Hiber Radio: ሕወሓት ኦህዴድን ለማፍረስ እየሠራ ነው | የኦሮሚያ ፖሊስ ኮማንደሮች በኮማንድ ፖስቱ እየታሰሩ ነው ቀጣዩ እርምጃ በብአዴን ላይ ነው

                                                                                     ኮማንደር ነገራ ዱፌራ እና የኦሮሚያ ፖሊስ ከሰላማዊ ተቃዋሚዎች ጋር

ሕወሓት ኦህዴድን ለማፍረስ ቀን ለሊት እየሰራ መሆኑ ተገለጸ:: በኮማንድ ፖስቱ አማካኝነት የተለያዩ የክልሉ ባለስልጣናትን ወደ እስር ቤት መውሰዱን ቀጥሎበታል::

ከሁለት ቀናት በፊት የነቀምት ከተማ ከንቲባና ምክትል አስተዳደሩን ማሰሩን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ የሚታወስ ሲሆን እስሩ ቀጥሎ የኢሊባቡር ፖሊስ ኮማንደር ነገራ ዱፌራ; የምስራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ ኮማንደር ጫላ ተሰማ፣ የሐረር ፖሊስ ምክትል ኮማንደር እያሱ በኮማንድ ፖስቱ መታሰራቸው ታውቋል::

የመቱ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ከዚህ ቀደም በከተማው የሕወሓት አባልና ባለሀብት የሆኑ ግለሰብ የኦሮሞና የአማራ ሕዝብን የሚያጋጭ በቁቤ የተጻፈ ፍላየር ፣ አውቶማቲክ መሳሪያና ቦንብ እንዲሁም የኦነግ ባንዲራ የተያዘበት ሲሆን ፖሊስ በሕዝቡ ጥቆማ የተያዘ ሲሆን የሕወሓት አፈ ቀላጤዎች የፖለቲካ እስረኞች ሲፈቱ ለምን አይፈታም ሲሉ ከሚጠይቁለት አንዱ ነበር።

የኦሮሚያ ፖሊስ ከህዝቡ ጋር መወገኑና በሰላማዊ ሰዎች ላይ አልተኩስም ማለቱ በአምቦ፣በሐማሬሳ የጥቃት ዒላማ አድርጎት የፖሊስ አባላቱ በግልጽ በአጋዚ በተተኮሰ ጥይት የተገደሉ ሲሆን ሕገ ወጡን አስቸኳይ አዋጅ ተገን አድርጎ የኦሮሚአን አስተዳደር እና ፖሊስ መዋቅር ማፍረስ ቀጥለዋል።

የህብር/ዘሐበሳ ምንጮችን ጠቅሰን ቀደም ሲልም ይህን እርምጃ ለመውሰድ ማሰባቸውን ደጋግመን የዘገብን ሲሆን ሕወሃት በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ወቅት ቅሬታ አንስቶባቸው ከነበሩ ተቋማት የብአዴንና የኦህዴድን አመራሮች ተጠያቂ ለማድረግ መሞከሩን በክልሎቹ የሚገኙ መገናኛ ብዙሃንን ማጥላላትና በተወሰነ ደረጃ የሕዝቡን ብሶት ለማሰማት የወሰዱትን እርምጃ መግታት እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል።

ሌሎች በርካታ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮማንደሮችና አዛዦች እየታሰሩ ሲሆን ስም ዝርዝራቸው እንደደረሰን እናቀርባለን::

የሕወሓት አገዛዝ በአሁኑ ወቅት በአቶ አባዱላ ገመዳ አማካኝነት በክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ እና በድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ዓብይ አህመድ መካከል ልዩነቶችን በመፍጠር ድርጅቱ 3 አቋም በያዙ ቡድኖች እንዲከፈል እያደረገው ሲሆን ሕወሓት ኦህዴድን አፍርሶ ሌላ ተላላኪ ኦህዴድ ለመፍጠር ከፍተኛ ሥራ እየሰራ መሆኑን የዘ-ሐበሻ/ሕብር ምንጮችን ጠቅሰዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የኦህዴድ አመራር ላይ የታቀደ ጥቃት ሊሰነዘር መሆኑና አባዱላ እና በረከት የሕወሃት ታማኝ የሆኑትን የራሳቸውን ቡድን እያደራጁ መሆኑን አስቀድሞ የዘገብን ሲሆን ከእነ ደብረፂዮን ጋር አስቀድሞም ከአዋጁ በፊት ሲሰሩ እንደነበር እነዚሁ ምንጮች ይገልጻሉ።

ሕወሃት ኦህዴን ካፈረሰ በኋላ ወደ ብአዴን እንደሚሄድ እነዚሁ ምንጮች እየተናገሩ ነው::

 Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *