መንግስት ጦርነት እንደነበር በይፋ አመነ

zemene-Kassie02

አርበኞች ግንቦት ሰባት በስልጣን ላኢ ባለው አገዛዝ ላይ በሁለት የተለያዩ ቦታዎች ጥቃት ከፍቶ ለቀናት የዘለቀ ጦርነት መግጠሙን ከገለጸ ማግስት ጀምሮ ጦርነት የለም ሲሉ የነበሩ የአገዛዙ መገናኛ ብዙሃንና ባለስልጣናት በዛሬው ዕለት << 30 የኤርትራ ተላላኪዎች ሰርገው ለመግባት ሲሞክሩ ተደመሰሱ> በሚል በድፍኑ ጦርነት መኖሩን አምነዋል።ጦርነቱ መቼና የት ቦታ ተደረገ የሚለውን ያልገለጸ ሲሆን ሁኔታውን <<ጦርነት>> እንደማይባል እና ሰሞኑን በሚል በጥቅሉ ለማለፍ ይሞክራል።

ከሳምንት በፊት የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ታጋይ ዘመነ ካሴ ለኢሳት እንደገለጸው ሰኔ 25 2007 ዓ.ም የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ሰራዊት በትግራይ ክልል ቀፍታ መሲል፣ ሆርጃሞ እና ማይሰገል በሚባሉ ቦታዎች ከሰፈረው የ ሕወሓት 24 ኛ ክፍለ ጦር፣ ፌደራል ፖሊስና ልዩ ኃይል ጦር ጋር ባደረገው ለአራት ሰዓታት የዘለቀ ከባድ ጦርት ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ገልጿል። ጦርነቱን ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት አርበኞች ግንቦት 7 ጦርነት አውጇል በሚል ከሁመራ- ዳንሻ፣ ከሁመራ- ሽሬ እና እንዲሁም በተጨማሪ ከሁመራ- ጎንደር የሚገኙት አውራ ጎዳናዎች ተዘግተው እንቅስቃሴ መገደቡ ተጠቅሷል።

ጦርነቱ መቀጠሉን የወጣው ዘገባ አስቀድሞ እንደገለጸው  አርበኞች ግንቦት 7 በሁመራና በወልቃይት ጠገዴ እንዲሁም በአርጃሞ አካባቢ ሶስት ስፍርዋዎች ሲያጠቃ በተጨማሪ በኦጋዴን (የኦጋዴን ነጻ አዉጭ ) በኬንያ በተለይም ሞያሌ አካባቢ ኦነግ (የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ) በተጨማሪ በቡሬና በካባቢዉ ትግራይ ትህዴን ( የትግራይህ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ) በአፋር የአፋር ህዝብ ነጻነት ግንባር ጉሬላ በተባለዉ የዉጊያ ስልት ጦርነት መተንኮሳቸዉ ተመልክቷል።

ዛሬ አርብ ሐምሌ 3 ቀን 2007 የወጣው ከአገዛዙ ጧቢያዎች አንዱ የሆነው ራዲዮ ፋና በዘገባው ከኤርትራ ጋር በሚዋሰን ምእራብ ትግራይ ድንበር አካባቢ ሰርጎ ለመግባት የሞከሩ ከ30 የማይልቁ የሻዕቢያ ተላላኪዎች መደምሰሳቸውን የፌደራል ፖሊስ ገለፀ ብሏል። ይሄው ዘገባ አያይዞም <<ከኤርትራ ጋር በሚዋሰን ምእራብ ትግራይ ድንበር አካባቢ ሰርጎ ለመግባት የሞከሩ ከ30 የማይልቁ የሻዕቢያ ተላላኪዎች መደምሰሳቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄነራል አሰፋ አብዩ ተናገሩ። በሻዕቢያ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ትንኮሳ ለመፈጸም ከሞከሩት ጸረ ሰላም ሃይሎች መካከል አብዛኞቹ ሲደመሰሱ ጥቂቶቹ በቁጥጥር ስር ውለዋል።>> ብሏል።

ጠ/ሚንስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ማክሰኞ ፓርላማ ላይ ቀርበው በግልጽ ጦርነት አለ ላለማለት ኤርትራ መንግስት በኢትዮጵአና በአካባቢው አገሮችን ለማተራመስ እየሞከረ ነው ከድርጊቱ ካልተቆተበ ሕዝቡን አማክረን ጦርነት እንገጥማለን የሚል ሀሳብ አንጸባርቀዋል።

የአገዛዙ ባለስልጣናትና ሚዲያዎቻቸው በግልጽ አርበኞች ግንቦት ሰባት ጦርነት ከፈተ ብለው ከመናገር የተቆጠቡት ሕዝቡ ውስጥ ሊመጣ የሚችለውን ከፍተና መነቃቃት በመፍራት ጥርጣሬ ለመፍጠርና ጉዳዩ ብዙም ትኩረት እንዳአገኝ ለማድረግ አደረጉት ጥረት አለመሳካት ጦርነት መኖሩን በተዘዋዋሪ እስከማመን መሄዳቸውን አረጋግጣል ሚሉ ወገኖች አሉ።

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ሕዝቡ ከጎኑ እንዲሰለፍ ጥሪ ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን የግንባሩ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው ጦርነቱ በዌአኔና በሳብአ መካከል ሳይሆን ጦርነቱ በሕዝብ ልጆችና ሕዝብና አገር እያጠፉ ያሉት የፖለቲካ ስልታጣኑን ከያዙት ጋር እንጂ ሰራዊቱም፣ፖሊሱም ሆነ ሕዝቡ ከታጋዮቹ ጎን እንደሚሰለፉ ምንም ጥርጥር እንደሌላቸው መግለጻቸው አይዘነጋም።

ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በዚህ ንግግራቸው <<..”…ለኢትዮጵያ ህዝብ ግልጽ ሊሆንለት የሚገባው ይሄ ጦርነት ከሻቢያ ጋር አይደለም….ይሄ ጦርነት ስለሻቢያ አይደለም…ይሄ ጦርነት የኤርትራና የኤትዮጵያ አይደለም!! ይሄ ጦርነት በዋናነት ወያኔ ስልጣን ላይ ለመቆየት የኢትዮጵያን ዲሞክራሳያዊ ኃይሎች ለመጨፍለቅ የሚያደርገው እንቅስቃሴ ነው…የኢትዮጵያ ህዝብ ይሄንን ይደግፈዋል ብየ ቅንጣትም አልጠራጠርም….የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ወያኔ እንደዚህ አይነት እብደት ውስጥ ቢገባ እንደበፊቱ እዚህ ውስጥ ይገባል ብየ አላስብም…!!!” ማለታቸው አይዘነጋም።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *