በእስር ላይ በሚገኙት እነሀብታሙ አያሌው ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠባቸው

Yeshewas_habtamu_daniel_abreha_001

በሽብርተኝነት ወንጀል ተጠርጥረው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ 19ኛ ወንጀል ችሎት ጉዳያቸው እየታየ፣ እና በእነዘላላም ወርቅአፈራሁ የክስ መዝገብ ተከስሰው የሚገኙት እነሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ዳንኤል ሺበሺ፣ ባህሩ ታዬ …የአቃቤ ሕግ ምስክሮችን ለመስማት ለሰኔ 1፣ 2 እና 3 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ዛሬ በችሎት ጸሀፊ በኩል እንደተሰጣቸው ጠበቃቸው አቶ ተማም አባቡልጉ ገልጸዋል፡፡

ተከሳሾቹ ወደፍርድ ቤት ቢመጡም የችሎት ጸሐፊው ‹‹ተጠርጣሪዎቹ በታሰሩበት ቦታ ከ20 ቀናት በፊት ቀኑ መቀየሩ ተናግሯቸው ነበር፡፡ እርሶንም ማግኘት ስላልቻልን ነው ቀኑን ያልነገርኖት›› እንዳሏቸው የጠቆሙት ጠበቃ ተማም በዛሬው ዕለት ችሎት ስላልተሰየመ ደንበኞቻቸው ተመልሰው ወደቂሊንጦ እንደሚያመሩ ተናግረዋል፡፡

ተከሳሾቹ፣ ከዚህ ቀደም በነበራቸው የፍርድ ቤት ውሎ ለዛሬ ተቀጥረው የነበሩት የአቃቤ ህግ ምስክሮችን በተከታታይ ቀናት ለመስማት መሆኑ ይታወሳል፡፡

(ህብር ሬዲዮን ዘወትር ከህብርና በዘሐበሻ ድህረ ገጽ በተጨማሪ በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 7124328451 ይደውሉ)

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *