Hiber radio ፕ/ት ባራክ ኦባማ አዲስ አበባ ሲገቡ ቀስተ ደመና መታየቱ ነዋሪውን አነጋገረ፣ ሕዝቡ ፕሬዝዳንቱ ቶሎ በሄዱልን የሚል ምሬት ውስጥ መግባቱ ተገለጸ፣ኦባማ አዲስ አበባ ገብተውም አገዛዙ በተቃዋሚዎች ላይ የሚያደርገውን ጫና መቀጠሉ፣አርበኞች ግንቦት ሰባት የህዝብ ንብረት የማውደም ዓላማ የለኝም ማለቱ፣የዶ/ር አክሎግ ቢራራ በኦባማ አማካሪ ሲሳን ራይስ መግለጫ ላይ የተሰጠ ቃለ መጠይቅ፣የሳንባ ካንሰር፣የኦባማ ጉዞ ዳሰሳ፣ሁበር የፈጠረው ጫናና የታክሲ አሽከርካሪዎች ስጋት እና ሎሎችም

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ
ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ ሐምሌ 19 ቀን 2007 ፕሮግራም

<…በኢትዮጵያው አገዛዝ የይስሙላ ምርጫ ላይ የፕሬዝዳንት ኦባማ አማካሪና የህወሃት ወዳጅ ሲዛን ራይስ የመቶ በመቶ ምርጫው ዲሞክራሲያዊ ነው ማለታቸውና እሳቸው እንደሳቁት እኔም ስቄያለሁ የሳቸው ሳቅና የኔ ሳቅ የተለያየ ነው። የመቶ በመቶ ምርጫው እንዳሉት ሳይሆን በርካታ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ፍሪደም ሀውስን ጨምሮ ምርጫው የድሮ የሶቪየትን ምርጫ ነው ፣የሰሜን ኮሪያን ምርጫ ነው የሚያስታውሰው ብለዋል። አምባሳደር ሱሳን ራይስ የጎዱት የኢትዮጵያን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለአሜሪካ በኢትዮጵያ ሕዝብ በኩል የሚኖረውን አክብሮትም ጎድተውታል።ምክንያቱም …>

 / አክሎግ ቢራራ በፕ/ ኦባማ የኢትዮጵአ ጉዞና የፕሬዝዳንቱ የብሔራዊ ጸጥታ አማካሪ የሆኑት ሱሳን ራይስ በጉብኝቱ ላይ የሰጡትን መግለጫ በተመለከተ ተጠይቀው ከሰጡን ሰፋ ያለ ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

 <…በአዲስ አበባ አራት አይነት ዩኒፎርም የለበሱ ፖሊሶች ሕዝቡን በከፍተኛ ሁኔታ እያስጨነቁት ነው ነገ(ሰኞ) ሕዝቡ በአብዛኛው በዚህ ተማሮ፣የታክሲው ወረፋ ስራ የሚሄድ አይመስለኝም/ ኦባማ እዚህም እያሉ ሕጋዊው የመኢአድ አመራሮች እየታደኑ እየታሰሩ ነው ግማሾቹ የደረሱበት አልታወቀም። ፕሬዝዳንቱም ተቃዋሚዎችን የሚያናግሩ አይመስለኝም…> አቶ አበበ ውቤ የህጋዊው መኢአድ የጭርቆስ ቀጠና ሀላፊ በእስር ስጋት ውስጥ ሆነው ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

የፕሬዝዳንት ኦባማ የኬኒያና የኢትዮጵያ ጉዞን ተከትሎ የተከሰቱ ተቃውሞና ድጋፎች ፣አስገራሚ ክስተቶች ሲዳሰሱ

አሜሪካ ጋር እንደምነወዳጅ ሁሉ ከአሜሪካ ጋር ልዮነቶች እንዳሉን ማወቅ አለብንየኬነያው / ኡሁሩ ኬኔያታ ( ልዩ ጥንቅር)

የሳምባ ካንሰርና ሐኪም ለሞቱ ቀን የቆረጠለት ግለሰብ በስራው ቦታ ባልደረቦቹን ሊሰናበት የሄደበት አስደንጋጭ ሁኔታና የጓደኞቹ ምላሽ( ልዩ ዘገባ)

 <… የቬጋስ አሽከርካሪዎች የሁበርን እየመጣሁ ነው ማለት ተከትሎ የመጣ ስጋት፣ የታክሲ ኩባንያዎቹ ተጨማሪ ታክሲ የማግኘት ሩጫና ስራው ላይ የሚያመጣው ተጽዕኖ …> (ውይይት ከታክሲ አሽከርካሪዎች ጋር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

/ ባራክ ኦባማ አዲስ አበባ ሲገቡ ቀስተ ደመና መታየቱ ነዋሪውን አነጋገረ

ሕዝቡ ፕ/ት ኦባማ ከኢትዮጵያ ቶሎ የሄደው ከዚህ አስጨናቂ ሁኔታ ውስጥ በተገላገልን የሚል ምሬት ውስጥ መግባቱ ተገለጸ

ባራክ ኦባማ ይሄ ኢትዮጵያ እንጂ አሜሪካ ወይም ኬኒያ አይደለምየኦባማን ወደ / መምጣት ከተቃወሙ ነዋሪዋች መካከል ያስማው ተቃውሞ

የግንቦት 7አርበኞች ግንባር ንቅናቄ የሕዝብ ንብረት የማውደም ዓላማ የለኝም አለ

በኢትዮኤርትራ ድንበር ላይ መጠነ ሰፊ ጦርነት ሊቀጣጠል እንደሚችል አንድ ምሁር አስጠነቁቁ

ኦባማ ኢትዮጵያው ገብተው የተቃዋሚ አመራሮችና አባላት በደህነቶች እየታፈኑ መወሰድ መቀጠሉን አንድ የተቃዋሚ አመራር ገለጹ

ታዋቂዋ አሜርካዊት የሲኒማ ተዋንያት እና ዳይሬክተር አንጄሊና ጆሊ ከኢትዮጵያ የወሰደቻት ልጇን ልታጣት ነው

ቴኤ የኡበርና ሊፍትን ወደ ቬጋስ መምጣት በመቃወም ከ320 በላይ ታክሲ ፈቀደ

ገደብ የነበረባቸውን ታክሲዎች ገደቡን አነሳላቸው

ኡበር በኒዮርክ የገጠመውን ጠንካራ ተቃውሞ በድል መወጣቱ ተዘገበ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-072615-080215

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *