Hiber Radio የአሸባሪው አይ.ሲ.ስ የመን መግባት በኢትዮጵያውያን ላይ ስጋት መደቀኑ፣ በሊቢያ ዛሬም ታፍነው የተወሰዱት መጨረሻ አለመታወቅ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር የኢትዮጵያውያን ለቅሶ ስርዓቱ እስካልተለወጠ ይቀጥላል ማለታቸው፣ በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያኑ የተቃውሞ ሰልፍ፣በጋምቤላ የአካባቢው ነዋሪዎችና የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ፍጥጫ፣ የዶ/ር አክሎግ የአሜሪካ መንግስት አሸባሪዎን የኢትዮጵያ መንግስት ከረዳ ለተሸበራው ሕዝብ ጥያቄ ምላሽ መስጠት አለበት ማለታቸውና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሐብታሙ አሰፋ

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-042615-050315

የህብር ሬዲዮ  ሚያዚያ 18  ቀን 2007 ፕሮግራም

< …የአሜሪካ መንግስት ህዝቡን የሚያሸብሩ እንደ ኢትዮጵያ መንግስት ያሉትን እየረዳ በአሸባሪዎች ለታረዱ ወገኖቻችን አልቆምም ማለቱ አግባብ አይደለም…የአገር ቤቱ አገዛዝ ጠመንጃውን ለሕዝቡ ጭቆና እያዋለ ይሄ ውርደት ሲመጣ መመከት ስላልቻለ ሕዝቡ የቤት አንበሳ የውጭ ሬሳ ማለቱ ትክክል ነው።ከጣሊያን ወረራ ወዲህ ይሄ ለኛ ትልቅ ውርደት ነው… >

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ   በሊቢያ ፣በደቡብ አፍሪካና በየመን ስለሞቱ ወገኖቻችንና አሁንስ ከዚህ ችግር እንዴት እንውጣ አስመልክቶ  ከሰጡን ማብራሪያ የተወሰደ

<… ኢህአዴግ ወዶም ይሁን በሕዝባዊ አመጽ ከስልጣን ቢወርድ ሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ኢትዮጵአውያን ጋር ሆኖ አገር ለመምራት የሚያስችል ያንን ታሳቢ ያደረገ  ስራ እየሰራን ነው… አገዛዙ ከስልጣን ወርዶ ለዜጎቹ በውስጥም በውጭም መብት የሚቆረቆር ስርዓት እስካልመጣ ድረስ ለቅሷችን አያበቃም…> ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በቬጋስ ለተሰብሳቢዎች ከተናገሩት (ሙሉውን ያዳምጡት)

የአይ.ሲ.ስ አሸባሪ ቡድን በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው የግፍ እርምጃና ዓለም አቀፉ ምላሽ  (ልዩ ጥንቅር)

<…አንድነትን ካፈረሱ በሁዋላ አባላቱን ሰማያዊ እንዲገቡ እየሰራህ ነው ብለው በሀሰት ከፓርቲው ፋይናንስ ጋር አያይዘው በሀሰተኛ ክስ ሊያስሩኝ ነበር ።ክትትሉ ግን ዛሬም በስደት ላይ  …>

አቶ ጸጋዬ አላምረው በስርዓቱ የፈረሰው የእውነተኛው አንድነት የም/ቤቱ ም/አፈ ጉባዔና የፓርቲው የፋይናንስ ሀላፊ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የሰማያዊ ፓርቲ የኢትዮጵያን ውርደት እና ሞት የሚያበቃው ይሄ ስርዓት ሲለወጥ ብቻ መሆኑን ገለፀ

በአሸባሪው አይኤስ የመን መግባት ኢትዮጵያውያን ስጋት ገብተዋል በደቡብ አፍሪካ መናገሻ ከተማ በአካባቢው የሚገኙ በርካታ ኢትዮጰያውያን የደረሰባቸውን የአካል ጉዳት የንብረት ውድመት በመቃወም ሀሙስ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸው ተሰማ

ከ28 በላይ ኢትዮጵያውያንን በሊቢያ ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው አይሲስ ላይ ከፍተኛ የአየርና የእግረኛ ጥቃት ተፈፀመበት

በደቡብ ምዕራብ ጋምቤላ የስደተኛ መጠለያ የሚገኝ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ከፍተኛ ውጥረት መንገሱ ተሰማ

የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ያለምንም ፍርድ አንድ ዓመት በእስር ማሳለፍ

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *