Hiber Radio: የአምቦ ዩኒቨርሲቲ መምህርና ጦማሪ ስዩም ተሾመ በኮማንድ ፖስት ታፍኖ ተወሰደ

በኢትዮጵያ ያለውን ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣የአስተዳደር ብልሹነትና የስልጣን ብልግና አዘወትሮ ከአገር ቤት በግልጽ በመጻፍ የሚታወቀው የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህርና ጦማሪ የሆነው ስዩም ተሾመ ዛሬ ማለዳ ከመኖሪያ ቤቱ በሕወሓት ኮማንድ ፖስት ታፍኖ መወሰዱን ለማወቅ ተቻለ።

ስዩም ተሾመ ከመታሰሩ በፊት የኮማንድ ፖስቱ በሕገ ወጥ መንገድ በጸደቀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሳቢአ ሊታሰር እንደሚችል ሰዎች እንደሚሰጉለት የጻፈ ሲሆን በገጹ ለዚህ ስጋት በሰጠው ምላሽ ሀሳቡን በነጻ መግለጹን እንደማያቆምና እስር ላይቀርለት እንደሚችል አስቀድሞ ማወቁን ገልጿል።

በተለያዩ ድረገጾች ላይ ሳይታክት በየዕለቱ በሃገራዊ ጉዳዮች ላይ አስተያየት በመስጠት የሚታወቀው የአምቦ ዩኒቨርስቲ መምህርና ጦማሪው  ስዩም ተሾመ ከዚህ ቀደምም በኮማንድ ፖስቱ ከሚሰራበት አምቦ ዩኒቨርስቲ ታፍኖ ተወስዶ ለአራት ወራት በጦላይ ወታደራዊ ካምፕ ድብደባና ስቃይ ተፈጽሞበት <<ተሐድሶ>> ባሉት ስልጠና ምስክር ወረቀት የተሰጠው ቢሆንም በእስር ላይ በደረሰበት የችካኔ ድብደባ ራሱን የቶርች ምሩቅ ሲል የተፈጸመበትን ግፍ ከእስር እንደተለቀቀ ማጋለጡ ይታወሳል።

ዛሬ ጠዋት 3 ሰዓት ገደማ ወሊሶ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በኮማንድ ፖስቱ  የጸጥታ ኃይሎች ታፍኖ  የተወሰደው ስዩም ተሾመ ወደ አዲስ አበባ እንዳጓጓዙት የዓይን እማኞች ተናግረዋል::

አገዛዙ በቅርቡ ጥቂት የህሊናና የፖለቲካ እስረኞችን ሲፈታ አንዳንዶች ቃሉን ጠብቆ ወደ ለውጥ የገባል ሱሉ ብዙዎች የነበራቸውን ጥርታሬ በተጭበረበረ መንገድ የጸደቀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ተከትሎት የመጣው እስራትና ግድያ አገዛዙ በሕዝብ ተገዶ ስልጣን እስካለቀቀ ድረስ በአገሪቱ ወዶ ለውጥ እንደማያመጣ ተደጋግሞ መገለጹ አይዘነጋም።

 

 Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *