Hiber Radio: ግልጽ ደብዳቤ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሙሉ ከኦሮሞ ቄሮ የተላለፈ ጥሪ

አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሕወሓት በሚጨፍርበት የሚንስትሮች ም/ቤት ጸድቋል። ከሶማሌ ክልል ተወክለው ለረጅም ጊዜ የቀድሞ የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ጀማል ድሪዬ ይህን የአፈና አዋጅ የፓርላማ አባላቱ በሕዝብ ላይ እንዳይጭኑ ሕዝቡ ተጽዕኖ እንዲአደርግባቸው ጥሪ አስተላልፈው ባለፈው ዕሁድ በህብር ራዲዮ ጥሪያቸውን በዜና ዘግበን ነበር። ዛሬ ቄሮ እንደ አቶ ጀማል ሁሉ ለፓርላማ አባላቱ ጥሪ አስተላልፎ አፋኙን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲቃወሙ ጥሪ አስተላልፏል። ቄሮ ጥሪ ተከትሎ ቀርቧል።ይህን ጥሪ ባለፉት ዓመታት የንጹሃን ሞትና መከራን ሲቃወሙ የነበሩ ሁሉ ሊደግፉት ይገባል የሚሉ ድምጾች ተበራክተዋል። ተከታተሉት።

ግልጽ ደብዳቤ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሙሉ ከኦሮሞ ቄሮ የተላለፈ ጥሪ

ከሁሉም አስቀድመን ባላችሁበት ሰላምታ ይድረሳችሁ።

ሁላችንም እንደሚናውቀው የኦሮሞ ቄሮዎች ህይውታችንን መስዋዕት አዲርገን የኦሮሞ ህዝብ መብትና ብሄርቤረሰቦች እኩልነት የተረገጋጠባትን ኢትዮጽያ ለመመስረት ሰላማዊ ትግል እያደረግን ነው። የኦሮሞ ህዝብ ሰላማዊ ትግል ይህችን አገር እየቀየራት ይገኛል።

ይሁን እንጅ አንባገነን የሆኑ የTPLF ጥቂት ኮንትሮባንዲስቶች ቡድን አገሪቷን ለማዝረፍ በተሃድሶ መሪዎች ና በቄሮ የተዘጋባቸዉን የዝርፍያ መንገድ መልሰዉ ለመቆጣጠር ፣ አገርቷን በጦር ሀይል ለማቆጠጣር አስቻኳይ ግዜ አወጅ እያዋጁ ይገኛሉ። ይሄ አዋጅ በማንኛውም ሁኔታ ተቀባይነት አይኖረዉም።

የተከበራችሁ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ኮንትሮባንድስቶች አገሪቷን ለመበዝበዝ እና ለመበታተን በኦሮሞ ህዝብና በመላው ብሄርቤረሰቦች ላይ የታዋጀ አዋጅ እንዲሰረዝ የበኩላችሁን የዜግነት ግደታ በመወጣት አገሪቷን ከዉድቀት እና ከመበታተን እንድታድኑ የኦሮሞ ቄሮ በዚህ ደብዳቤ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ከዚህ አልፎ አዋጁ የሚጸድቅ ከሆነ የኦሮሞ ቄሮና ህዝብ የአፀፋ ምላሽ ተጠያቂዎቹ ሕወሓት( TPLF) እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መሆናችሁን እናሳስባለን።

ከሰላምታጋር

የኦሮሞ ቄሮ”

 Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *