ለሕወሃት ሊቀመንበርነት የአባይ ወልዱና የዶ/ር ደብረጽዮን ቡድን የስልጣን ሽኩቻ ላይ ናቸው ፣መቀሌ ላይ የፌዴራል ፖሊስና የክልሉ ልዩ ሀይል ከፍተኛ ጥበቃ እያካሄደ ነው

TPLF_leaders_05

 

 

የሕወሃት መሪዎች የመቀሌና የአዲስ አበባ በሚል ተባድነው የስልጣን ሽኩቻ ላይ የቆዩ ሲሆን ሲጠበቅ የነበረው የሕወሃት ጉባዔ የዚሁ ማሳረጊአ እንደሚሆን የሚጠበቅ ሲሆን እንደተጠበቀውም ጉባዔውን ተከትሎ የሁለቱ ቡድኖች ሽኩቻ ይፋ እሆነ መሄዱንና ለሊቀመንበርነት የየበኩላቸውን ትግል እአደረጉ እንዳሉ ለማወቅ ተጭሏል። ሁኔታውን አስመልክቶ አምዶም ገ/ስላሴ ከመቀሌ የጻፈው ውጥረቱን በግልጽ ያስረዳል።

የህወሓት ሊቀ መንበርነት…?

_______________

የህወሓት 12ኛ ጉባኤ መካሄድ ተከትሎ የሊቀ መንበርነት ስልጣን ሽኩቻ እየተካሄደበት ይገኛል። ኣብዛኛው የትግራይ የፌስቡክ ኣክትቪስቶች፣ ወጣቶችና ሙሁራን የህወሓት ኣባላት፣ ሌሎች ለውጥ ፈላጊ ኣክትቪስቶችና ሌሎች ፖለቲከኞች በጉጉት እየጠበቁት ይገኛሉ ። የኣርከበ በድምፅ በጉባኤው መሳተፍ ለብዙዎች የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ወደ ኣሸናፊነት የተጠጋ ቢመስላቸውም ጉዳዩ ሌላ ነው። ኣርከበ ተመልሶ የማይወዳደር መሆኑ ስላረጋገጡ የትግራዩ ኣንጃም እንዲሳተፍ በኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ታስረው የመጡት የወረዳ ተሳታፊዎች(ማንበብና መፃፍ የማይችሉ የሚገኙባቸው ሴቶችና ገበሬዎች የሚገኙባቸው የኣባይ ወልዱ ታማኞች ) እንዲፈቅዱለት ኣድርገዋል። እንዲሳተፍ የተቀሰቀሰው ” ኣርከበ የመጣው ለሊቀ መንበርነት ሳይሆን በባቡርና ኢንዳስትሪ ከፍተኛ ስራ እንዲሰራ ነው። ስለዚ ቢሳተፍ ችግር የለውም ” የሚል ተነግሮሯቸው ነው።

“ኣባይ ደራ” የሚል የበረሃ ስሙ በመጥራት ” ከመለስ ሞት በሗላ ድርጅቱ ኣጋጥሞት የነበረው ከፍተኛ ችግር ያለ ኣባይ ደራ ምርጥ መሪነት ድርጅታችን ለመበታተን ይዳርጋት ነበር ” የሚል ፕሮፖጋንዳ ተምረው ኣጥብቀው በመያዝ ኣሁንም ሌላ ኣማራጭ እንደሌለ ኣምነው ለማስፈፀም ተዘጋጅተዋል። ወፍ የለም “ኣባይ ደራ ” የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ ሲቆጣጠሩ የቴሌው ኔትወርክ ደግሞ ዶክተር ደብረፅዮን በእጃቸው ይገኛል። ኣባይ ወልዱ የቴሌው ኔትወርክ ለመቆጣጠር ሞባይል ስልክ ወደ ኣዳራሽ እንዳይ ገባ ኣድርገዋል። እነ ዶክተር ደብረፅዮን ደግሞ የኣንድ ለ ኣምስት ኔትወርክ እንዳይሰራ መበተን ይጠበቅባቸዋል። ለውጥ ……………… የምትጠብቁ የዋሆች እርማቹ ኣውጡ። በስብሰባው ኣንድ ተሳታፊ ህዝቡ ክፉኛ ተቀይሞናል፣ የመረጠንም ዕሬት ዕሬት እያለው ነው። ስለዚ ለውጥ የህልውናችን ጉዳይ ነው። ኣለበለዚያ ጥፋት ቅርብናት በማለት የተናገረው ደማቅ ጭብጨባ ኣስገኝቶለታል። ስብሰባው ከተያዘለት ግዜ በላይ እንደሚፈጅ ታውቋል። የመቐለ ከሓወልቲ እስከ ኣክሱም ሆቴል ያሉ ጎዳናዎች በቖልዑ ኣሸንዳ ምትክ ብሬን የጫኑ ፓትሮል የፌደራል ፖሊስና የክልል ልዩ ሃይል እየጠበቁ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አስቀድሞ በህብር ሬዲዮ ህወሓት መሪዎችን የስልጣን ሽኩቻ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በዘገብንበት ወቅት የህወሓት ታዣዥ የሆኑት የብአዴንና የኦህደዴድና የዸህዴግ አመራሮችን ሁለቱም ቡድኖች የየራሳቸውን ደጋፊ ለማሰባሰብ ሲሚክሩ ተስተውሏል። ህወሓት በ1993 ለሁለት የተከፈለ ሲሆን የአቶ መለስ ቡድን ከባድመ መልስ ሊዘምትበት ተነሳውን ቡድን አንጃ የሚል ስም ለጥፎ ማባረሩ የሚታወስ ሲሆን ከተባረሩት ውስጥ አቶ አባይ ጸሐዬ ይቅርታ ጠይቀው ሲመለሱ አቶ ገብሩ አስራትን ጨምሮ ተባረው የቀሩ እንደ አቶ ስዬ በሙስና ታስረው የወቱ ነበሩ።

የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ህወሓት ተከፍሎ የነበረ ሲሆን ጠላቶቻችን ብሎ የፈረጀው ሌላው የኢትዮጵአ ሕዝብ ስልታን ሊያገኝ ይችላል በሚል ጉዳዩን በሽምግልና ፈቶ አብሮ በክልልና በፌዴራል ዋና ዋናውን ስልታን ተቆጣጥሮ የቆው ሀይል ለዘንድሮውም ክፍፍል ተመሳሳይ <<ሽምግልና>> ሊአካሂድ ይችል ይሆናል። የቀሩት የይስሙላ ስልጣን የሚይዙ የሌሎች ድርጅት መሪዎች እንደተለመደው አሸናፊውን ቁጭ ብለው መጠበቃቸው አንዳንዶችን አስገርሟል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *