን ሚካኤልን አግብተው የጠቅላይ ሚንስትርነትን ሹመት ተጨምሮላቸው ቢትወደድ ተባሉ።

ይህ ሁሉ የሚያሳየን በጊዜው የነበረው የስልጣን ሽኩቻ እነ ፋሽስት ወያኔና ኦነግ እንደሚያራግቡት በዘር የተቧደኑ ሰዎች የሚያደርጉት ትግል ሳይሆን፣ በችሎታ፣ በቅርርብና በአምቻ ጋብቻ ያለ ዘር ልዩነት የሚደረግ እንደነበረ ነው። ለዚህ አስረጅውም ከፍ ሲል ከቀረበው የቢትወደድ ታሪክ በተሻለ የሚያስረዳ ሊኖር አይችልም። የአማራ የበላይነት እያሉ የሚያላዝኑ ሰዎች የሚጻፍላቸውን ተረት እንዳለ ሳያላምጡ የሚያወራርዱ በመሆናቸው ከማስረጃ ይልቅ በጩኸት የፈጠራ ታሪካቸውን ለማሳመን ሲጥሩ ይውላሉ።

በተረፈ ሳይመረምሩ ሀሳብ የሌለበት ወሬ ይዘው «ኢትዮጵያ የኦሮሞ ጠቅላይ ሚንስትር ኖሯት አያውቁም » ለሚሉ ወሬ ደጋሚዎች «ከመጠምጠም መማር ይቅደም» ፤ «ወሬ ሲነግሩህ ሀሳብ ጨምርበት» የሚለውን የአያቶቻችን ጥልቅ ምክር በመለገስ ልሰናበት!

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ፣ 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው ። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

One Comment on “Hiber Radio: ወሬ ሲነግሩህ ሃሳብ ጨምርበት በአቻምየለህ ታምሩ”

  1. Amen Achamyeleh! This was what has been missing from the political discourse the past 30-yrs or so. The facts, the facts were missing!
    In a time where a ProfessorEzkiel decries, I paraphrase “Amanuel Abraham-Minister of Mines… was discriminated against during the Emperor’s era…” shows the level of disconnect and misrepresentation by the so called elite. Regardless of the claim above, an individual who achieved a ministerial position during the Emperor’s time (or during any regime’s tenure for that matter) and who was an in-law of the Emperor is now claiming to have been discriminated against? How about the fact Sir, the fact that he was a Minister? Doesn’t that fact in and by itself refute all such claims for any rational observer?
    I applaud the author above for bringing out all our heroes and they are our heroes, Ethiopian heroes who happen to have an Oromo ethnicity! These and many, many thousands of proud and gallant Ethiopians who served their Country honorably happen to be Oromos and are our heroes, our role models, our patriots! They are us! There is absolutely no difference for all of us mosaic group of Ethiopians what the ethnicity of a hero is, who died to preserve our country from the Italian Invaders, from the Turks, from the Derbush, etc.
    And the best part of who we are as a people is the surfacing of this realization after 27-years of undermining of our “Ethiopian Identity”. We as Ethiopians are being born again through our new and young brand of leaders, viz. Lemma Megersa, Abiy Ahmed, etc. They realize the Oromos are the backbone for Ethiopia, period! And first and foremost they are Ethiopians, they have paid dearly for this country before Weyane and before that shaabiya disseminated the big lie they fabricated to destroy our national identity. Both Weyane and shaabiya knew they had to tear this fabric apart before they can consolidate power. But we are coming back!
    May the truth prevail in honor of our Grand Heroes, Abebe Aregay, Mesfin Seleshi, Kebede Bizunesh, etc., etc.,……

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *