Hiber Radio አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም እንድትመረምር መጠየቁ፣በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን ሞተን ሻማ ከማብራታችሁ በፊት በሕይወት ታደጉን ሲሉ ጥሪ አስተላለፉ፣በእስራኤል የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የጠነከረ ተቃውሞ ተከትሎ ባለስልጣናት ዘረኛ እርምጃ የወሰደውን ፖሊስ እናባርራለን ማለታቸው፣ዶ/ር መረራ በአገር ቤት ያለው የወጣቱ ሁኔታ ምርጫ 97ን ያስታውሳል ማለታቸው፣ የመኢአድ አባላት እየታፈኑ መወሰድ መቀጠሉ፣ የጦማሪ ሶሊያና ሺመልስ ቃለ መጠይቅ፣ በኦቲዝም ጉዳይ ውይይት ከባለሙያዎችና ከወላጅ ጋር እና ሌሎችም

habtamu1

የህብር ሬዲዮ  ሚያዚያ 25  ቀን 2007 ፕሮግራም

< …በእስር ቤት በሴቶችም በወንዶችም ላይ የሚፈጸመው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የጭካኔ ቅጣት በእነ ኤዶም ላይ የተጀመረ አይደለም እነሱ ደፍረው በማዕካላዊ የተፈጸመባቸውን ማጋለጣቸው ነው። ይሄ ወንጀል በሰብዓዊነት ላይ የተሰራ በመሆኑ በይርጋ የሚቀር አይደለም ወንጀለኞች መቼም ቢሆን ለፍርድ የሚቀርቡበት ነው…እኛ ለራሳችን ነጻነት መቆም ያለብን እኛው የአሜሪካዋ ባለስልጣን ግን… >

ጦማሪ ሶሊያና ሽመልስ በማዕከላዊ ምርመራ ሳሉ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬና ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን በመርማሪዎች የተፈጸመባቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ያቀረቡትን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ለጠየቅናት ከሰጠችን ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<… በየመን ያለን ኢትዮጵያውያን እሳት ውስጥ ነው ያለነው አሸባሪዎቹ የሱኒ አማጽያንን ካረዱበት ቦታ እኔ ካለሁበት የየመን ዋና ከተማዋ ሰንዓ አርባ ኪሎ እርቀት ነው ያለው…ስንሞት ሻማ ቢበራልንና ሰልፍ ቢወጣልን ምን ይጠቅማል አስቀድሞ ወገን ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ ለዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር እና አይ.ኦ.ኤም ይጩህልን። በተለይ በኤደን ያሉት ወገኖቻችን ከፍተኛ ችግር ላይ ናቸው…>

ጋዜጠኛ ግሩም ተ/ሀይማኖት ከየመን ሰንዓ ለህብር ከሰጠው ወቅታዊ ማብራሪያና የድረሱልን ጥሪ መልዕክቱ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

በእስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በወገናቸው ላይ ለተወሰደው ዘረኛ እርምጃ ያሳዩት ቁጣ የተቀላቀለበት ተቃውሞና የባለስልጣናቱ ምላሽ   (ልዩ ጥንቅር)

ውይይት በኦቲዝም ላይ

ኦቲዝም ምንድነው? የኦቲዝም ያለባቸውን ልጆች እንዴት ለይተን በጊዜ ተገቢውን የህክምና እርዳታ ማግኘት ይችላሉ? ኦቲዝም ያለባቸው ልጆችና ወላጆቻቸው በማህበረሰባችን የሚገጥማቸው ፈተና እና መፍትሄው

ከዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ከአትላንታ፣ ሰናይት አድማሱ የስነ ልቦና ባለሙያ ከሎስ አንጀለስ እና ከዚያው ከተማ የሁለት ልጆች ወላጅ የሆነችው ወ/ሮ ፌቨን ፋንቱ ጋር ተወያይተናል(ሙሉውን ያዳምጡት)

<…መንግስት ለስልጣኑ ካድሬው ለሆዱ አስቸግሮናል ።ሕዝቡን ስብሰባ እንዳይወጣ ሞክረው አልተሳካላቸውም አርባና ሃምሳ ሺህ ሰው በተለይ ወጣቱ ግልብጥ ብሎ ወጥቷል። ሁኔታው ምርጫ 97ን ያስታውሳል…እኛን ደገፉ ባሏቸው ላይ የሚደረገው ጥቃት ቀጥሏል…>

ዶ/ር መረራ ጉዲና ስለ ወቅታዊው የፓርቲያቸው የምርጫ ቅስቀሳ እና በስርዓቱ ስለሚደረግባቸው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ ከሰጡን ማብራሪያ(ሙሉውን ያዳምጡ)

የክፍለ ዘመኑ የቡጢ ውድድር በቬጋስ እና የአሸናፊው ቡጢኛ ማይዌይዘርና የፓኩዋያ የቅዳሜ ምሽት ግብ ግብ(ውይይት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የአሜሪካ መንግስት የአገር ቤቱን አገዛዝ ከማሞካሸት እንዲቆጠብና ስለ ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት አያያዝ ትክክለኛ ምልከታ እንዲኖረው ተጠየቀ

በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን የአሸባሪዎች ጥቃት ሰለባ ከመሆናችን በፊት በቁማችን ድረሱልን አሉ

ዶ/ር መራራ ጉዲና በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የወጣቱ ስሜት ምርጫ 97 የሚያስታውስ መሆኑን ገለፁ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ስደተኛው ሲኖዶስ የሊቢያ ሰማዕታትን በየዓመቱ ለመዘከር ወሰነ

ሕዝቡ አሸባሪዎቹን በወገኖቹ ላይ የወሰደውን የግፍ ግድያ ኢንዳያይና እንዳያሰራጭ ተጠይቋል

በየመን የሚገኘው አይሲስ የሱኒ አማጽያንን በጭካኔ ገደለ

የኢትዮጵያኑ እጣ ፋንታ አልታወቀም

የእስራኤል ባለስልጣናት በኢትዮጵያ ቤተ እስራኤላዊ ላይ የዘረኝነት ጥቃት የፈፀመው ፓሊስ ከስራ እንደሚባረር አስታወቁ

ኤርትራ የኬኒያ ፕሬዝዳንት ሁሩ ኬኒያታ በአየር ክልሌ እንዳያመሩና ወደ አሜሪካ የሚያደርጉትን ጉዞ አላስተጓጎልኩም ስትል አስተባበለች

የመኢአድ አባላት ታድነው እየታሰሩ ነው

ጠ/ሚ/ር ኔታኒያሁ የኢትዮጵያውያኑን ተወካይ ሊያነጋግሩ ነው

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-050315-051015

(ህብርን በተጨማሪ  በዘሐበሻ እና በሌሎችም  ያዳምጡ። በተጨማሪ በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 2139924347 ይደውሉ)ነ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት  በቀጥታ በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽና  በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል በየቀኑ ለማዳመጥ 2 መጫን ብቻ በቂ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *