Hiber Radio: ሕወሃት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን አፍኖ ለመውሰድ ተደጋጋሚ የሽብር ሙከራውን ቀጥሏል፣ቻይና የሕወሃት/ኢህአዲግ አገዛዝን እና የኤርትራው አቻውን ለማግባባት ፍላጎት አላት ተባለ፣፣ኢትዮጵያውያን ከሕወሓት አገዛዝ ባርነት ሊያወጣን የሚችለው በጋራ ስንታገል እንጂ የተናጠል ትግሉ ውጤት እንደማያመጣ ተገለጸ፣አንድ የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣን አወዛጋቢው የህዳሴ ግድብን በምስጢር መጎብኘታቸው ግብጽን አስቆጣ፣የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላትን አገዛዙ በአሸባሪነት መክሰሱ ይፋ ሆነ እና ሌሎችም

 

ጋዜጠኛ ሀብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ  ታህሳስ 9 ቀን 2009 ፕሮግራም

<…ኢትዮጵያውያን ተነጣጥለን የምናደርገው ትግል ያስከተለው ተነጣጥሎ መመታት ነው።በዘርም እንደራጅ፣በሀይማኖትም ይሁን በዚያ አገር ላይ ነጻነት ለማምታት ትግሉን ብሄራዊ መልክ ካላሲያዝነው፣ትግላችን የጋራ ካልሆነ የእኛ አለመስማማት በተዘዋዋሪ የምንጠላውን ስርዓት እድሜ ማርዘም ብቻ ሳይሆን ..> ጋዜጠኛና አክቲቪስት ሳዲቅ አህመድ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ካደረግንለት ውይይት የተወሰደ(ቀሪውን ያዳምጡት)

የዳንኤል ሺበሺ ትዝብት ከእስር ቤት

ሶሪያ የመጨረሻው ዘመን ፍንጭ?፥ወይስ የሶስተኛው የዓለም ጦርነት አውድማ? በሶሪያዋ ከተማ አሌፖ ላይ እየደረሰ አለው እልቂትና ቀድሞ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች ፥መጻህፍት እና ፓለቲከኞች ስለ ሶሪያው እልቂት የሰጡት ትንበያዎች ከወቅቱ ጋር ሲዳሰስ (ልዪ ዘገባ)

የታሰሩትን እንደግፍ ቤተሰቦቻቸውን እናስባቸው (የህብር ጥሪ)

በማህበራዊ ሚዲያው የለውጥ ፈላጊው ሀይል ወቅታዊ ትኩረት እና የጎንዮሽ ንትርኩ ማብቂያ የት ላይ ይሆን?

ከሶስቱ የማህበራዊ ሚዲያው ንቁ ተሳታፊዎች ጋር የተደረገ ውይይት የመጨረሻ ክፍል

ከጋዜጠኛ በብዩ ሲራክ፣እሸቱ ሆማ ቀኖ እና አክቲቪስት ሙሉነህ ዮሐንስ

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ሕወሃት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱን አፍኖ ለመውሰድ ተደጋጋሚ የሽብር ሙከራውን ቀጥሏል

ቻይና የሕወሃት/ኢህአዲግ አገዛዝን እና የኤርትራው አቻውን ለማግባባት ፍላጎት አላት ተባለ

የቤጂንግ መንግስት አካባቢያዊ ጥቅሞቿን ለማስከበር ወታደራዊ ሀይል እስከ መጠቀም እንደምትደርስ ተገለጸ

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን በድጋሚ ቤተሰቦቹ ሊያገኙት አልቻሉም

የአማራ ሕዝብ ላይ በስነ ተዋልዶ ጤና ስም ሕወሃት የጀመረውን የዘር ማምከን መቀጠሉ ተነገረ

ኢትዮጵያውያን ከሕወሓት አገዛዝ ባርነት ሊያወጣን የሚችለው በጋራ ስንታገል እንጂ የተናጠል ትግሉ ውጤት እንደማያመጣ ተገለጸ

የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላትን አገዛዙ በአሸባሪነት መክሰሱ ይፋ ሆነ

የእንግሊዝ መንግስት ለአምስት ኢትዪጵያዊያን ታዳጊ አርቲስቶች የሰጠው 140ሚሊዮን ብር ባለስልጣናቱን አስቆጨ

ገንዘቡ 154 ዓመታት ያለ ስጋት የሚያስራቸው ነበርተቺዎች

 አንድ የሳውዲ አረቢያ ባለስልጣን አወዛጋቢው የህዳሴ ግድብን በምስጢር መጒብኘታቸው ግብጽን አስቆጣ

“የባለስልጣኑ ጉብኝት በግብጽ ህዝብ ላይ የተቃጣ ሴራ ነው”የግብጹ ዲፕሎማት

በኢትዩጵያው የቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ሰሞኑን ህይወቱ ያለፈው ኬኒያዊው እስረኛ የኬኒያ ባለስልጣናትን ለትችት ዳረገ

የአገሪቱ ፕ/ት ጭምር ባለስልጣናቱ በጉዳዩ ጣልቃ እንዲገቡ ቢጠየቁ ዝምታን መርጠዋል

የጋምቢያው ፕ/ት ያያህ ጃሜ ስልጣን በፍቃዳቸው ካለቀቁ ዎጋቸውን እንደሚስጧቸው የጎረቤት አገራት አስጠነቀቋቸው

ተመራጩ ፕ/ት ጃሜን ለፍርድ እንደማያቀርቡ አቋማቸውን ገለጹ

ሌሎችም 

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

 ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በየቀኑ በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ በ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ ከ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *