Hiber Radio: ማዲንጎ አፈወርቅ በወቅቱ በሃገራችን ባለው ሁኔታ የተነሳ በሰሜን አሜሪካ ሊያደርጋቸው ያቀዳቸውን ኮንሰርቶች ሰረዘ

madingo-002

በቅርቡ ከዚህ ቀደም በአላሙዲን በሚደገፈው ፌዴሬሽን ላይ ለመዝፈን በመወሰኑ ላስቀየመው ሕዝብ ይቅርታ የጠየቀው ድምጻዊ ማዲንጎ አፈወርቅ መጪውን አዲስ ዓመት አስመልክቶ ያዘጋጀውን የሙዚቃ ኮንሰርት በአገራችን በወቅታዊው ሁኔታ ሳቢያ መሰረሱንና ለሌላ ጊዜ ማራዘሙን ለዘሐበሻ ገለጸ። ማዲንጎ አዲሱን ዓመት አስመልክቶ በዋሽንግተንና በተለያዩ የአሜሪካ ከተሞች በመጪው ወር አቅዷቸው የነበሩትን ኮንሰርቶች በሙሉ ሰርዞ ለሌላ ጊዜ አራዝሟል።

ምርቻ 97 ተከትሎ በአገር ቤት ንጹሃን ሰኔ 1/1997 ዛሬም ስልጣን ላይ ባለው ሕወሓት በተጨፈጨፉ ወቅት በአውሮፓ የነበረውን ኮንሰርት ሕዝብ ከተጠራ በሁዋላ ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ መሰረዙ ይታወሳል።

በቅርቡ ታዋቂ አርቲስቶች በአገር ቤት ያለውን ግፍ አገዛዝ በመቃወምና ከሕዝብ ጎን በመቆም የተለያዩ የሙዚቃ ስራዎችን የኦሮሞና የአማራ ሕዝብ ተቃውሞን ተከትሎ ማውጣታቸው አይዘነጋም። 25 በቀኝ ሒድልኝ የሚለው የፋሲን ደሞዝ፣የመሐሪ ደገፋው <<ጎንደር>> እና የመስፍን በቀለ ሰላም ለኢትዮጵአ ብሎ ወታደሩ ወገንህን አትግደል ያለበት ዜማ ሲጠቀሱ የተለያዩ የኦሮሚኛ ሙዚቃ አቀንቃኞችም በበኩላቸው ትግሉን የሚደግፉ ሰማዕታቱን የሚያከብሩ ዜማዎችን አውጥተዋል። በአሁኑ ወቅት በዓሉት ተከትሎ የሚደረጉ የሙዚቃ ኮንሰርቶች ሊሰረዙ ይገባል ወገናችን እየሞተ ነው ለተጎዱት ወገኖች ገቢ ካልሆነ በቀር ጊዜው የመዝናናት አይደለም የሚሉ ተቃውሞዎችን መደመጥ ጀምረዋል።

ድምጻዊ ማዲንኦ በዘሐበሻ በኩል ያስተላለፈውን የኮንሰርቱን መሰረዝ ይፋ ያደረገበትን መልዕክዩን ያድምጡት።

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *