Hiber radio የተባበሩት መንግስታት በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ማጣራት አድርጎ ለመንግስት ጥያቄ ማቅረቡ፣ ኢትዮጵያዊው በቨርጂኒያ ለኢሚግሬሽን ባለስልጣናት አልተባበርም ከማለት አልፎ አገሬ ከላካችሁኝ አውሮፕላኑ ላይ ጥቃት ይሰነዘራል ማለቱ ከባድ እስራት ሊያስከትልበት መሆኑ ፣ በአንጋፋው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ስም የተሰየመ ሕዝባዊ ስብሰባ በሚኒሶታና በሌሎችም ከተሞች ለመጥራት መታቀዱ፣ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ንግግር፣የሰሜን አሜሪካ 32ተኛ የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል መጠናቀቅ ፣በፕ/ት ኦባማ የኢትዮጵያ ጉዞ ላይ የቀረበ ተቃውሞና ሎሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሰኔ 28 ቀን 2007 ፕሮግራም

32ተኛው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ያባህል ፌስቲቫል መጠናቀቅ በተመለከተ ውይይት (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በዚህ አዳራሽ አንዳርጋቸው ጽጌ የዞን 9 ጦማሪያን ቢገኙ ምን ሊነግሩን ይችሉ ነበር …ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ዋና ፀሃፊ ጆን ኬሪ በፃፈው ደብዳቤ ላይ የሚያሳስበው ጉዳይ በእስር ቤት የሚያሳልፈው ጊዜ ሳይሆን የወደፊቱ ያገሩ ጉዳይ ነው። እሱ ተስፋ ያልቆረጠ …> ናይጀሪያዊቷ የሰሃራ ቲቪ ጋዜጠኛ አዲዎላ ባለፈው ሐሙስ ምሽት በዋሽንግተን ዲሲ ካደረገችው ንግግር የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…ከዚህ በኋላ ህዝብ ሰብስቦ ማውራት ላቆም ነው ። ጊዜው ተቀይሯል.. ትግል ለደካማ መንፈስ አይሆንም ።ትግል መውደቅን ይጠይቃል። ሲወድቁ ግን ለመነሳት መሞከርን ይጠይቃል። ስንወድቅ ልታዩን ትችላላችሁ ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ …>

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር በዋሽንግተን በኢሳት አምስተኛ ዓመት ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ ቀሪውን ያዳምጡት

አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ከነበረከት ጋር በስልጣን በነበሩበት ወቅት ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋና ሲሳይ አጌና የጋዜጣ ፈቃድ ስለጠየቁ አሸባሪዎች ናቸው በሚል ሪፖርት መጥቶ መወያየታቸውን ምስክርነት ሰጡ (የንግግራቸውን ክፍል ያዳምጡት)

የጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ቀን በሕዝባዊ ስብሰባ በሚኒሶታና በሌሎች አካባቢዎች ሊካሄድ እቅድ መያዝ (ልዩ ውይይት)

< …ፕ/ት ኦባማን ከጉዟቸው ማስቀረት አንችልም…ሔደው የሚስማሙት ግን የእኛ አልቃይዳ የእኛ አልሸባቦች ከሆኑት ወያኔዎች ጋር መሆኑን መግለጽ እንችላለን…> ጋዜጠኛና አክቲቪስት አበበ ገላው የፕ/ት ኦባማን የኢትዮጵያ ጉዞ ዕቅድ በተመለከተ ከተናገረው (ሙሉውን ያዳምጡት)

አክቲቪስትና ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ካደረገው ንግግር ትቂቱን አካተናል ሙሉውን ያዳ

ድህረ ፕ/ት መሃመድ ሙርሲ የተካሂደው የግብጾች አብዮት እና ያስከተለው ውጣውረድ ሲዳስስ

ግብጽ ከአምባገን መንግስት ወደ አክራሪ ሙስሊሞች እና በ ወታደራዊ እዝ ስር የወደቀችበት የሁለት ዓመቱ ፖለቲካዊ ጉዞ(ልዮ ዘገባ)

<…በኢትዮጵያ አረጋውያንን የሚጦር የለም ።ህ/ሰቡ ነው መንከባከብ ያለበት። የመጣሁት በአዋሳ በባለሀብት ለተገነባው የአረጋውያን መጦሪያ የውስጥ ቁሳቁስ ለማሟላት ወገኖቻችንን ለመጠየቅ ነው…> ሲ/ር ዘቢደር ዘውዴ የሜሪ ጆይ ዋና ዳይሬክተር በአሜሪካ ስለሚያደርጉት ቆይታ ከተናገሩት (ያዳምጡት)

ሌሎችም ቃለ መጠይቆች

ዜናዎቻችን

የተመድ አጣሪ ኮሚሽን በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እስራት  ዙሪያ  ለኢሕአዲግ መንግስት  ባለ 8 ገጽ  ጥሪ አቀረበ

አንዳርጋቸው  ጽጌ  የሞራል  ካሳ ሊስጣቸው  እና በአስቸኳይ ሊለቀቁ ይገባልየተመድ የሰብዓዊ መብት  አጣሪ ቡድን የውሳኔ ሃሳብ

ለአሜሪካ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ጥያቄዎችአልታዘዝምያለው ኢትዮጵያዊ ከባድ እስር ሊጠብቀው ነው

እኔን በጉልበት አውሮፕላን ላይ በመጫን ወደ አገሬ ለማባረር ከሞከራችሁ በአውሮፕላኑ ላይ ጥቃት ይሰነዘራልኢትዮጵያዊው ተከሳሽ

ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በሁዋይት ሐውስ ተቃውሞ በማድረግ የፕ/ ኦባማን አገር ቤት ጉዞ ተቃወሙ

የኢትዮጵያው  ዋሊያ ብሄራዊ የእግር ኳስ  ቡደን የከኔያ  ሃራምቤ ቡደንን በሜዳው ላይ   በማሸነፍ ድል በድል ሆኑ

ለሽንፈታችን  ዋንኛ ተጠያቂዎቹ እኛው  እራሳችን  ብቻ ነንየከኔያው አሰልጣኝ

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ የታላቅ ኣህቷን  ሪከርድ ለመስበር ተቃርባ እድል ራቃት

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችንና በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-070515-071215

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *