Hiber Radio : የቬጋሱን ጭፍጨፋ ያካሄደው ግለሰብ በርከት ያለ ሕዝብ ለመጨረስ በመኪና ላይ ጠምዶ ለማፈንዳት ማቀዱ ተገለጸ

የዕሁዱን ጭፍጨፋ ያካሄደው ስቲቨን ፓዶክ እና በሆቴል ክፍሉ ከተገኙ መሳሪያዎች በከፊል

(ህብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ) የላስ ቬጋሱን የዕሁድ የሀርቨስት ሩት 91 የአገረሰብ የሙዚቃ ኮንሰርት ከ22 ሺህ በላይ ታዳሚዎች ላይ ካለበት የማንዳላቤ 32ተኛ የሆቴል ክፍል የ64 ዓመቱ  ስቲቨን ፓዶክ በከፈተው ተኩስ 58 ንጹሃንን ገሎ ከ527 ከማቁሰሉም በተጨማሪ ሌላ ጥፋት የማድረስ ዓላማ እንደነበረውና በተሽከርካሪው ውስጥ በተከራየው ዘመናዊ ሄቴል ስዊት ከተገኘው 23 መሳሪያ ሌላ ሃምሳ ፖውንድ የሚመዝን ተቀጣጣይ እና 1600 ተጨማሪ ጥይቶች መገኘታቸውን ሲኤን ኤን ጠቅሶ ተጨማሪ ጥፋት የማድረስ ሀሳብ እንነበረው አመልክቷል።

የዕሁዱን ጭፍጨፋ ያካሄደው ይሄው ግለሰብ በሙዚቃ ዕድምተኞቹ ላይ ከተኮሰው በተጨማሪ ወደ አየር ማረፊያ አጠገብ ወደሚገኝ የነዳጅ ማጠራቀሚያ ሁለት ጊዜ የተኮሰ ሲሆን ሁለቱም ምንም ጉዳት አለማድረሱን ተቀጣታይ ነገርም እንዳልነበር ይሄው ዘገባ ጠቅሶ አስቀድሞ በከተማዋ በዳውን ታውን ከሴምቴምበር 22 እስከ 25 በተደረገው <<ላይፍ ኢዝ ቢዩቲፉል>> የተሰኘው ኮንሰርት ፊት ለፊት ካለ ህንጻ ክፍል ተከራይቶ መገኘቱ ፣በተሽከርካሪው ውስጥ የተገኘው ተቀጣጣይ ነገርና ተጨማሪ ጥይት በርከት ባለ ሕዝብ ላይ ደግሞ ጥቃት ለማድረስ እቅድ እንደነበረው ተጠቁሟል።

ፖሊስ ዛሬም የዕሁዱን ጭፍጨፋ ያካሄደውን ስቴቨን ፓዶክ ዋና ዓላማ እየመረመረ ሲሆን ከዕሁዱ ጥቃት ቡዋላ የማምለጥ ዕቅድ እንደነበረው የላስ ቬጋስ ሜትሮ ፖሊስ ዋና አዛዥ ሸሪፍ ጎሴፍ ላምባርዶ ገልጸው ዝርዝረ መረጃውን ከመግለጽ ተቆጥበዋል።

ዛሬም ጭፍጨፋውን ያካሄደው ግለሰብ ለምን ለማያውቃቸው ሰዎች ላይ የሩምታ ተኩስ ከፍቶ 58 ገድሎ ከ527 በላይ ያቆሰለበት አብይ ምክንያት ዛሬም ምላሽ አላገኘም። ማንም ስለ ዕቅዱ አስቀድሞ ያወቀ እንደሌለ ከወንድሙም ሆነ ከሴት ጓደናው የተገኘውን መረጃ መሰረት በማድረግ ተገልጿል።

በማካራን ኤርፖርት አጠገብ በሚገኘው የግል አየር ትራንስፖርት ከሚሰጥበት የንግድ ድርጅት በሆነው የነዳጅ ማጠራቀሚያ ላይ የ64 ዓመቱ ጥቃት አድራሽ ከተኮሰው ሁለት ጥይት አንደናው የላይኛውን የውጭ ክፍል ጠልቆ ለመግባት ቢሞክርም ምንም ጉዳት አለማድረሱን ባለስልጣናት ገልጸዋል።

የዕሁዱን ጭፍጨፋ አድራሽ ከጥቃቱ በሁዋላ ለማምለጥና በመኪና ላይ አጥምዶ የማፈንዳት ሀሳብ ሳይሆነው እንዳልቀረ የገመቱት ተንታኞች ራሱን ባይገል ኖሮ ተከታዩ ዕቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ መንቀሳቀሱ እንደማይቀር ተመልክቷል።

የዕሁዱን ጭፍጨፋ ለማድረስ ከተከራየው የማንዳላቤ 32ተኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ ስዊት አስቀድሞ ዳውንታውን የተካሄደውን ኮንሰርት ሊያይ የሚችልበትን ኦገዴን ኮምፕሌክስ ኮንዶ የተከራየ መሆኑን የፖሊስ ሀላፊው ትላንት በሰጡት መግለጫ መግለጻቸው ይታወሳል። ግለሰቡ ሁኔታውን ቃኝቶ ይሆን የሚለውም ለጊዜው አለመታወቁ ተገልጿል።ይሄው ግለሰብ ባለፈው ዓመት ብቻ 33 አውቶማቲክ ጠመንጃዎችን መግዛቱ ይፋ ሆኗል።

የጸጥታ ጉዳይ የዕሁዱን ጭፍጨፋ ተከትሎ ከፍተኛ ትኩረት እንደሚሰጠውና ከዚህ በሁዋላ ኮንሰርቶች፣ፌስቲቫሎች አዘጋጆች ትልቅ ትኩረት እንደሚሰጡት ተጠቅሷል።

ለ58 ንጹሃን መሞትና ከ527 በላይ መቁሰል ተጠያቂው የእሁዱን ጭፍጨፋ ያደረሰው የ64 ዓመቱ ግለሰብ አስቀድሞ በእሱ ጥያቄ በኔቫዳ ከቬጋስ 80 ማይል እርቀት ላይ አብራው የምትኖረውን የሴት ጓደኛውን ወደ ፊሊፒን መላኩን በጠበቃዋ በኩል በሰጠችው ተጨማሪ መረጃ ገልጻለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በቬጋስ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ በከተማዋ በተሌአዩ ስፍራዎች በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ወደ ጊዜያዊ የደም መለገሳ ጣቢአዎች በመሄድ ደም ለመለገስ አንዳንዶች 7 ሰኣት ያህል ጭምር የተሰለፉ ሲሆን ተጎጂዎችን ለመርዳት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ በጎ ፈቃደኞች የበኩላቸውን ድጋፍ ሲአደርጉ ተስተውሏል።

ለፖሊስም ሆነ ለኤፍ.ቢ.አይ ተጨማሪ መረጃ ስለ ጥቃት አድራሹ ማንም ሰው ያለውን መረጃ እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቧል።ለላስ ቬጋስ ፖሊስ ተጨማሪ መረጃ ያለው በስልክ ቁጥር 702 828 3111 ወይም በቬጋስ ለሚኖሩ በ311 መደወል ለተጎጂዎች ለመርዳትም የጎፈንድ ሚ አካውንት ተከፍቶ እርዳታ እየተሰባሰበ ነው።

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 ወይም 712-432-8451 በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *