Hiber Radio የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ዕቅድ ከፍተኛ ትችት ገጠመው “ፕሬዝዳንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ሄዱ አልሄዱ የመብት ረገጣው አይቆምም” አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን ፣ ዶ/ር መረራ የፕ/ት ኦባማ ኢትዮጵያ ለመሄድ መዘጋጀት ከአምባገነኖች ጋር መሞዳሞድ ለራሳቸውም አሳፋሪ መሆኑን መግለጻቸው እና ሌሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ የሰኔ 14  ቀን 2007 ፕሮግራም

<< …ኦባማ ለብዙ የአፍሪካ ወጣቶች በአጠቃላይ ለዓለምም ጭምር አዲስ የትውልድ መሪ ሆኖ ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን በዓለም እንዲያብብ ያደርጋል ተብሎ የተጠበቀ ሰው በመጨረሻ ከዲክታተሮች ጋር ዝቅ ብሎ መሞዳሞድ ውስጥ መግባቱ በዚህ ደረጃ ዝቅ ማለቱ ለኛ ብቻ ሳይሆን ለራሱም ቢሆን አሳፋሪ ነው  …>> ዶ/ር መረራ ጉዲና  የኦባማን ወደ ኢትዮጵያ መጓዝ በተመለከተ ካደረግንላቸው  ቃለ መጠይቅ  የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…የኦባማ ወደ ኢትዮጵያ መሄድ የሚያሳየው የኢትዮጵያን መንግስት ተላላኪነት እንጅ ዲሞክራሲያዊነት አይደለም ።  ጦር ላኩ ሲባል ይልካሉ … ይህ የማንቂያ ደውል ነው በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ድምፁ እንዲሰማ ስትራቴጂ ነድፎ መንቀሳቀስ አለበት…> ከዞን ዘጠኝ ጦማሪያን አንዷ ከሆነችው ሶሊያና ሺመልስ ጋር ካደረግነው ቃለ ምልልስ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ርዕዮት ዓለሙ ጡቷን አሁንም ያማታል ሆስፒታል ከሄደች ከአንድ አመት በላይ ሆኗቷል… እኔም አንድ አመት ከስምንት ወር እንዳልጠይቃት የተደረገብኝ እግድ ተነስቶ መጠየቅ ከጀመርኩ ገና ሁለተኛ ሳምንቴ ነው አሁንም በሌሎች ሰዎች እንዳትጎበኝ እንደተከለከለ ነው…> እስከዳር አለሙ  ከጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ እህት ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ጀኔራል ጃጋማ ኬሎ እና አርበኛ አምዴ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ አላቸው…ጄኔራል ጃጋማ የበጋ መብረቅ የተባሉት ወደአዲስ አበባ ሲገሰግስ የነበረውን የፋሽስት ጦር ከጓደኞቻቸው ጋር ወግተው ታላቅ ጄብዱ በመፈፀማቸው ነው…>በማህበራዊ ሚዲያ የታሪክ ተራኪው ኤድዋርዶ ባይሮኖ ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…አንድ ነገር ስለ ጄኔራል ጃጋማ ኬሎ መጨመር እፈልጋለሁ ። ጣሊያን በአስተርጓሚ እኛ ጸባችን ከእናንተ ጋር አይደለም ከአማራ ጋር ነው ሲላቸው ሰርገኛ ጤፍ አስመጥተው እሳቸውም ይህን ለይልኝ ሲሉ ይህን መለየት ከባድ ነው ነበር ያላቸው ዛሬ አንዱን ካንዱ ለማጋጨት የሚተጉት ዘረኞች ባለዕራዕይ ነን ሲሉ ያ ከየት እንደመጣ የጄኔራል ጃጋማ ኬሎ በዚያ ዘመን አስተዋይነት አብሮ ቢጠቀስ…> አድማጭ ስለ ጄኔራል ጃጋማ ያነበቡትን ጠቅሰው ከጠየቁት(ያዳምጡት)

የዘጠኝ ጥቁር አሜሪካውያን በደቡብ ካሮላይና ግዛት በፀሎት ቤት ውስጥ ሳሉ በነጭ  ዘረኛ ወጣት አሜሪካዊ መገደልን ተከትሎ በድፍን አሜሪካ የተጫረው የዘር እና የሽብርተኝነት ውጥረት ሲፈተሽ ( ልዩ ዘገባ )

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ዕቅድ ከፍተኛ ትችት ገጠመው

“ፕሬዝዳንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ሄዱ አልሄዱ የመብት ረገጣው አይቆምም” አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን

አል ሸባብ በኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት የጥበቃ ኬላ ላይ ጥቃት ሰነዘረ

የሰማያዊ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች አሁንም ወደ ሳሙኤል ቤተሰቦች ለለቅሶ እንዳይሄዱ መታገዳቸው ተገለፀ

የአጋዚ ጦር አምስት ወታደሮች ኤርትራ የሚገኘውን የአማራ ዴሞክራሲ ሀይል ንቅናቄን ተቀላቀሉ

መድረክ አገዛዙ በአባላቱ ላይ የፈፀመውን ግድያ አወገዘ

“ኢትዮጵያ ከመፈንቅለ መንግስት ነፃ አገር ነች ማለት ይከብደኛል አንድ ኮረኔል ታንኩን ይዞ ብቅ ሊል ይችላል” ዶር ዳኛቸው አሰፋ የቀድሞ የአአዩ መምህር

ደቡብ አፍሪካ እና ሱዳን በአልበሽር ጉዳይ ወደ ሙሉ ወታደራዊ ግጭት ሊገቡ እንደነበር ተጠቀሰ

የአልበሽር ነፍስ በ1400 የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች ተመነዘረች

በኢትዮጵያ የመብት ረገጣን በፍርድ ቤት ጭምር መግለጽ አልተቻለም

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት  በቀጥታ በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽና  በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-062115-062815

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *