Hiber Radio ከጦማሪያኑ ሶስቱ ተፈቱ ፣ የቀሩትን ጨምሮ የሌሎች ፖለቲካ እስረኞች መጨረሻ አልታወቀም

zone-9ners2

 

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ አስማማው ሃይለጊዮርጊስና ጦማሪ ዘላለም ክብረት በአንድ መዝገብ ከተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ፍርድ ቤት ቀጠሮዋቸው ሳይደርስ ፋይላቸው ተዘግቶ ከእስር ቤት ወጥተው ከቤተሰብ መቀላቀላቸው ከአዲስ አበባ የወጡ መረጃዎች ገለጹ።

ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ ከእስር ቤት በሁዋላ ከቤተሰቦቹ ጋር ቦሌ የሚገኘው መድሃኒዓለም ቤተ ክርስቲያን ተሳልሞ መመለሱን ቤተሰቦቹ የለጠፉት ፎቶ ግራፍን ይፋ ሆኗል።

ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁን፣ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ፣ናትናኤል ፈለቀ፣አቤል ዋበላ እና በፍቃዱ ሀይሉ በእስር ላይ ናቸው። የቀሪዎቹ እስረኞች ዕጣ ምን እንደሆነ አልታወቀም።

ስለሚያገባን እንጦምራለን በሚል መርህ በመጻፋቸው ብቻ ለእስርና ለፈጠራ ክስ የተዳረጉት ጦማሪያን ጉዳይ ሰፊ ኣለም አቀፍ ተቃውሞ ያስከተለ ሲሆን በእነ ሶሊያና ሽመልስ ክስ ሳቢያ ለፊታችን ሐምሌ 13 ለብይን መቀጠራቸው ይታወሳል።

ባለፈው ሰኔ 8/2007 ቀጠሮ አንደኛዋን ተከሳሽ ሲሊአና ሽመልስን ይመለከታል የተባለው <ሲ.ዲ >> በግልጽ ችሎት ይታያል ተብሎ ሲጠበቅ ዳኞች ያለ አንዳች ማብራሪያ በግልጽ ችሎት አይታይም በማስረጃነት ተቀብለነዋል ማለታቸው ይታወሳል።

የጦማሪያኑ መፈታት ከፕ/ት ኦባማ ጉዞ ጋር ይያያዝ ዌኢም በሌላ ምክንያት እስካሁን የሚታወቅ ባይኖርም አንዳንዶች የኦባማ ጉዞን እቅድ በምክንያትነት ያነሳሉ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *