በሙስሊሙ ኮሚቴዎች ላይ በፍርድ ቤት የተሰጠውን የፖለቲካ ውሳኔ በመቃወም ጫና የመፍጠር እንቅስቃሴ ሊደረግ ነው

Ethiopian-Muslim-committee1

የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊዎች ላይ ትላንት የሰጠውን የጥፋተኝነት ውሳኔ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን የሌላ እምነት ተከታዮችም በወገኖቻቸው ላይ የተላለፈውንየጥፋተኝነት ውሳኔ በማህበራዊ ሚዲአና በልዩ ልዩ መገናኛዎች እንደማይቀበሉትና የፖለቲካ ውሳኔ መሆኑን እገለጹ ይገኛሉ። ድምጻችን ይሰማ ውሳኔውን ያወገዘ ሲሆን መንግስት ላይ ኣለም አቀፍ የተባበረ ጫና ለማድረግ መታቀዱን ይፋ አድርጓል።

ድምጻችን ይሰማ በዚህ መግለቻው ባለፉት ሶስት ዓመት በላይ በሙስሊሙ ሰላማዊ ጥአቄ ላይ ስርኣቱ እወሰደ ያለውን ግፍ እርምጃና ከጥአቄው ውጭ ሲያቀርባቸው የነበሩ ሀሰተና ክሶች አድገው ኮሚቴዎቹን በፈጠራ እስከ መክስና በሀሰት ክስ መነሳነት ራሱ ከሳሽ ራሱ ጥፋተና የሚባልበት ሂደት ተቀባይነት ስለሌለው በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ያለው ሕዝብ ተቃውሞ እንደሚቀጥልና ሰፊ ጫና ለመፍተር እንደሚንቀሳቀስ ገልጿል።

ትላንት የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ የወንጀል ችሎት በእነ አቡበክር አህመድ የክስ መዝገብ የአቃቤ ህግን እና የመከላከያ ምስክሮችን ቃል በንባብ አሰምቶ ማጠናቀቁን ተከትሎ ዛሬ በ18 ተከሳሾች ላይ ፍርድ ሰጥቷል። በዚህም መሰረት አቡበከር አህመድ፣ አህመዲን ጀበል፣ ያሲን ኑሩ፣ ካሚል ሸምሱ፣ በድሩ ሁሴን፣ ሼህ መከተ ሙሄ መኮንን፣ ሳቢር ይርጉ፣ መሀመድ አባተ፣ አህመድ ሙስጠፋ፣ አቡበከር አለሙ፣ ሙኒር ሁሴን፣ ሼህ ሰኢድ አሊ፣ ሙባረክ አደም፣ ካሊድ ኢብራሂም በተከሰሱባቸው በፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ አራት ላይ በተዘረዘሩት መቀስቀስ፣ ማነሳሳት እና ማሴር በሚሉ ወንጀሎች ጥፋተኛ ማለቱ አይዘነጋም። በዚሁ ውሳኔ ቀሪዎቹ ሙራድ ሽኩር፣ ኑሩ ቱርኪ፣ ሼህ ባህሩ ኡመር እና የሱፍ ሄታቸው በፀረ ሽብር ህጉ አንቀፅ ሰባት ላይ በተጠቀሰው በመሳተፍ ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል። ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለሀምሌ 27 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት ቀጠሮ ሰትቷል።

ተከሳሾቹ እና ዐቃቤ ህግ ከሀምሌ 10 ብለውም የቅጣት ማቅለያ እና ማክበጃ አስተያየታቸውን እንዲያቀርቡም ታዟል። ፍርድ ቤቱ ትላንት ጠዋት ከከሳሽና ከተከሳሽ በኩል በተካሄዱ ክርክሮች አምስት ጭብጦችን መመርመሩ ገልጿል። ከአምስቱ ጭብጦች መካከል መንግስት በእስልምና ሃይማኖት ጣልቃ ገብቷል አልገባም? የሃይማኖቱ ተከሳሾችን ከፋፍሏል አልከፋፈለም? እና የመጅሊሱ ምርጫ ከህገ መንግስቱ ጋር ተጋጭቷል? አልተጋጨም? የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው። ችሎቱ እነዚህን ጭብጦች ሲመረምር በተለያዩ ሃገራት ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ የሚራመዱ አሰራሮችን አይቷል። ከዚህ ሰፊ ሃተታ በኋላ መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አለመግባቱን፣ ተከታዮችን አለመከፋፈሉንና የመጅሊሱ ምርጫ ከህገ መንግስቱ ጋር ሳይቃረን በሃይማኖታዊ ስርአት መካሄዱን ከምስክሮችና ከማስረጃ ቃል በማገናዘብ አረጋግጫለሁ ማለቱን ተከትሎ ነው ከሰዓት በኋላ የጥፋተኝነት ውሳኔውን ሰጥቷል።

የዛሬው የድምጻችን መግለጫ ውሳኔውን ተከትሎ ቀታዩን የሙስሊሙን ማህበረሰብ ትግል የሚአሳይ በመሆኑ ተከትሎ ቀርቧል።

ወቅታዊ መግለጫ ከድምጻችን ይሰማ

ረቡእ ሰኔ 19/2005

ከሐምሌ 2003 የአሕባሽ ይፋዊ የግዳጅ ጠመቃ መጀመር በኋላ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሃይማኖቱና ህገ መንግስታዊ መብቱ ላይ የተቃጣበትን አደጋ ለመመከትና ለማስቆም መንግስትን ሲማጸን ቆይቶ በታህሳስ ወር የአወሊያ ተማሪዎች የመንግስት ጸረ እስልምና እንቅስቃሴ ት/ቤታቸው ድረስ መምጣቱ አሳስቧቸው በጀመሩት እንቅስቃሴ ትግሉ አሀዱ ተባለ፡፡ የተማሪዎቹ የአካዳሚክ ነጻነት ተጥሶ መምህራኖቻቸው መባረራቸውና የመስጂዱ ኢማም ከቦታቸው በመንግስታዊው መጅሊስ መነሳታቸው የተማሪዎቹን ብቻ ሳይሆን የህብረተሰቡንም ስሜት የፈነቀለ እርምጃ ነበር፡፡ ህብረተሰቡ በአወሊያ ተማሪዎች በተደረገለት ጥሪ በብዛት በመገኘት እና ጉዳዩን ከመንግስት ጋር ተነጋግሮ በሰላም ለመፍታት ይረዳል የተባለ ሕዝባዊ ኮሚቴ ተመርጦ ሕጋዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ጀመረ፡፡

 

የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የወራት ያላሰለሰ ዲፕሎማሲያዊና ሰላማዊ ጥረት በመንግስት አሻፈረኝ ባይነት ሲመክንና ሁኔታዎችን መንግስት በራሱ እኔ አውቅልሀለው ባይነት ለማስኬድ በመወሰንና የተመረጡትን የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የሽብር ትእይንት በመፍጠር በእስር ላይ ሲያውላቸው፤ ለሰባት ወራት ያክል በኮሚቴው አማካኝነት ሰላማዊ ድምጹን ሲያሰማ የቆየው ሙስሊም ህብረተሰብ ወዳልተገባና ሰላማዊ ወደልሆነ አቅጣጫ ይሄዳል ብለው መንግስትና በመንግስት ዙሪያ ያሉ ሁሉ ጠብቀው እና ተመኝተው ነበር፡፡ ሆኖም ያ ሳይሳካ ‹‹ታጋይ ያልፋል፤ ትግል አያልፍም›› በሚል መርህ ቀድሞ በነበረው ሰላማዊ ዲሲፕሊን ትግሉን ቀጥሏል፡፡ ይህም ማለት ኮሚቴዎቻን ከታሰሩ በኋላ ሁለቱን አገር አቀፍ የኢድ ትእይንቶች ጨምሮ በርካታ ህዝባዊ ትእይንተ ተቃውሞዎች እና ሌሎች ተጓዳኝ የትግል ስልቶች ለአንድ አመት ያህል ውጤታማ በሆነ መልኩ ተከናውነው ዛሬ ላይ ደርሰናል፡፡

 

ይህ ታሪካዊ ሀላፊነት የተጣለበት ድምጻችን ይሰማ መጪዎቹን ጊዜያት ይህን ሕዝባዊ መነሳሳትና የህብረተሰቡን ለዲን መከታ ሆኖ የመዝለቅ ፍላጎት ከግምት ውስጥ በማስገባት ላለፉት ጥቂት ወራት በትግል መስመራችን ላይ መሰረታዊ ለውጥና ውጤት ሊያመጡ የሚችሉ የማሻሻያ እቅዶችና እቅዶቹን ለማስፈጸም የሚረዱ የሰው ሀይል ማጠናከርና ቅንጅት ለመፍጠር የሚረዱ እንቅስቃሴዎች ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ይህን እንቅስቃሴ ማድረግ ሙስሊም መሆን ወንጀል እስከመምሰል በደረሰበት የአገራችን ተጨባጭ እጅግ አስቸጋሪና ፈታኝ ቢሆንም ይሄንን ሁሉ ተቋቁሞ በጥንቃቄ ማከናወኑ የአላህ ጥበቃ ያልተለየው ሂደት ላይ መሆናችንን አመላካች ነው፡፡ በዚህም መሰረት ትግሉ እንቅስቃሴውን በውጤታማነት እና አሳታፊነት ለማስቀጠል የሚረዳ እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ለመግባት ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

ይህ እቅድ ከመዘጋጀቱ በፊት የ‹‹ድምጻችን ይሰማ›› የእስከአሁኑ ጉዞ አመርቂ በሆነ መልኩ ግምገማ ተካሄዶበታል፡፡ ይህም ያስፈለገበትምክንያት የእንቅስቃሴያችንን ጠንካራና ደካማ ጎኖች ለመለየት እና ድክመት ያለበትን ለመለየት እና ክፍተቱን በአግባቡ ለመረዳት ጠንካራ የተባሉትን ጎኖች ደግሞ አጎልብቶ ለማስቀጠል ሲባል ነው፡፡ በዚህ ግምገማ ሂደት የሙስሊሙ ህብረተሰብ ሚና ከፍተኛ የነበረ ሲሆን በተለያዩ ጊዜያት ባዘጋጀናቸው የአስተያየት መሰብሰቢያ መድረኮች በዋነኝነትም በገጻችን የውስጥ መልእክት (ኢንቦክስ) አማካኝነት በርካታ ጠቃሚ ግብአቶች ማግኘት የተቻለ ሲሆን፤ እነዚህ ግብአቶች ለእቅዱ ወሳኙን ሚና አበርክተዋል፡፡ ይህንንም ማድረግ ያስፈለገው በሕዝባዊው እንቅስቃሴ ውስጥ የህብረተሰቡ ሀሳብና ትችት ጉልህ ድርሻ ያለው መሆኑን በማመን ነው፡፡ በቀዳሚው የትግሉ ሂደት ግምገማ ዙሪያና በአዲሱ ፕላን ላይ የምሁራንም ሚና ከፍተኛ እንደ ነበር መካድ አይቻልም፡፡ በሃይማኖታዊ እውቀታቸው እንዲሁም በአካዳሚክ እውቀታቸው አንቱ የተሰኙ ምሁራንን፤ እንዲሁም በዲን እውቀታቸው ፊቅህ ላይና ቀዳሚውንና የአሁኑን የእስልምና ታሪክ ያጠኑ ምሁራን በእቅዱ ላይ ጉልህ አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

በዚህም መሰረት አጠቃላይ የተሃድሶና ሽግሽግ ስራዎች በዋነኝነትም በግንዛቤ፣ መዋቅርና በትግበራ መንገዶች ላይ የተከናወኑ ሲሆን ቀጣዩ ጉዞም ስልታዊ መንገድን በተሻለ መልኩ የሚከተልና ጊዜያዊ ችግሮች ላይ ሙሉ አትኩሮቱን ከማድረግ ይልቅ የችግሮቹ ቁልፍ እና መሰረቶቹን ለማስተካከል ጥረት ያደርጋል፡፡ በአመራርና አሳታፊነት ደረጃም ከስር ጀምሮ ያለውን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያቀፈና በመሬት ላይ ያለውን የመረጃና ክንውን ተስፋፊነቱ የተሻለና ሁሉንም ህብረተሰብ ያዳረሰ ይሆናል፡፡ በዚህ ረገድ የህብረተሰቡም በራሱ ተነሳሽነት ስራዎች ላይ ለመሳተፍ የሚያሳየው ዝግጁነት ወሳኝ እንደሚሆን ግልጽ ነው፡፡ ጥያቄዎቻችን ይመለሱ ዘንድ መንግስት ላይ የሚፈጥረው ጫና እና ተጽእኖም አሁን ካለው በተሻለ እና በተቀናጀ መልኩ እንዲያይል በማድረግ የህብረተሰቡን ሀይል ማጠናከርም መሰረታዊ አላማው ይሆናል፡፡ መጪው ጊዜ የረመዳን ወቅት በመሆኑና ሙስሊሙ ህብረተሰብ ለመንፈሳዊ ተግባሮች የበለጠ የሚሳብበት ወቅት በመሆኑ ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀምም ሕጋዊ ጥያቄዎቻችን ተገቢውን አዎንታዊ ምላሽ እንዲያገኙ በከፍተኛ ሁኔታ የምንንቀሳቀስበት ነው፡፡ መጪውን ረመዳን ውጤታማ ለማድረግ የሚረዳ እቅድም የተዘጋጀ ሲሆን ይሄን ለማሰፈጸምም ሁሉም ሙስሊም በራሱ ተነሳሽነት ክንውኖች ላይ በመሳተፍ ሀላፊነቱን እንዲወጣ እንጠይቃለን፡፡

 

በመረጃ ተደራሽነት መስክም መረጃን ለአብዛኛው ሙስሊም ህብረተሰብ ለማድረስ የሚረዱ መንገዶችን ለመቀየስ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ በተለይም ከዋነኛው የመረጃ መለዋወኛ የፌስቡክ ድረ ገጽ ውጪ ያሉ የመረጃና ኮሙኒኬሽን መንገዶችን እንደአማራጭነት ለመጠቀምና የህብረተሰቡ መረጃ ምንጮች አቅርቦት እንዲሰፋ የታቀደ ሲሆን በዚህመ መሰረት በፌስ ቡክ ውስጥ አማራጭ መንገዶችን ለመፍጠር በተደረገ ጥረት የድምጻችን ይሰማ አንግሊዝኛ፣ አረብኛ፣ ኦሮምኛ እና ትግርኛ ገጾች ተከፍተው ከፊልና ሙሉ አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲገኙ ዋናው የአማርኛ ገጽን ድንገት ሊከሰት ከሚችል የኢንተርኔት ጥቃት ለመከላከልና ቀድሞ ለመዘጋጀት ተጠባባቂ ድምጻችን ይሰማ ቁጥር ሁለት ገጽ በዛሬው እለት ተከፍቶ ግልጋሎት መስጠት ጀምሯል፡፡ ይሄንን ገጽ ሁሉም ላይክ እንዲያደርገውም መልእክታችን ነው፡፡ የአዲሱ ገጽ ሊንክም ይኸው ነው፡፡

ከፌስቡክ ውጪ ትዊተር እና ጎግል ፕላስ የተባሉት አማራጭ ማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ከፌስቡክ ገጻችን ጋር የሚመሳሰል አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን፡፡ አሁን ደግሞ በያሆ ግሩፕ፣ በኢሜይል እና በፌስቡክ የውስጥ መልእክት (inbox) አማካኝነት በአንድ ጊዜ አስከ ሃምሳ ሺህ ሙስሊሞችን ተደራሽ ለማድረግና የሚወጡ መረጃዎችን ለማሰራጨት ቅድመ ዝግጅት ላይ እንገኛለን፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በደምጻችን ይሰማ የተዘጋጀ ድረ ገጽ (website) በበርካታ መረጃዎች በመሞላት ግንባታውን አጠናቅቆ ለስራ መዘጋጀቱን ስናበስራችሁ በደስታ ነው፡፡

ከአገር ውጪ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተም ጥያቄዎቻችን ምላሽ እንዲያገኙ መንግስት ላይ ጫና ለመፍጠር የሚረዱ ክንውኖች በቅንጅት የሚሰሩ ሲሆን የሙስሊሙን የዳያስፖራ ማህበረሰብ እምቅ ሀይልና ጫና የመፍጠር አቅም ከግንዛቤ በመክተት መንግስት ላይ ትርጉም ያለው አለም አቀፍ ጫና ለመፍጠር ተግባራዊ እንቅስቃሴ ይደረጋል፡፡ በተጨማሪም መንግስት በአገር ውስጥ አለም አቀፍ ህግጋትን በመተላለፍ በሙስሊሙ ላይ እየፈጸማቸው ያሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ለማጋለጥና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማቅረብ ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የሚከናወኑ ሰፊ ተግባራት ይኖራሉ፡፡ ከሚደረገው ትግል ጎን ለጎንም ሙስሊሙ ህብረተሰብ ማግኘት የሚፈልገውን ዲሞክራሲያዊና ሕገ መንግስታዊ መብቶች ለማስከበር ለሚደረጉ ማናቸውም የእርቅና የሰላም መፍትሄዎች ሁሉ ሁሌም ዝግጁ እንደሆንን ለማሳወቅ እየወደድን በቀጣይ በምናደርጋቸው እንቅስቃሴዎችም አቅም በፈቀደ መጠን የሃይማኖትም ሆነ አካዳሚክ ምሁራንን በማሳተፍና ሃሳባቸውን ለትግሉ ግብአት አድርጎ በመጠቀም ጉዞአችንን እንቀጥላለን፡፡ ይላል

 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችንና በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *