Hiber Radio: ክርክር – በአበበ ቶላ እና በአቻምየለህ ታምሩ | በኢትዮጵያ የትግራይ የበላይነት አለ ወይስ የለም? | ያድምጡ – ይሳተፉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ  5639993994 ወይም 563999-3988 1641-793-8229 ወይም 1641-715-8596  በመረጡት ቁጥር መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን፣ googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

One Comment on “Hiber Radio: ክርክር – በአበበ ቶላ እና በአቻምየለህ ታምሩ | በኢትዮጵያ የትግራይ የበላይነት አለ ወይስ የለም? | ያድምጡ – ይሳተፉ”

  1. እውነት የትግራይ የበላይነት አለ?
    የትግራይ ህዝብ እና ሕወሓትስ አንድ ናቸው?
    በኢትዮጵያስ አፓርታይድ አለ?
    እነዚህ እና ሌሎች ጉዳዮች አንስተው አበበ ቶላ (Abe Tokicho) እና አቻምየለሽ ታምሩ ክርክር ሰምቼ የለገሠ አስፋው ንግግር እንዳስታወስ አስገደደኝ
    በ1980 ዓ.ም በመቐለ ማዘጋጃ ቤት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ሰብስበው እንዲህ ብለውን ነበር፤
    “ዓሣ ባህር ውስጥ ገብቶ ውሃ ሳይነካ አይወጣም። ወንበዴ ትግራይ እየኖረ የትግራይ ህዝብ ወያኔ አደለም ለማለት ይከብዳል ዓሣውን ለመጨረስ ደግሞ ውሃውን ማድረቅ ነው ያለብን” ብለው ዛቻና ፍከራ ሰነዘሩ ይህንን በተናገሩ ሦስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የትግራይ ከተሞች በአውሮፕላን ቦንብ ጋዩ። የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል እንደሚባለው የፈራነው አልቀረም፤ የጋደኛዬ ቤተሰቦች በአንድ ጀምበር ሓውዜን ላይ አለቁ። ይህንን ያስቆጣው የትግራይ ሕዝብ ለህልውናው ሲል ከአፍሪካ ተወዳዳሪ የሌለው የደርግ ጦር ከሌሌች ህዝቦች በመሆን ድምጥማጡ አጠፉት።
    ህዝብ እንደ ጠላት መፈረጅና ለማጥፋት መሞከር ከመሬት በታች ይከታል።
    የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ እምብርት ነው። የትግራይ ህዝብ የመፍትኄ አካል እንጁ ጠላት ሁኖ አያውቅም።
    ድርጅትና ህዝብ አንድ አደለም።
    የለገሠ አስፋው ፍረጃና ፉከራ አሁንም እየሰማን ነን ቆም ተብሎ ቢታሰብበት። የትግራይ ህዝብ ቢቃዎምም ዝምታ የመረጠው በዚህ ምክንያት ነው።
    ለአቤ ቶክቾ አድናቆቴ እገልፃለሁ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *