Hiber Radio: በቬጋስ የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ ፖሊስ የጀመረውን ምርመራ አለማጠናቀቁን ገለጸ ፣ተጨማሪ መረጃዎች ወጥተዋል

በቬጋስ ባለፈው ዕሁድ ምሽት ለሀገረሰብ የሙዚቃ ኮንሰርት በተሰባሰቡ ከ22 ሺህ በላይ እድምተኞች ላይ የ64 ኣመቱ የኔቫዳ ሜስኪት ነዋሪ የሆነው ስቴቨን ፓዶክ  ከነበረበት የማንዳላቤ ሆቴል 32ኛ ፎቅ የሆቴል ክፍል በከፈተው አውቶማቲክ ተኩስ ሳቢያ በወሰደው የጭፍጨፋ እርምጃ  የሟቾች ቁጥር 59 የደረሰ ሲሆን ከ527 በላይ ንጽሃን ቆስለዋል።አደጋውን አስመልክቶ የላስ ቬጋስ ሜትሮ ፖሊስ ዛሬ ማምሻውን በሰጠው ተጨማሪ መግለጫ የአደጋው ሁኔታ ምርመራ ተጨማሪ ጥቂት ቀናት እንደሚፈጅ ገልጿል።

ፖሊስ ከመገናና ብዙሃን የሚነሱ ጥያቆዎችን መሰረት አድርገው በሰጡት መግለጫ የአደጋውን መንስዔ ለማጣራት ጊዜ እንደሚያስፈልግ፣በአደጋው ወቅት የነበሩ ሁኔታዎች አስመልከቶ ምክትል የፖሊስ አዛዡ ኬቨን ማከማሂል እንደተናገሩት የአደጋ አድራሹ ከዘጠኝ እስከ 11 ደቂቃ ለሚሆን ጊዜ መተኮሱን፣ፖሊስ ፈጥኖ ተኩስ መከፈቱን ወዲአው አውቆ የወሰደውን እርምጃና ተያያዥ ጉዳዮች አብራርተዋል።

ለመገናና ብዙሃን ይፋ የሆነውን በገዳዩ ሆቴል ክፍል የነበረውን መሳሪያ እና ገዳይ ወድቆ በአንድ ጎን የሚያሳውን ፎቶ አስመልክቶ በሰጡት መግለቻ ፎቶው እውነተኛ መሆኑና እንዴት ወጥቶ ለአደባባይ እንደበቃ የውስጥ ምርመራ እንደሚአደርጉ ጠቁመዋል። በጊዜው በአደጋው ሳቢያ ተሽከርካሪያቸውን መውሰድ ስላልቻሉና ተጨማሪ መረጃ ስላላቸው ሰዎች መረጃዎቻቸውን ለፖሊስ ስለሚሰጡበት አግባብ ገልጸዋል። የምርመራ ሂደቱ ጊዜ እንደሚያስፈልገው ጠቁመው በአደጋው ወቅት ለመዝናናት በስፍራው ከባለቤቱ ጋር ሳለ በቀጥታ ሕይወት ለማዳን ሲረባረብ የሞተው የፖሊስ ባልደረባ ቻርልስተን ሀርትፊልድ የከፈለውን መስዋዕትነት አስታውሰው የመታሰቢያ ዝግጅትዩን ስፍራ ይፋ አድርገዋል።

የቬጋሱ አደጋን መድረስ ተከትሎ ሲ.ኤን.ኤንን ጨምሮ የተለያዬ ዓለም አቀፍ መገናና ብዙሃኖች የቀጥታ ስርጭታቸውን ከቬጋስ አድርገው የተለያዩ ዘገባዎችን እአቀረቡ የሚገኝ ሲሆን በተለይ አወዛጋቢ ሆነው የመሳሪያ ቁጥጥር አጀንዳ ዳግም ተቀስቅሶ ተሌአዩ አስተያየቶች የሚሰጡ ሲሆን የዕሁዱን ጭፍጨፋ ያካሄደው ተጠርጣሪ የ64 ኣመቱ ስቲቨን ፓዶክ ከሄቴል ክፍሉ የተገኘውን 23 መሳሪያ ጨምሮ ከቤቶቼ የተገኘውን አካቶ 47 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች የተገኘበት መሆኑ ተገልጿል። ጡረተኛ አካውንታት እና ቤቶችን በማከራየት ጥሩ በኑሮው የተደላደለ የነበረው ግለሰብ ከቬጋስ 80 ማይል እርቀት ላይ በምትገኘው ሜስኪት ነዋሪ የነበረ ሲሆን በመቆመር የሚዛናና በመሆኑ በተደጋጋሚ እንደሚመጣ መገናና ብዙሃን ዘግበዋል።

ዝርዝር መግለቻዎችን የያዘው የዛሬው ምሽት የፖሊስ መግለጫን አያይዘነዋል። በዚህ አጋጣሚ የህብር ሬዲዮ አዘጋጆች በአደጋው ሳቢአ ሕይወታቸውን ላጡ እና በደረሰው የአካል ጉደዳት የተሰማንን ሐዘን እየገለጽን በግል ከምናውቃቸው ጀምሮ ከመላው ኣለም አድማጮቻችን ስለአለንበት ሁኔታ ተጨንቃችሁ ለላካችሁልን መልዕክት ደርሶናል እናመሰግናለን። ተጨማሪ መረጃዎችን ለማቅረብ የምንሞክር ሲሆን ዝርዝር መግለቻ የያዘውን ፖሊስ መግለቻ አያይዘን አቅርበናል።

ህብር ሬዲዮ አደጋውን አስመልክቶ አስቀድመን በመጠኑ መዘገባችን ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *