የአሸባሪው አይ.ሲ.ስ ዋና መሪ መሞቱ ይፋ ሆነ

በሊቢያ ኢትዮጵያውያንን በግፍ የገደለው የአሸባሪው የአይ.ሲስ ዋና መሪ አቡበከር አልባግዳዲ ሞተ

የአሸባሪው የአይ.ሲ.ስ ዋና መሪ የሆነው አቡበከር አልባግዳዲ ዛሬ መሞቱን የኢራን ራዲዮ ዘገበ። በሬዲዮው ዘገባ መሰረት ባለፈው ማርች አሜሪካ በወሰደችው የአየር ጥቃት በኢራቅ ውስጥ በጽኑ ቆስሎ የነበረ መሆኑን ገልጿል።

የአሸባሪው ድርጅት መሪ ከመሞቱ በፊት ተተኪውን አቡ አል አፍሪን የማድረግ እቅድ እንደነበረው ተገልጿል።

ዘ-ጋርዲአን አስቀድሞ ባውጣው ዘገባ የአሸባሪው አይ.ሲ.ስ ዋና መሪ በደረሰበት የአየር ጥቃት በጽኑ ቆስሎ ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሌላው የአሸባሪው የአይ.ሲስ ክንፍ የመን መግባቱን ተከትሎ በዚያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ስጋት ላይ መውደቃቸውን ህብር ሬዲዮ በየመን ሰንዓ የሚገኘውን ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖትን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳ።

ህብር ሬዲዮ በየቀኑ ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በዘ-ሐበሻ እናበስልክ 712-432-8451 ደውሎ ሁለትን በመጫን ማዳመጥ ይቻላል።abu-bakr-al-baghdadi_isis leader died

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *