ሕዝቡ የወያኔ ባለስልጣናት ካቀዱለት ጥፋት እራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ ቀርቧል!

የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ ኤርትራን ጉዞ ተከትሎ በስልጣን ላይ ያለው የወያኔ(ህወሃት) ኢህአዴግ አገዛዝ የተለመደ ዘርን ከዘር የማጋጨት ሴራውን ቀጥሎበታል። የደህነት መስሪያ ቤቱም በተለይ ሰላማዊ ሰዎችን ጭምር ዒላማ ያደረገ የሽብር ጥቃት በተለይ አሁን የሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴ ያለባቸውን አካባቢዎችና የመሀል አገርን ጨምሮ ተግባራዊ ለማድረግ ማሰባቸው ሾልኮ እየወጣ ነው። ከዚህ ቀደም ዊክሊክስ እንዳጋለጠው በሴፕቴምበር 2006 በአዲስ አበባ ካራ ቆሬ ሶስት የኦሮሞ ብሄራዊ ኮንግረስ አባላትን በአንድ ቤት አስገብተው በፈንጂ ገለው የኦነግ አባላት ለሽብር ተዘጋጅተው እዚያው አፈነዱ ማለታቸውን አጋልጧል። የሽብር ድርጊቱ አቀነባባሪዎች የኢትዮጵያው አገዛዝ የደህንነት መ/ቤት መሆኑ በሪፖርቱ ግልጽ ነው። ዛሬም ለማንኛውም ጥፋት ተጠያቂው ይህ የግፍ ስርዓት በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ፣የጠረጠረውን መረጃ በቻለው መንገድ ሁሉ እንዲያጋልጥ ጥሪ እየቀረበ ነው። ለሁሉም ለዘረኛ ቅስቀሳቸውም ሆነ ለሽብር ሴራቸው ለሚደርሰው ሁሉ ተጠያቂዎቹ እነሱ ናቸው። ለዛሬው የብርሃኑ ተዘራን ወገኔ ጋብዘናችሁዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *