የሕወሓት የስልጣን ሽኩቻ በአዲስ አበባው ቡድን እየተመራ ነው፣ እነ ብአዴንም ሊቀመንበራቸውን መረጡ

metekakat_02

በስልጣን ሽኩቻ እየታመሰ ያለው ሕወሓት ከነሐሴ 16 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ እአካሄደ ያለውን ጉባዔ ተከትሎ አልተጠበቁ ክስተቶች መታየት ጀምረዋል። የአዲስ አበባና የመቀሌ ቡድን በሚል ከሁለት የተቧደኑትና በአንድ በኩል በወቅቱ የትግራይ ክልል ፕ/ት አባይ ወልዱ በሌላ በኩል ም/ጠ/ሚ/ርና የኢኮኖሚ ዘርፍ ሀላፊ ዶ/ር ደብረጽዮን በሌላ በኩል ዋናውን የሕወሃት ስልታን ለመቆጣጠር ውስጥ ውስጡን ሲደራጁና አንዱ አንዱን ሲከስ የቆየ ቢሆንም በጉባዔው ያለ ድምጽ ይሳተፉ የተባሉት እነ ስብሃት ነጋ ድንገት ጉባዔው ከተጀመረ በሁዋላ የድምጽ ተሳታፊ ሆነዋል። በመተካካት ስም ከፓርቲ ቀጥተኛ ስልጣን ያልነበራቸው ስብሃት ነጋ፣ አርከባ ዕቁባይ፣አቶ ብርሃኔ ገ/ክርስቶስ እና ስዩም መስፍን እና የቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንትና አቶ ሀይለማሪአም የጸጥታ አማካሪ ጸጋዬ በርሄ እና ሌሎች 17 አመራሮች የድምጽ ተሳታፊ ሆነዋል።

በአዲሱ ውሳኔ መሰረት ራሱን ሲያደራጅ የቆየውና የአዲስ አበባውን ቡድን በአንድ ለአምስት ይረታል የተባለው የአባይ ወልዱ ቡድን አጣብቂኝ ውስጥ የወደቀ መስሏል። አቶ አርከበ በምርቻ አልተሳተፈም የክልል ፕሬዝዳንትም ሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆን አይችልም የሚል ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩት ደጋፊዎቹ በጉባዔው አስቀድሞ በተጠና ሴራ የድምጽ ተሳታፊ መሆኑ ከታወቀ በሁዋላ የአቶ አባይን ቡድን ማጥላላት ይዘዋል። በእነ አባይ ቡድን ላይ ያልተጠበቀ ቻና የፈጠረው የእነ ስብሃት ያለ ድምጽ ይሳተፋሉ ተብሎ በጉባዔው የድምጽ ስልታን ማግኘት ግለሰቦቹ በድርጁቱ አመራር ውስት አስቀድመው ባላቸው ተሰሚነት የሚፈልጉትን ለመቀባትና አብረውት ለቆሙት ደብረጽዮን ድል አድርገው የቆጠሩም አሉ።ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሕወሓት ሌሎቹን ድርጅቶች ሁሉ ጭሰና አድርጎ ዋና ዋና የአገሪዩን ስልጣንና ኢኮኖሚ ተቆታትሮ የዘለቀው <<ኢህአዴግ>> እና አጋር በሚሌ ባሰባሰባቸው ድርጅቶች አማካይነት ሲሆን የሕወሓትን የስልጣን ሽኩቻ ተከትሎ ዋና ዋናዎቹ ታዛዦች በኦህዴድ፣በብአዴንና በደህዴግ ያሉት አስቀድመው በጉባዔያቸው የድርጅቶቹን መሪዎች መርጠው የአለቃቸውን የሕወሃት መጨረሳ እየጠበቁ መሆኑ አስቀድሞ መዘገቡ ይታወሳል። ስለ ጉዳዩ ሪፖርተር ጋዜጣ በበኩሉ የዘገበ ሲሆን ስለ ልዩነቱም ሆ የስልታን ሽኩቻው ሳይጽፍ ቀርቷል።

ሦስቱ አባል ድርጅቶችም ጉባዔያቸውን አካሂደዋል ከነሐሴ 16 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በመቐለ ሰማዕታት አዳራሽ እየተደረገ ባለው 12ኛው የሕወሓት ጉባዔ፣ በመተካካት ተሸኝተው የነበሩ የሕወሓት አመራሮች በጉባዔው እንዲመረጡና እንዲመርጡ ተወሰነ፡፡ አዘጋጅ ኮሚቴው የጋበዛቸው ያለ ድምፅ እንዲሳተፉ ነበር፡፡ ከ1,650 በላይ ጉባዔተኞች በታደሙበት ጉባዔ የተገኙ አንድ ተሳታፊ ከዚህ ቀደም ተገፍተው የወጡ ያሏቸው ነበር አመራሮች በድምፅ እንዲሳተፉ ጥያቄ ካቀረቡ በኋላ፣ በጉዳዩ ላይ የመከረው ጉባዔ በጭብጨባ በሙሉ ድምፅ ጥያቄውን ተቀብሎታል፡፡ በዚህም መሠረት ዶ/ር አርከበ እቁባይ፣ አቶ ስብሃት ነጋ (አቦይ)፣አምባሳደር ሥዩም መስፍን፣ አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ፣ አቶ ፀጋዬ በርኼን ጨምሮ 17 ነባር አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ ጉባዔው በእስካሁኑ ቆይታው በአንደኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ በመልካም አስተዳደርና በመተካካት ላይ ተወያይቷል፡፡ በመልካም አስተዳደር እጦት ክልሉ እየተጠቃ እንደሆነ በርካታ አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡ በተለይ በአንድ የሃይማኖት አባት የቀረበው የመልካም አስተዳደር እጦት ትኩረት የሳበ ነበር፡፡ የሕወሓት አመራሮች ድርጅቱ ቀድሞ አንግተውት የነበረውን ዓላማ እንደረሱ በአጽንኦት ገልጸው፣ ፍትሕ በገንዘብ እየተገዛ የክልሉ ሕዝብ የማያውቀው አዲስ ባህል በመጎልበቱ ይህንንም እንደሚዋጉት አመልክተዋል፡፡ ‹‹እሳት ያልፈራ ሕዝብ እናንተን የሚፈራ ይመስላችኋል?›› ሲሉም ጥያቄአቸውን አቅርበዋል፡፡ መተካካትን በተመለከተም ወደ መገፋፋት በመቀየሩ ያለ ዕድሜና አቅም ማነስ ዶ/ር አርከበና አምባሳደር ብርሃነ እንዲወጡ መደረጉን ተችተዋል፡፡ እንደ ድሮው መገማገምና አንዱ አንዱን ተጠያቂ ማድረግ በመሸፋፈንና በመጠባበቅ መቀየሩም ተገልጿል፡፡

የሕወሓት ሊቀመንበርና የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ዓባይ ወልዱ የቀረበውን ቅሬታ ተቀብለው፣ የተሠራ ነገር ቢኖርም ትልቅ ዳገት እንደሚጠብቅ ገልጸዋል፡፡ የአመራር አባላት ራሳቸውን ማጥራትና ወደ ራሳቸው መመልከት እንደሚኖርባቸው አሳስበዋል፡፡ ዶ/ር አርከበ በጉባዔው ንቁ ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን፣ ሕዝቡ ቅሬታ እያቀረበ ያለው በፍትሕ አካላትና በፓርቲው አባላት መሆኑ አሳሳቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ጉባዔው ዛሬ የሚጠናቀቅ ሲሆን፣ የሥራ አስፈጻሚና የማዕከላዊ ኮሚቴ እንዲሁም የቁጥጥር ኮሚሽን አባላትን ይመርጣል፡፡ 11ኛው የብአዴን ድርጅታዊ ጉባዔ በባህር ዳር በድርጅቱ ሪፖርት ላይ ተወያይቷል፡፡ ጉባዔው በክልሉ የተመዘገበውን የኢኮኖሚና ዕድገትና የግብር ምርት ውጤታማነት የገመገመ ሲሆን፣ ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ 10.4 በመቶ በመድረሱ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ መቻሉ ተገልጿል፡፡ የመጀመርያው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች፣ መልካም አስተዳደር፣ ትምህርት፣ ጤናና ሌሎች መስኮችም በግምገማው ተካተዋል፡፡ መልካም አስተዳደርን በተመለከተና በሥራ ፈጠራ ጉድለቶች መኖራቸውን የገመገመው ጉባዔው፣ የክልል ከፍተኛ አመራሮችም ለችግሩ ከፍተኛውን ድርሻ እንደሚይዙ አውስቷል፡፡ የድርጅቱ ጉባዔ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የብአዴንና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላትን፣ የድርጅቱን ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር በመምረጥ ማክሰኞ ምሽት ተጠናቋል፡፡ ማክሰኞ ምሽት የተመረጡት እነማን እንደሆኑ ግን አልታወቀም ነበር፡፡

ኢሕዴድ በአዳማ ከተማ 8ኛ ጉባዔው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል፡፡ በጉባዔው በክልሉ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ለማምጣት የሚችሉ አዳዲስ ሐሳቦች እንደ ግብዓት ሲሰባሰቡ እንደነበር ተገልጿል፡፡ በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን በክልሉ የ11.2 በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብና የኢኮኖሚውን መዋቅራዊ ሽግግር ለማፋጠን የሚያስችሉ ውሳኔዎች ይተላለፋሉ ተብሏል፡፡ የኦሕዴድን ድርጅታዊ ህልውና ይፈታተናሉ የተባሉት ትምክህትና ጠባብነት፣ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ የተንዛዙ አሠራሮችና ፍትሐዊነት የጎደላቸው አመራሮች በጉባዔው ወቅት መነሳታቸው ታውቋል፡፡ ላለፉት ሦስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው የኦሕዴድ ጉባዔ ማክሰኞ ምሽት ማተሚያ ቤት እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነበር፡፡

የደኢሕዴን ጉባዔ በሐዋሳ ማክሰኞ ነሐሴ 19 ቀን 2007 ዓ.ም. ተጠናቋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ሊቀመንበር ሆነው እንዲቀጥሉ ሲመረጡ፣ የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለምክትል ሊቀመንበርነት ተመርጠዋል፡፡ ጉባው በሦስተኛ ቀን ውሎው የመጀመርያውን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ገምግሞ፣ በምግብ እህል ራስን መቻል ላይ አበረታች ውጤት መገኘቱን ተወያይቶበታል፡፡ አበረታች የተባሉ ስኬቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ፣ ይቀራቸዋል የተባሉት ላይ ደግሞ በተጠናከረ ሁኔታ ርብርብ እንዲረደረግ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ የጤናና የትምህርት ዘርፍ ተደራሽነታቸው መልካም መሆኑ ተወስቶ፣ የጥራት ጉዳይ ግን እንዲታሰብበት ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡ በተጨማሪም ጠባብነት፣ ብልሹ አሠራርና ሙስና በድርጅቱ ውስጥ ቦታ እንደማይኖራቸው ውሳኔ ላይ መደረሱ በውይይቱ ወቅት ተነስቷል፡፡ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት፣ የደኢሕዴንና የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላትም ተመርጠዋል፡፡ የተሟላ ዝርዝር ግን ማግኘት አልተቻለም፡፡ በተያያዘ ዜና የብአዴን ነባር ታጋይና ከፍተኛ አመራር የነበሩት አቶ አዲሱ ለገሠ በክብር መሰናበታቸው የተገለጸ ሲሆን፣ አቶ ዮሴፍ ረታም እንዲሁ ተሰናብተዋል፡፡ የደኢሕአዴን ሊቀመንበር፣ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል በመሆን ያገለገሉት ዶ/ር ካሱ ኢላላ እንዲሁ ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት በክብር መሰናበታቸው ተገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ አስቀድሞ በህብር ሬዲዮ ህወሓት መሪዎችን የስልጣን ሽኩቻ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በዘገብንበት ወቅት የህወሓት ታዣዥ የሆኑት የብአዴንና የኦህደዴድና የዸህዴግ አመራሮችን ሁለቱም ቡድኖች የየራሳቸውን ደጋፊ ለማሰባሰብ ሲሚክሩ ተስተውሏል። ህወሓት በ1993 ለሁለት የተከፈለ ሲሆን የአቶ መለስ ቡድን ከባድመ መልስ ሊዘምትበት ተነሳውን ቡድን አንጃ የሚል ስም ለጥፎ ማባረሩ የሚታወስ ሲሆን ከተባረሩት ውስጥ አቶ አባይ ጸሐዬ ይቅርታ ጠይቀው ሲመለሱ አቶ ገብሩ አስራትን ጨምሮ ተባረው የቀሩ እንደ አቶ ስዬ በሙስና ታስረው የወቱ ነበሩ።

የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ ህወሓት ተከፍሎ የነበረ ሲሆን ጠላቶቻችን ብሎ የፈረጀው ሌላው የኢትዮጵአ ሕዝብ ስልታን ሊያገኝ ይችላል በሚል ጉዳዩን በሽምግልና ፈቶ አብሮ በክልልና በፌዴራል ዋና ዋናውን ስልታን ተቆጣጥሮ የቆው ሀይል ለዘንድሮውም ክፍፍል ተመሳሳይ <<ሽምግልና>> ሊአካሂድ ይችል ይሆናል። የቀሩት የይስሙላ ስልጣን የሚይዙ የሌሎች ድርጅት መሪዎች እንደተለመደው አሸናፊውን ቁጭ ብለው መጠበቃቸው አንዳንዶችን አስገርሟል።

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *