Hiber Radio: በሶማሌ ክልል በአብዲ ኢሌ ትዕዛዝ አንድ ወጣት ታንቃ ተገደለች፣ተቃውሞ ተጠናክሮ ይቀጥላል ተብሏል

የሶማሌ ክልሉ ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌ የተነሳበትን ተቃውሞ ለማፈን የልዩ ሀይሉ ታጣቂዎች አፍነው የወሰዷትን ወጣት ጣይሲር ሞሀመድ ፉድ -ሞሀመድ አንቀው ገለው ዘዛ በቀብሪዳህር ጎዳና ላይ ጥለዋት መሄዳቸውን የክልሉ ተወላጅ አክቲቪስቶች ገለጹ።

የሶማሌ ክልሉ ፕ/ት አብዲ ኢሌ ባስተላለፈው ትዕዛዝ ወጣቷዋነ የገደሉዋት አጎቷ ሐጂ አቢሌ ፊሂዬ ከፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋዬ ጋር በአካባቢው ስላለው ሁኔታ ተገኛንተው በተናገሩበት ወቅት ስለ አብዲ ኢሌ ጠንካራ ተቃውሞ እና በዝርዝር የሚፈጽመውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በማጋለጣቸው ለበቀል ወጣቱዋ መገደሉዋን አክቲቪስቶቹ ገልጸዋል።

የወጣቱዋ በአብዲ ኢሌ ታጣቂዎች ታንቆ መገደል በክልሉ ከፍተኛ ቁጣ ሊቀሰቅስ እንደሚችልና የሰሞኑ ተቃውሞ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚችል ተገልጿል።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *