Hiber Radio: ብአዴን ሁለቱን የሕወሓት ቀኝ እጆች በረከትና ታደሰ ጥንቅሹን አገደ

በአማራ ሕዝብ ላይ የሕወሓትን የግፍ አጀንዳባላቸው ስልጣን ሲያስፈጽሙ ከቆዩት በድርጅቱ ውስጥ ከሕወሓት ቀኝ እጆች መካከል ሁለቱ አቶ በረከት ስምዖን እና ታደሰ ካሳ(ጥንቅሹ)ን ከማዕከላዊ ኮሚቴነት አገደ።

ብአዴን ለእግዱ ምክንያት አድርጎ የጠቀሰው  በጥረት ኮርፖሬት ላይ በፈፀሙት ተግባር ሲል በድፍኑ የገለጸ ሲሆን አቶ በረከት ስምኦን፣ሕላዌ ዮሴፈፍ እና ታደሰ ጥንቅሹ መቀሌ ላይ ከሕወሓት መሪዎች ጋር ለግንቦት 20 ከትመው ጸረ ለውጥ ምክር ከማድረግ በተጨማሪ በአማራ የተለያዩ ከተሞች በተለይ በረከትና ህላዌ እየተዘዋወሩ ለውጡን ለመቀልበስ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር አስቀድሞ በጊዜው መዘገባችን ይታወሳል።

የሕወሓት ባለስልታናት ከሰሩት ግፍ አቻ የሚሆን ጸረ አማራ ሕዝብ ግፍ በማቀድና በማስፈጸም ጉልህ ሚና ካላቸው የህወሓት ወኪል የሆኑ የብአዴን አመራሮች በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት በረከትና ታደሰ ናቸው።ሕዝቡ ባለፈው በደብረ ማርቆስ አቶ በረከት አሉበት የተባለ ሆቴል ላይ  ጥቃት ያደረሰ ሲሆን የሳቸው ነው የተባለ መኪናም እስከመቃጠል ደርሷል።ሕዝብ በእንደመር ስም ከፈጸሙት ወንጀል ሳይጠየቁ ነጻ ሊሆኑ አይገባም ከሚላቸው ውስጥ አቶ በረከትእና አቶ ታደሰ ካሳ ይገኙበታል።ብአዴን በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ  ዝርዝር መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ እነ አቶ በረከትን እስከ ጉባዔው ከማገድ አልፎ ደንቡን በማሻሻል የሕወሓት ተልኮ ፈጻሚዎች የሆኑትን ነባር አባላት እነ አዲሱ ለገሰን ጨምሮ በጉባዔ እንዳይሳተፉ ውሳኔ አሳልፏል።ነባር አባላት በሚል ታርጋ በየስብሰባው እየገቡ የህወሓትን ተልዕኮ ሲአስፈጹሙ የነበሩት አዲሱ ለገሰና ሌሎችም በዚህ ውሳኔ ዘለው የሚገቡበት ስብሰባ አብቅቷል።

አቶ አዲሱ ለገሰ በምርጫ 97 እነ መለስን ኢንተር ሐሞይ ቅስቀሳ አጠናክሮ የአማራ ሕዝብ ላይ ሰፊ ጥፋት እንዲፈጸም ያደረገና ፋና በተሰኘው የኢህአዴግ ልሳን በሬዲዮ ቀርቦ ጸረ አማራ ቅስቀሳ ያደረገ ከሕወሃት ታማኝ አገልጋዮች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *