Hiber radio: ፕ/ር መረራ ጉዲና ኢሕ አዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ፣ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የአገዛዙ አጋዚ ወታደሮች በዩኒቨርስቲው ውስጥ ገብተው የሚያደርሱባቸውን ጥቃት በመቃወም ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄዱ፣ሴት ተማሪዎች መደፈራቸው ተገለጸ፣ ኤርትራ የየመኑን አካባቢያዊ ጦርነትን መቀላቀሏን በይፋ አሰታወቀች፣ሸንጎ የአገዛዙ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የድንበሩን ጉዳይ ጨምሮ ያቀረቡትን የተምታታ ሪፖርት አጣጣለ ፣አገዛዙ የቅማንት ብሔር የማንነት ጥያቄን ውዝግብን ለማብረድ ልዩ ኮሚቴ አዋቅርኩ ይላል፣ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ህወሃት ሆን ብሎ ተጨማሪ መሬት ለመውሰድ ያለመበት አጀንዳ ነው የሚሉ አሉ፣የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እና ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የአገዛዙ ፍርድ ቤት 28 ቀን ፈቀደ፣ ዛሬ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ለመወያየት ወደ ካርቱም የተጓዙት የኢትዮጵያ ልዑካኖች ከሰብሰባው ቦታ አርፍደው ደረሱ እና ቃለ መጠይቅ ቃለ መጠይቅ ከአቶ አለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ጋር እና ሌሎችም አሉን

የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ፣ከላይ አቶ አለሙ ያይኔ የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣ ካርታ፣ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው፣ከታች ፕ/ር መረራ ጉዲና፣የተማሪዎቹ ተቃውሞ.ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ
የህብር ሬዲዮ ዋና አዘጋጅ ፣ከላይ አቶ አለሙ ያይኔ የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣ ካርታ፣ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው፣ከታች ፕ/ር መረራ ጉዲና፣የተማሪዎቹ ተቃውሞ.ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ

የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 17 ቀን 2008 ፕሮግራም

<…አቶ ሀይለማሪያም የሚሉት የሚታመን ቢሆን ኖሮ ድንበር ለሱዳን አይሰጥም ነበር። ይሄን ስርዓት ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት አይተነዋል ።የማይታመን የአገሪቱን ጥቅም አሳልፎ የሚሸት ነው። የሳቸው የተምታታ ንግግርን ትተን ኢትዮጵያውያን ለሱዳን ቆርሰው ሊሰጡ በሩጫ ላይ ያሉበትን የአገራችንን ለም መሬት ለመስጠት የሚደረግ ማንኛውም ውል እንቃወማለንከኢትዮጵያ የትኛውም ግዛት አካባቢ ተቆርሶ የሚሄድ መሬት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚመለከት ነው። ዛሬ የአገራችን መሬት ተላልፎ ለሱዳን እንዳይሰጥ በርካታ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች፣የአንድነትም ሆነ የብሄር ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መገናኛ ብዙሃን፣በርካታ የሀይማኖትና የሲቪል ማህበራት የአገሪቱ ድንበር ለሱዳን ተላልፎ እንዳይሰጥ ተቃውመዋል።ይህንኑ ፒቲሽን ሁሉም እንዲፈርመውና ፊርማው ለተባበሩት መንግስታት …> የአቶ ዓለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…የዚህ ስርዓት ባለስልጣናት በኦሮሚያ ክልል ሕዝቡ ያነሳውን ሰላማዊ ጥያቄ በመሳሪያ ሀይል ለማዳፈን የቻሉትን ሁሉ እርምጃ ወስደዋል።ህጻናትን ሳይቀር ገለዋል።አቶ ሐይለማሪያምን ጨምሮ እጃቸው በደም የተጨማለቀ ነው ጊዜው ሲደርስ በዓለም አቀፉ ወንጀለኛ ፍርድ ቤት ፊት የሚያቀርባቸው ግፍ ነው የፈጸሙት።የሕዝቡ ምሬት ጫፍ ደርሷል።በማሰር በመግደል ሰጥ ለጥ አድርገን እንቀጥላለን የሚለው ህልማቸው ብዙም የሚሳካ አይመስልም።በሁሉም ወገን ያለው ልሂቃን ማሰብ ያለበት በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች እንዳሰቡትና ሲያደርጉት እንደኖረው ከታሪኩ በክፉ በክፉ ብቻ ላይ ታስሮ በዚያ ሲነታረክ ሲጋጭ መኖር ወይም ወደፊት በሚያራምደው የጋራ ጉዳይ ላይ ማተኮር አለበት ይህ ካልሆነ ግን… > ጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ በወቅቱ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ከአገር ቤት ከሰጠውት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

ለወደብ አልባዋ ኢትዮጵያ የወጪ እና የገቢ ንግድ የጀርባ አጥንት የሆነችው ጅቡቲ ውስጥ ሰሞኑን የተከሰተው ፖለቲካዊ ቀውስ ሲዳሰስ (ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

/ መረራ ጉዲና ኢሕ አዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ

የሚሊዮኖች ደጋፍ ያለው ሰላማዊ እና ሕዝባዊ ተቃውሞን ማስቆም በጭራሽ አይቻልም/ መረራ ጉዲና

የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የአገዛዙ አጋዚ ወታደሮች በዩኒቨርስቲው ውስጥ ገብተው የሚያደርሱባቸውን ጥቃት በመቃወም ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄዱ

ሴት ተማሪዎች መደፈራቸው ተገለጸ

ኤርትራ የየመኑን አካባቢያዊ ጦርነትን መቀላቀሏን በይፋ አሰታወቀች

ሸንጎ የአገዛዙ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የድንበሩን ጉዳይ ጨምሮ ያቀረቡትን የተምታታ ሪፖርት አጣጣለ

አገዛዙ የቅማንት ብሔር የማንነት ጥያቄን ውዝግብን ለማብረድ ልዩ ኮሚቴ አዋቅርኩ ይላል

የቅማንት የማንነት ጥያቄ ህወሃት ሆን ብሎ ተጨማሪ መሬት ለመውሰድ ያለመበት አጀንዳ ነው የሚሉ አሉ

የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እና ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የአገዛዙ ፍርድ ቤት 28 ቀን ፈቀደ

ዛሬ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ለመወያየት ወደ ካርቱም የተጓዙት የኢትዮጵያ ልዑካኖች ከሰብሰባው ቦታ አርፍደው ደረሱ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-122715-010316

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *