Hiber radio : የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ኤርትራ ትግሉን በአካል መቀላቀል ሰፊ መነቃቃት መፍጠሩና የአገዛዙ ደጋፊዎች ድንጋጤ ፣ አንድ ወታደር ሶስት ኮሌኔሎችን ገድሎ በርካቶችን አቁስሎ ራሱን ማጥፋቱ ፣ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሁለት መኪናዎች ውስጥ የተደበቁ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋል፣መድረክ ፕ/ት ኦባማ በጉብኝታቸው ወቅት እንዲያናግሩት ጥያቄ ማቅረቡ፣የአቶ አንዳርጋቸው ፍርድ ቤት መቅረብ አጠራጣሪነት፣ካናዳ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ዜጋዋን ችላ ማለቷ ማስወቀሱ፣ ገንዘቤ ዲባባ የእህቷን ሪኮርድ ለመስበር ፍላጎቷን መግለጿ፣የሁበር የ7.3 ሚሊዮን ዶላር መቀጣትና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

habtamu11

የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 12 ቀን 2007 ፕሮግራም

 <…የዶ/ር ብርሃኑ ኤርትራ መግባት አርበኞች ግንቦት ሰባት ጦርነት ከጀመረበት በላይ በለውጥ ደጋፊው ሐይል ትልቅ መነቃቃትና ድጋፍ የፈጠረ ነው። በስርዓቱ ደጋፊዎችና በሌሎች ደግሞ ተቃውሞ ሲስተናገድበት ተስተውሏል…እርምጃው የኢትዮጵያን ቀጣይ ፖለቲካ አመላካች ነው። በሃምሳዎቹ ዕድሜ የሚገኙትና በቅርቡ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ያገኙት ዶ/ር ብርሃኑ የሳቸው ወደ በረሃ መግባት በሰራዊቱ፣በራሱ በገዢው ፓርቲም ውስጥም ትልቅ ልዩነት መፍጠሩ አይቀርም።ይልቅ ማሰብ የሚያስፈልገው ለውጡን ተከትሎ ሊመጣ የሚችለውን…>

ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ለህብር ሬዲዮ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ በረሃ መውረድ በትግሉ ላይ የሚያመጣውን ለውጥ በተመለከተ ተጠይቆ ከሰጠን ሰፋ ያለ ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ጥሬ ስጋ መብላትን ያመጣው አባቶቻችን ጣላትን ሲዋጉ እሳት አንድደው በመመገብ በቀላሉ ጠላት ያሉበትን እአወቀ ጥቃት ሲሰነዝር ለመሸሽ …> የጥሬ ስጋ አመጋገብ ባህላችን እና ኣለም አቀፍ የዘገባ ትኩረት ማግኘቱ( ልዩ ጥንቅር)

<…ከዩኒቨርስቲው ውስጥ ያባረሩኝ ያው ፖለቲካ ነው ለስሙ የጡረታ ዕድሜ ደርሷል ይላሉ እኔን በሀይለስላሴ ጊዜ ያስተማሩኝ ህንዶች ሳይቀሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እአስተማሩ ነው…ፕ/ት ኦባማ ከመጡ አይቀር መድረክ ለማነጋገር ያንድ ወገን የገዢውን ፓርቲ ብቻ ሰምተው እንዳይሄዱ እድል እንዲሰጠን ጠይቀናል።የኦባማ መጥቶ መሄድ ግን…>

ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ስለተባረሩበት ውሳኔ፣በአገር ቤት ስላለው የተቃውሞ ፖለቲካና የኦባማን ጉዞ አስመልክቶ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የዶ/ ብርሃኑ ነጋ ኤርትራ ትግሉን በአካል ለመቀላቀል መሔድ በማህበራዊ ሚዲያው ሰፊ መነቃቃትን ፈጠረ

የአገዛዙ ደጋፊዎች ድንጋጤ ተስተውሏል

አንድ ወታደር ሶስት ኮሌኔሎችን ገድሎ በርካቶችን ካቆሰለ በኋላ ራሱን ማጥፋቱ ተገለፀ

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በሁለት መኪናዎች ውስጥ የተደበቁ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አሽከረካሪዎቹ እየታደኑ ናቸው ተብሏል

 አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ለምስክርነት /ቤት እንዲቀርቡ የሰጠው ውሳኔ ተግባራዊነት አጠራጣሪ ሆኗል

መድረክ ፕሬዝዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ወቅት እንዲያነጋግሩት ጥያቄ ማቅረቡን / መረራ ጉዲና ገለፁ

የአሜሪካ ኤምባሲ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ይዘዋል

ሁበር በካሊፎርኒያ 7.3 ሚሊዮን ዶላር ቅጣትና በአንድ ወር ውስጥ አገልግሎቱን እንዲያቋርጥ ዳኛ ውሳኔ ሰጠ

ውሳኔውን በመቃወም ኩባንያው ይግባኝ የማለት እቅድ እንዳለው ገለፀ

የካናዳ መንግስት በኢዮጵያ ውስጥ የታሰረ ዘጋዋን ባለመወሰዷ ከፈተኛ ትችት ገጠማት

ኬንያ ኢትዮጵያዊያን መኮነኖችንን ማሰሯን እና ለኪሳራ እንደዳረጓት ባለሰላጣናቱዋ ገለጹ

የእስራኤል መንግስት ኢትዮጵያዊው አባ ወራን ከቤተሰቦቻቸው ነጥሎ ለያባርራቸው ወሰነ

አምባሳደር ግርማ ብሩ መገንጠልን ከሚቃወሙ ወገኖች የከረረ ጥያቄ ገጠማቸው

እረ ሰለኮንደሚኒየም ከማወራት በፊት ኣንድ አድረጉን ፣አትገነጣጥሉንአንድ ተቃዋሚ ለአቶ ግርማ ያቀረቡት ምክር

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ 23 አመታት ያልተደፈረ የአለም ክብረወስንን ሰበረች

የታላቅ እህቷን ረኮርድም ለመሰበር ቋምጣለች

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችንና በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-071915-072615

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *