በአሜሪካ ሁለት የቴሌቪዥን ጋዜጠኞች በቀጥታ በሚተላለፍ ፕሮግራም ላይ ሳሉ በቀድሞ ባልደረባቸው ተገደሉ

አሊሰን ፓርከር ከባልደርባዋ (ምስል ቀራጩ) አዳም ዋርድ ጋር
አሊሰን ፓርከር ከባልደርባዋ (ምስል ቀራጩ) አዳም ዋርድ ጋር

ታምሩ ገዳ- ህብር ሬዲዮ (ላስ ቬጋስ )የአሜሪካው ኤቤሲ ቴሊቭዥን እህት ኩባንያ ለሆነው የቨርጂኒያው WDBJ7 ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ የሆነችው የ 24 አመቷ አሊሰን ፓርከር ወደሌላ ድርጅት ለመዛወር እድል በማግኝቷ ከ WDBJ7 ጋር የመጨረሻዋ ሰራዋ የሚሆነውን የዛሬው የቀጠታ(live) ቃለምልልስ ነበር ።ይሁን እንጂ አሊሰን ከባልደርባዋ (ምስል ቀራጩ) አዳም ዋርድ ጋር በስራ ተጠምደው ሳሉ በአንድ ወቅትለአጭር ጊዜ የሰራ ባልደረባዋ በነበረው በሁዋላም ከሰራው በተባረረው የ41 አመቱ ቬስታር ፈላንግስተን በተተኮሰባቸው ጥይት ህይወታቸው አልፏል።

ቃለምልልስ ሲደረግላቸው የነበሩት እንግዳም ቆሰለዋል ።ገዳዩ ቬስታር እርምጅውን የወሰደው በጥላቻ ሰሜት ተነሳስቶ መሆኑን በቲዊተር እና በፊስ ቡኩ ላይ ጠቅሶ የራሱን ህይወትም ማጥፋቱ ተገልጻል ።እዚህ ላይ ይሄ አሳዛኝ ድርጊት ሲፈጠር የአሊሰን እጮኛ እና ዜና አቅራቢ የሆነው ክሪስ እና የተቀሩት የእለቱ ተረኛ ባልደረቦች በሙሉ ደርጊቱን ከስቱዲዮ በቀጥታ የመለከቱ ነበር። ሃዘኑንም አስደንጋጭ እና ድርብ ድርብርብ አድርጎታል።

የቴሌቪዠኑ ጣቢያው ሃላፊ የሆኑት ማርክም “ጋዜጠኞች ወደ ጦር ሜዳ ሲላኩ አደጋ እንዳይገጥማቸው ትሰጋለህ ፣እንደዚህ አይነቱ ክስተትን ግን እንዲት እናምናለን?”በማለት ሃዘናቸውን እና ድንጋጤያቸውን ገልጸዋል።

 

የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *