Hiber Radio: የዶ/ር አብይ አህመድ ፈተናዎች | ክንፉ አሰፋ

ከልክ በላይ ለጥጠው‹፤ እንደ ልብ አንጠልጥል ፊልም ያቆዩትን ፍትግያ ትናንት በዜና ሲሰብሩት ደስታቸውን ይገልጹ የነበሩት ዜጎች ጥቂት አልነበሩም። ወትሮውን በስብሻለው ከሚለን ስራዓት አዲስ ነገርየሚጠብቅ ተስፈኛ ቢደሰት ብዙም አይደንቅም። የጠቅላይ ሚንስትር እንጂ የስራዓት ለውጥ መች ተመለከትን? ዶ/ር አብይ አህመድ በዚህ ቀውጢ ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኖ መመረጡ ግን ከክብሩናከስልጣኑ ይልቅ ፈተናው ያመዝናል።

ለሶስት ቀናት ተብሎ የተጀመረው ግብግብ ይሉት ክርክር  በተነገረለት ቀን መቋጨት ያለመቻሉ በራሱ የሚነግረን ነገር ነበር። አወዛጋቢው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ፣ ፓርላማ ላይ በጸደቀበት ወቅት  ዶ/ርአብይ  በስፍራው ባለመገኘታቸው የህወሃት ሰዎች ክፉኛ እንደተበሳጩ አይተናል። ይህንን ቅሬታ በብሎገሮቻቸውም ሳይቀር ሲገልጹልን ነበር።

ደስታቸውን ከልክ ባለፈ መንገድ እየገለጹ ያሉት ወገኖች ይህንን አጋጣሚ  እንደ ምክንያት ሳይሆን እንደ መዳረሻ ካዩት ግን በህዝብ ትግሉ የተከፈለው መስዋእትነት ሁሉ ከንቱ ነበር ማለት ያስችለናል።  የጠቅላይ ሚንስትርነት ስፍራ የለውጥ ማራመጃ ሳይሆን እንደ አንድ ትልቅ  ግብ ስናየው ነው ስህተቱ።

ማህደረ ትውስታችን አጭር ካልሆነ በስተቀር ሊያሳስበን የሚገባው አዋጁን ተከትሎ የበታች አመራሮች በሙሉ እስር ቤት መታጎራቸው እንጂ የኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስትር  መሆን አልነበረም። ስሜታችንንሊነካ የሚችለው  ስደት፣ አፈና እና ግድያው እንጂ በወታደሩ ክርን ውስጥ ያለች ሃገር ጠቅላይ ሚንስትር መሆን አልነበረም።

ግራም ነፈሰ ቀኝ ዶ/ር አብይ ተመርጠዋል።  ይህ ደግሞ ያለ ህወሃት በጎ ፈቃድ ከቶውንም ሊሆን አይችልም። ምርጫ፣ ብልጫ፣ ደብረጽዮን ሁለት ድምጽ፣ አብይ 108 ድምጽ፣ ምናምን የሚሉት ትርክትእኛን ትንሽ ፈገግ ቢያደርገንም ፈረንጆቹን ያሳምን ይሆናል።ምን አይነት ታኮ እንዳሰቡ ባይታወቅም፣  ምርጫቸው ሳይፈልጉት የሚውጡት መድሃኒት አይነት ይመስላል።  እንደ ኮሶ እያንገሸገሻቸው ዶ/ር አብይንበስፍራው አስቀምጠውታል።   ለዚህም አንዱ እሳቤ የኦሮሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን እንቅልፍ እየነሳቸው ያለውን የቄሮ አመጽ ሊያበርደው ይችላል ከሚል ሂሳብ ተነስተው ነው። የሰላማዊው ሽግግር ለውጥየሚሉት ጨዋታቸው  ደግሞ ለምዕራቡ አለም መሸቀያ ይሆናቸዋል።  የገቡበት አደገኛ ማጥ ፋታ አልሰጣቸውም።  ግዜ መግዛት አለባቸው።

አዲሱ ተመራጭ እርግጥ እንደ መለስ ዜናዊ ባለ ሙሉ ስልጣን ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል? በህገ መንግስቱ ላይ የሰፈፈረውን ስልጣን ተግባራዊ ያሚያደርግ  ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ ግዜ የሚፈታውጉዳይ ቢሆንም፡ በፊቱ ላይ ሁለት ነገሮች ተደቅነዋል።  እድል እና ፈተና። ምርጫው የሱ ነው።  እንደ አነሳሱ እድሉን ይጠቀምበታል ብለን እናምናለን። ዶ/ር አብይ የህዝብን  ጥያቄ መልሶ እርቅ እና ፍትህንየማስፈን እድል አለው። ይህንን ለማድረግ ደግሞ፡ ይህንን ከማይፈልጉ የህወሃት ጡረተኞች ጋር መፋጠጡ ግድ ይላል።  የህወሃት መርህ የሆነው የዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት በራሱ እንቅፋት ነው። ተግራሮቶቹንእና  እንቅፋቶቹን አልፎ  ይህንን እድል ከተጠቀመ ታሪክ ሰርቶ ያልፋል።  ያ ካልሆነ ግን እንደ ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ አሻንጉሊት ተብሎ የሞራልም ውድቀት ይሆንበታል።

ዶር አብይ የአዲሱ ትውልድ ትግል ውጤት ነው። ስለዚህም  ችግሩን ከላይ ሳይሆን ከታች፤  በውስጡ እየኖረ ያውቀዋል።  ከሌሎቹ በበለጠም ይረዳዋል።  እናም ይፈታዋል የሚል እሳቤ አለ። ይህንንሲያደርግ ብቻውን አይደለም። ለለውጥ የተነሳው ሃይል ከጀርባው እንዳለ ይገነዘባል።

አንደበተ ርቱዕ ነው። አብሮነትን እና ፍቅርን ይሰብካል።  ባገኘው መድረክ  ሁሉ ከዘር ጥበት ወጥቶ ኢትዮጵያን ከፍ የማድረግ አዝማሚያ ይታይበታል።  ይህን ማድረጉ ደግሞ ከኢትዮጵያዊነትንከሚያቀነቅኑ ሳይቀር ድጋፍ አግኝቷል። ይህ ሰፊ የህዝብ ድጋፍ ወታደራዊ አገዛዙ የከረቸመውን በር የመስበር ጡንቻ ይሆነዋል።

“መለስ የጀመረውን ልጨርስ ነው የመጣሁት” ብለው ነበር ሃይለማርያም ደሳለኝ በተሾሙ ወቅት። ዶ/ር አብይም ሃይሌ የጀመሩትን አንዳንድ ነገሮች ከዳር እንደሚያሰርስ ተስፋ አለን። ለምሳሌ ማዕከላዊሚዚየም ሆኖ ያስጎበኙናል።

አብይ ስፍራውን የያዘው ኢህአዴግን ለማዳን ነው ወይንስ ሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ? ግዜ ይጠይቃል። ጥያቄውን እሱ እና የለማ ቲም የሚመልሱት ይሆናል።  … መልካም እድል!

 Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *